icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ሄል-ዳይቨርስ 2 ውስጥ የተካተተውን አዲሱን `ላስ-16 ሲክል` መሣሪያን እንዴት መክፈት ይቻላል?

በሄል-ዳይቨርስ 2 ሃሴትን ይቀዳጁ ፥ በአሮው-ሄድ ቪዲዮ ጌሞች ስቱዲዮ የተሰራው ቪዲዮ ጌም ቀድሞ ከተለቀቀው ምዕራፍ ይበልጥ ተጫዋቾቹን ለማስደሰት በድጋሚ መቷል ፣ በአዲሱም ምዕራፍ ተጫዋቾች በምናበ አፅናፈ-ዓለማት ውስጥ በጀብድ የተሞሉ እና የጋለ-ስሜት ውስጥ የሚያስገቡ ውጊያዎች ውስጥ ራሳቸውን እንዲያገኙ የማድረግ አቅምን ይዞ ነው የመጣው።

በዚህ በጀብድ እና በውጊያዎች በተሞላበት ዓለም ተጫዋቾች እጅግ በጣም በርካታ የጦር መሳሪያዎች አማራጮችን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ፥ ከጠመንጃ እስከ ነበልባል መወርወሪያ ድረስ የተለያዩ እና ዘርፈ ብዙ የጦር መሣሪያ ክምችቶች የሚገኙ ሲሆን ፥ እያንዳንዱ መሳሪያም ጠላትን ማንበርከክ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ አገልግሎትን ይሰጣሉ። በዚህ መመሪያም አደገኛውን ላስ-16 ሲክል እንዴት እጅዎ ማስገባት እንደሚችሉ እና ጦር ሜዳውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ እናያለን።

በሄልዲቨርስ 2 ውስጥ የተካተተውን አዲሱን የላስ-16 ሲክል መሳሪያ ፥ ከጦር መሳሪያ መሸጫ መደብር በ20 ሜዳሊያዎች መግዛት የሚችሉ ሲሆን ፥ ይህን የልብ-አድርስ መሳሪያ በውጊያ ወቅት በመጠቀም ጠላት ላይ ከባድ ውድመትን ማድረስ ያስችሎታል።

ጨዋታቸውን የበለጠ አጓጊ ማድረግ የሚፈልጉ ተጫዋቾች ፥ የዋር-ቦንድ የውጊያ ማለፊያ (Warbond Battle Pass) አስደሳች አማራጮችን የሚሰጥ ሲሆን ከነዛም ውስጥ እንደ ፥ ጦር መሳሪያ መከላከያ ትጥቆች ፣ የጦር መሳሪያ ገፅታ መለዋወጫዎችን ፣ እና ወታደርዎን እንደፍላጎቶ ማስተካከል እና ማዘመን ያስችሎታል።

ልዕሏ ምድር (Super Earth) እነዚህን መልዕክቶች በይፋ አፅድቃለች።

ሄል-ዳይቨርስ ትብብርዎን ይሻል ፥ ማኔጅድ ዲሞክራሲን ወደ ጋላክሲው ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ፥ ፕለይ-ስቴሽን 5 እና ፒሲ ላይ ይቀላቀሉ።

ፒኤስ 5: https://t.co/U6Kmi8LciU

እስቲም: https://t.co/bkbHdXMQwEhttps://t.co/R5JX02iIs4

- ሄል-ዳይቨርስ™ 2 (@helldivers2) መጋቢት 13፣ 2024 እ.ኤ.አ

ሆኖም ሄል-ዳይቨርስ 2 ለኤክስ-ቦክስ ተጠቃሚዎች ባለመዘጋጀቱ ተጫዋቾች ላይ ቅሬታን የፈጠረ ሲሆን ፥ ከ80,000 በላይ ፊርማዎችን ቢሰበስቡም ፣ እስካሁን የኤክስ-ቦክስ ተጫዋቾች ለጥያቄያቸው መልስ አላገኙም። ይህም ሆኖ ግን ሄል-ዳይቨርስ 2 የእዚህ ዓመት ምርጥ ቪዲዮ ጌም መሪነቱን ተቆናጦ ቀጥሏል።

ለማስታወስ ያህል በአሮው ሄድ የቪዲዮ ጌሞች ስቱዲዮ እና በሶኒ ኢንተራክቲቭ ኢንተርቴንመንት ትብብር የተሰራው ሄል-ዳይቨርስ 2 የካቲት 8 ቀን 2024 ለፕለይ ስቴሽን 5 እና ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ተጫዋቾች ለጨዋታ በቅቷል።

ጅማሬውን አ.ኤ.አ በ2015 ያደረገው የሄል-ዳይቨርስ ተከታይ ምዕራፍ ትልቅ ለውጦችን ይዞ ነው የመጣው።  የመጀመርያው ምዕራፍ የአይሶሜትሪክ እይታ የነበረ ሲሆን ፥ አዲሱ ምዕራፍ ደግሞ የሦስተኛ ወገን እይታን (third-person perspective) ይዞ መጥቷል ፣ ይህም ይበልጥ ተመራጭ ያደርገዋል

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !