icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

አልቢዮን አንላይን ላይ የሚገኙ ግብዓቶች ዝርዝር ፡ የትኛው ይበልጥ ተመራጭ ነው? 

አልቢዮን ኦንላይን ጌም ከአንድ በላይ ተጫዋቾችን ማሳተፍ የሚችል እና የቪዲዮ ጌም ዘርፍ ላይ አብዮት ያስነሳ እና ፣ የፈለጉትን የጨዋታ ዘይቤ ማዋቀር የሚችሉበት ልዩ የኦንላይን ጌም ነው። የገፀ-ባህሪዎን አቅም ማሳደግ የሚችሉ የተለያዩ አማራጮችን እና የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ወደ ውግያውን ዓለም ለመቀላቀል ይዘጋጁ! 

አልቢዮን ኦንላይን የተለያዩ ግብዓቶች ያሉት ሲሆን ፣ እያንዳንዱም የተለያየ የጨዋታ ተሞክሮ ይሰጣሉ፡ 

  • ጦር (The Spear)፡- ይህ መሳሪያ በፍጥነት ለመንቀሳቀስ እና ጦር ሜዳ ላይ ጠላቶችን በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚጠቅም ሲሆን፣ ለብቻዎም ይሁን በቡድን ለመዋጋት ያገለግላል። 

  • ድርብ ሰይፎች (The Dual Swords)፡- ይህ መሳሪያ በፍጥነት መንቀሳቀስ እና ከባድ ጉዳት ማድረስ የሚያስችልዎ ሲሆን ፣ የቅርብ ውግያ እና የግል አሰሳ ወዳጅ በሆኑ ተጫዋቾች ዘንድ ተመራጭ ነው። 

  • አስማታዊው በትር (The Esoteric Staff)፦ ይህ መሳሪያ ከሩቅ ሆነው መዋጋት እንዲችሉ እና የጦር ጓዶችዎን ማገዝ የሚያስችልዎ ሲሆን ፣ ከጥቃት የመከላከል አቅሙ ግን አነስተኛ ነው። 

  • የውግያ መጥረቢያ (The War Axe)፡- ይህ ከባድ መሳሪያ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚያስችልዎ ሲሆን ፣ ለብቻዎም ይሁን በቡድን ለመዋጋት ይጠቅማል። 

  • መስቀለኛው ቀስት (The Light Crossbow)፡- ይህ ዘርፈ ብዙ መሳሪያ ፥ ከሩቅ ሆነው ጥቃት ለማድረስ ፣ ጠላቶትን ለማዳከም እና ፣ የተነጣጠረ ዒላማ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ይጠቅማል። 

  • ታላቁ እሳት ተኳሽ በትር (The Great Fire Staff)፡- ይህ መሳሪያ ባለ ከፍተኛ ኃይል አስማትን በመጠቀም ከሩቅ ጠላቶችን መቆጣጠር የሚያስችል ቢሆንም ፣ የመንቀሳቀስ ፍጥነትዎን ግን ይገድባል። 

  • ህይወት ማደሻ (The Nature Staff)፡- ለጦር ጓዶችዎ ድጋፍ ለመስጠት ፣ ለመፈወስ እና ተፈጥሯዊ ጉዳት ለማድረስ ያስችሎታል። 

  • ቀስት (The Bow)፡- ይህ መሳሪያ ከሩቅ ጥቃት እንዲያደርሱ እና ጦር ሜዳ ላይ በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ ያስችሎታል። 

  • ታላቁ ድግምታዊ በትር(The Great Cursed Staff)፡- ይህ መሳሪያ ምትሃትን በመጠቀም ከርቀት ጠላት ላይ ዘለግ ያለ ጥቃት ለማድረስ እና ለመቆጣጠር ያስችላል። 

  • የጦር ጓንት (The Battle Gauntlets)፡- ይህ መሳርያ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ እራሶን እና የጦር ጓዶችዎን ከጠላት እየጠበቁ በተመሳሳይ ሰዓት ጥቃት ማድረስን ያስችሎታል። 

የአልቢዮን ኦንላይን ተጫዋቾች ቢያሻቸው ውግያ ፣ እርዳታ ወይም አሰሳን ማድረግ የሚያስችሏቸውን አማራጮች በመጠቀም በነፃይቱ ዓለም ላይ የራሳቸውን ጀብድ የመፍጠር ነጻነት ተሰጧቸዋል። በእውነቱ ከሆነ "ምርጥ" የሚባል ግብዓት የለም ፣ ሁሉም በአጨዋወት ዘይቤ እና ፍላጎት መሰረት የሚወሰኑ ናቸው። ሆኖም ግን ፣ ታላቁ ድግምታዊ በትር ፣ ቀስት እና የጦር ጓንት በተጫዋቾች ዘንድ ተመራጭ ናችው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !