"የጨዋታ ጣቢያን መቀላቀል አለመቻል" ፡ ሄል-ዳይቨርስ 2 ላይ የሚያጋጥሙ ብልሽቶችን እንዴት ማስተካከል ይቻላል?

በ2024 እ.ኤ.አ. እጅግ በጣም በጉጉት የሚጠበቁ ብዙ ቪድዮ ጌሞች የሚወጡበት ዓመት ነው ፣ ከአነዚህም መካከል ሄል-ዳይቨርስ 2 ግንባር ቀደሙ እና ዋነኛው ነው። ከብዙ ጥበቃ በኋላ ፥ ይህ የሶስተኛ ወገን ተኳሽ እይታን (third-person shooter) ፣ እና ከአንድ በላይ ተጫዋቾችን ማስተናገድ የሚችለው ቪድዮ ጌም ፣ በስተመጨረሻ ፥ የካቲት 8 ፣ ሐሙስ ቀን ጀምሮ ተጫዋቾች አስደናቂውን የውጊያ እና ስልታዊውን ዓለም እንዲያስሱ ፥ ኮምፒውተር (PC) እና ፒኤስ5 (PS5) ላይ ለጨዋታ በቅቷል፣
ነገር ግን ፣ ብዙውን ጊዜ ኦንላይን ቪድዮ ጌሞች ላይ እንደሚስተዋለው ፣ በጣም የሚጠበቁ እና ገናና ስም ያላቸው ቪድዮ ጌሞችም ላይ አልፎ አልፎ ቴክኒካዊ ብልሽቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። ተጫዋቾችን ብዙ ጊዜ ከሚያጋጥማቸው ጉዳዮች አንዱ ፥ በጓደኛም ይሁን በሌላ ተጫዋች የተጀመረ የጨዋታ ጣቢያን መቀላቀል አለመቻል ነው።
ይህን ትግስት ሊፈታተን የሚችል እክል በተቻለ ፍጥነት ለመቅረፍ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በሚሰሩት አዘጋጆችም ዘንድ የታወቀ ነው። ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስም ፥ እክሉን ለማስወገድ የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ነጥቦችን ቡድኑ አጋርቷል።
የመጀመሪያው መፍትሄ ፥ ልዩ የጨዋታ መድረኮችን (crossplay) ማጥፋት እና የተጫዋች መፈለጊያ አማራጭን ወደ "ጓደኞች ብቻ" (Friends only) መቀየር ሲሆን ፥ ይህንን ለማድረግ በቀላሉ ጨዋታውን በማቆም ፣ "ማስተካከያ" ዝርዝሮች ገፅ (Setting menu) ውስጥ በመግባት ፣ ልዩ የጨዋታ መድረኮች (crossplay) ያጥፉ እና የተጫዋች መፈለጊያ አማራጭን ወደ "ጓደኞች ብቻ" (Friends only) ይቀይሩ። ይህን ዘዴ የተጠቀሙ በርካታ ተጫዋቾች ችግሩን መፍታት እና የጨዋት ጣቢያዎችን ያለችግር መቀላቀክ አስችሏቸዋል።
በአንዳንድ ተጫዋቾች የተሰጠው ሌላው መፍትሄ ራስ-ሰር ሂደቶች (Automatons) መቆጣጠሪያ ክፍልን በመክፈት ከትዕዛዝ ክፍልዎ (command room) ፈጣን ጨዋታን ማስጀመር ነው። እንደ አማራጭም ፣ ለብቻዎ ጨዋታውን ያስጀምሩ እና ጨዋታው ከተጅመረ በኋላ የእርዳታ ስልትን (SOS stratagem) ተጠቅመው ሌሎች ተጫዋቾች እንዲቀላቀሉዎት ማድረግ ይችላሉ።
ይሁን እንጂ ከላይ የተቀመጡት መፍትሄዎች ለሁሉም ሰው ላይሰሩ እና ሌሎች እክሎች በጨዋታ ወቅት ሊከሰቱ እንደሚችሉ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፦ አንዳንድ ተጫዋቾች የመቆጣጠሪያ ስርዓቱ (nProtect) ጋር በተገናኘ ፈጣን ጨዋታዎችን መቀላቀል እንደተቸገሩ እና ከጨዋታው የጸረ-ማጭበርበር ስርዓት ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዳጋጠሟቸው ገልጸዋል።
እነዚህ ጥቃቅን ቴክኒካል ችግሮች ቢኖሩም ፣ በጋለ-ድርጊቶች እና ገድሎች የተሞላው ሄል-ዳይቨርስ 2 ተጫዋቾችን ማስደሰቱን ቀጥሏል። ትንሽ ትዕግስት እና ብልሃት ካለዎት ፥ በእርግጠኝነት ይህን የጋላክሲዎች ጀብዱ ሙሉ በሙሉ ማጣጣም እና ከጓደኞችዎ ጋር በመሆን በጣም ፈታኝ የሆኑትን የአጽናፈ ሰማያት ውድድሮችን ማሸነፍ ይችላሉ።