
ያለምንም ጥርጥር ሄል-ዳይቨርስ 2 የወቅቱ አስደናቂ ጨዋታ ነው። በአሮው-ሄድ ቪዲዮ ጌሞች ስቱዲዮ የተሰራው ቪዲዮ ጌም እንደቀድሞው ተጫዋቾቹን ለማስደሰት በድጋሚ የመጣ ሲሆን ፣ በአዲሱም ምዕራፍ ተጫዋቾች በምናበ አፅናፈ-ዓለማት ውስጥ በጀብድ የተሞሉ እና የጋለ-ስሜት ውስጥ የሚያስገቡ ኃይለኛ ውጊያዎች ውስጥ ራሳቸውን እንዲያገኙ የማድረግ አቅምን ይዞ ነው የመጣው። በዚህ በድርጊቶች የተሞላ ጨዋታ ፥ ተጫዋቾች እጅግ በጣም በርካታ የጦር መሳሪያዎች አማራጭ የቀረበላቸው ሲሆን ፣ እያንዳንዱ መሳሪያም ጠላትን የማንበርከክ ልዩ አቅም ያላቸው ናቸው። ከሽጉጥ እስከ ጠመንጃ ድረስ ያሉ አጋዥ መሣሪያዎች የተካተቱ ሲሆን ፣ የተዘጋጁት የመሳርያ አማራጮችም ፥ ሁሉም ተጫዋቾች ከጨዋታ ዘይቤያቸው ጋር ተስማሚ የሆኑ መሳሪያዎችን እንዲያገኝ ያስችለዋል።
ከሄል-ዳይቨርስ 2 አስደናቂ መሳሪያዎች መካከል ኤም-105 ስታልዋርት ፥ ጦር ሜዳ ላይ ባለው ጠላትን የማሽመድመድ አቅሙ ይታወቃል። ታድያ ይህን አደገኛ መሳሪያ እንዴት መክፈት ይቻላል? መልሱ ቀላል ነው ፥ ከእርስዎ የሚጠበቀው ደረጃ 2 ላይ መድረስ እና በቀጥታ ከመሳሪያዎች መደብር በ3,500 ዋር-ቦንዶች (warbonds) ብቻ የግልዎ ማድረግ ነው። የመቋቋም አቅማቸው አነስተኛ ከሆኑ ግዙፍ ጠላቶች ጋር በሚደረግ ውጊያ ወቅት ይህ መሳሪያ ቁልፍ ሚናን ይጫወታል። ሆኖም ግን ፣ ኤም-105 ስታልዋርት የመሳሪያ መከላከያን የታጠቁ ሠራዊቶች ላይ ጉዳትን የማድረስ አቅሙ አነስተኛ እንደሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል።
ጨዋታቸውን የበለጠ አስደሳች እና አጓጊ ማድረግ ለሚፈልጉ ተጫዋቾች ፥ የዋር-ቦንድ የውጊያ ማለፊያ (Warbond Battle Pass) አስደሳች አማራጮችን ይሰጣል። ይህን ማለፊያ በመግዛት ፣ ተጫዋቾች እንደ ፥ የጦር መሳሪያ መከላከያ ትጥቆች ፣ የጦር መሳሪያ ገፅታ መለዋወጫዎች ፣ እና ልዩ የማስተካከያ አማራጮች እና በርካታ ማራኪ ሽልማቶችን እንዲያገኙ ያስችላል። በዚህ የውጊያ ማለፊያ ፥ ደረጃዎችን እየጨመሩ በመጡ ቁጥር በሚያገኟቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሽልማቶች የችሎታዎን ጣሪያ ማሳየት ይችላሉ።
እንደ አለመታደል ሆኖ ፥ ሄል-ዳይቨርስ 2 ለኤክስ-ቦክስ ተጠቃሚዎች ባለመዘጋጀቱ በተጫዋቾች ዘንድ ቅሬታን አስተናግዷል። ተጫዋቾች ሄል-ዳይቨርስ 2 ኤክስ-ቦክስ ላይ እንዲገኝ ያላቸውን ፍላጎት የሚገልፅ ከ80,000 በላይ ፊርማዎች ቢሰበስቡም ፣ እስካሁን ግን ለጥያቄያቸው መልስ አላገኙም። አሁንም ግን በተስፋ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
ይህንን አስደሳች ጨዋታ ሰፊው የቪዲዮ ጌም ማህበረሰብ የመጫወት ዕድልን ስለሚሰጥ ፥ ሄል-ዳይቨርስ 2 በቅርቡ ኤክስ-ቦክስ ዝርዝር ውስጥ እንደሚካተት ተስፋ እናደርጋለን።
እንደ ማጠቃለያ ፣ ሄል-ዳይቨርስ 2 ለቪዲዮ ጌሙ ዓለም ድንቅ ስራን አቅርቧል ፣ ይህም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ተጫዋቾች አስደናቂ የቪዲዮ ጌም ተሞክሮን የሚሰጥ ሲሆን ፥ በአስደናቂው አቀራረቡ ፣ በበርካታ የጦር መሳሪያ አማራጮቹ እና ልዩ የማስተካከያ አማራጮቹ ፣ በያዝነው 2024 አ.ኤ.አ ዓመት ከወጡ ምርጥ ቪዲዮ ጌሞች ውስጥ አንዱ የሚያደርገው ሲሆን ፣ ለጦርነት እና በጀብድ የተሞሉ ቪዲዮ ጌም አፍቃሪያንን ልብ በመግዛት ተቀዳሚ ምርጫ ሆኗል