
ሄል-ዳይቨርስ 2 በአሁኑ ጊዜ የቪድዮ ጌምች ዓለም ላይ ሞገዶችን እያስነሳ ይገኛል።. በአሮውሄድ ቪድዮ ጌም ስቱዲዮ የተሰራው ይህ ጌም ከቀድሞው ምዕራፍ ተሞክሮን በመውሰድ አዲሱን ምዕራፍ ወደ አዲስ ከፍታ ወስዶታል። ተጫዋቾች በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ በጀብድ የተሞሉ ውጊያዎች ላይ በመሳተፍ ድልን በመቀዳጀት ላይ ይገኛሉ።
በዚህ በድርጊቶች የተሞላ ዓለም ውስጥ ለተጫዋቾች የተዘጋጁ ከጠመንጃ እስከ ነበልባል መወርወሪያ ድረስ የተለያዩ እና ዘርፈ ብዙ የጦር መሣሪያ ክምችቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ የጦር መሣሪያዎች መካከል እጅግ አስፈሪው እና ባለ አስደናቂ አቅሙ "ፈንጂ" ጃር-5 ዶሚነተር ነው። ጥያቄ መሆን ያለበት ፥ ይህን መሣሪያ እንዴት ነው ማግኘት የሚቻለው?
ጃር-5 ዶሚናተርን ለመክፈት ፕሪሚየም ዋር-ቦንድን መግዛት አስፈላጊ ነው። ፕሪሚየም ዋር-ቦንድን አንዴ ከገዙ በኋላ ፥ ይህን አስደናቂ መሳሪያ ገጽ 3 ላይ በ80 ሜዳሊያዎች ማግኘት ይችላሉ። በከፍተኛ ጉዳት የማድረስ አቅሙ ፣ በአጭር ጊዜ ብዙ የተኩስ ዙሮች እና መጠነኛ የጦር መሳሪያ መከላከያ ትጥቆችን ዘልቆ በመግባት አቅሙ ፣ ጃር-5 ዶሚናተርን በሄል-ዳይቨርስ 2 የጦር አውድማዎች ላይ የድል መቀዳጃ ቁልፍ ያደርገዋል።
የጨዋታቸውን የበለጠ አስደሳች እና አጓጊ ማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎች ፕሪሚየም ዋር-ቦንድ የውጊያ ማለፊያ (Premium Warbond Battle Pass) ብዙ ማራኪ ሽልማቶችን ይሰጣል። ከነዚያም መካከል ፣ ከጦር መሳሪያ መከላከያ ትጥቆች እስከ የጦር መሳሪያ ገፅታ መለዋወጫዎች ፣ እና ልዩ የማስተካከያ አማራጮች በውስጡ የያዘ ሲሆን ፥ ይህም ጨዋታዎን እንደፍላጎትዎ እና የፈለጉት ርቀት ያህል ማስኬድ ያስችልዎታል።.
ሆኖም ሄል-ዳይቨርስ 2 ለኤክስ-ቦክስ ተጠቃሚዎች ባለመዘጋጀቱ ተጫዋቾች ላይ ቅሬታን የፈጠረ ሲሆን ፥ ከ80,000 በላይ ፊርማዎችን ቢሰበስቡም ፣ እስካሁን የኤክስ-ቦክስ ተጫዋቾች ለጥያቄያቸው መልስ አላገኙም።
ፉክክርን የሚሹ ብቸኛ ተዋጊም ይሁኑ ፣ የቡድን ተዋጊ ፣ ሄል-ዳይቨርስ 2 ለሁለቱም የሚሆን አስደሳች እና አጓጊ የጨዋታ ተሞክሮ ያቀርባል ፣ ሄል-ዳይቨርስ ላይ ሁሉም ሰከንዶች በጋሉ ደስታዎች የተሞሉ ናቸው።.