
የፊታችን ሰኞ ፣ ሚያዝያ 29 2024 እ.ኤ.አ ፣ አልቢዮን ኦንላይን አውሮፓ ለሚገኙ የቪዲዮ ጌም አፍቃሪያን አዲስ ሰርቨር በማዘጋጀት አዲስ ታሪክ የሚሰራበት ዕለት ሲሆን ፣ አዲሱም ሰርቨር አውሮፓ ፣ ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ (MENA Region) ለሚገኙ ተጫዋቾች አስደሳች ተሞክሮን ለመስጠትን ታልሞ የተዘጋጀ እና አዲስ ጅምርን የሚያመላክት ሲሆን ፣ አውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾችን እጅጉን በተሻሻለ የኢንተርኔት ግንኙነት እንዲጫወቱ ያስችላል። ይህም ተጫዋቾች የአልቢዮን ቆይታቸውን ሀ ብለው እንዲጀምሩ እና ባለፉት ሰባት ዓመታት ያካበቱትን ልመድ በመጠቀም ጨዋታውን እንዲያጣጥሙ ያስችላቸዋል ።
አልቢዮንን መጫወት ከመጀመርዎ በፊት የጌሙን መሠረታዊ ነጥቦች መረዳት ተገቢ ሲሆን ለዚህም ተብሎ በጌም ውስጥ ስለሚገኙ የተለያዩ ግብዓቶች ፣ ችሎታዎች እና የጦር ስልቶች በዝርዝር የሚገልጽ አጋዥ መመሪያ ጌሙ ውስጥ ተካቷል። ከመጫወትዎ በፊት እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች መረዳት ጌሙን ይበልጥ እንዲያጣጥሙት ይስችሎታል።
አልቢዮን ኦንላይን ላይ ከፈለጉ የደፋር ተዋጊ ፣ የተዋጣለት የእጅ ጥበብ ባለሙያ ወይም የወንበዴ ነጋዴ ገፀ-ባህሪ ሆነው መጫወት ይችላሉ። ከእርስዎ የሚጠበቀው መላበስ የሚፈልጉትን ገፀ-ባህሪ መምረጥ እና በሱ ልምድዎን ማካበት ብቻ ነው። በተጨማሪም ከተካተቱት የጦር መሳሪያ ዝርዝሮች ውስጥ ከአጨዋወት ዘይቤ ጋር የሚስማማ መሳሪያ መምረጥዎን አይዘንጉ።
ምንም እንኳን ብዙ ተልኮዎችን ለብቻዎ መወጣት ቢችሉም ፣ አልቢዮን በህብረት በሚንቀሳቀሱ ቡድኖች የሚገዛ ዓለም ነው። በቡድን መንቀሳቀስ ለብቻዎ መወጣት የማይችሏቸውን መሰናክሎችን ማለፍ የሚያስችል ሲሆን ፣ ቡድኖችን በመቀላልቀል ወይም ጓደኞችዎ/ሌሎች ተጫዋቾች ጋር ህብረት በመፍጠር የተለያዩ ስልቶችን ሊማሩ ፣ በትግል ወቅት እርዳታን ሊያገኙ ፣ እና ብቻዎን ማሳካት የማይችሏቸውን ተግዳሮት መወጣት ይችላሉ።
የአልቢዮን ኦንላይን ኢኮኖሚ ልክ እንደ ገሃዱ ዓለም ኢኮኖሚ ሁሌ ተለዋዋጭ ነው። ነገሮችን በርካሽ ገዝቶ በውድ መሸጥ ፣ ጠቃሚ ሀብቶችን መሰብሰብ እና ገንዘብዎን በጥበብ ኢንቨስት ማድረግን መማር በዚህ በፉክክር የተሞላ ዓለም ውስጥ ለመበልጸግ እና የሀብት ማማን ለመቆናጠጥ ያስችላል!
በተጨማሪም የአልቢዮን ዓለም በአደጋዎች የተሞላ ዓለም በመሆኑ አካባቢዎን በሚገባ በማጥናት እና ከአላስፈላጊ ጀብዶች በመቆጠብ ፥ ራስዎን ከዱር እንስሳት ፣ ተቃራኒ ቡድኖች እና ድበቅ ወጥመዶች ራስዎን በጠበቅ አይዘንጉ።
ሁሉም ሰው አልቢዮን ኦንላይን ላይ አላስፈላጊ ስህተቶችን ይሠራል ፣ ይሄም ምንም ማለት አይደለም! በውድቀት ተስፋ ሊቆርጡ ሳይሆን የሚገባው ፣ ከስህተት በመማር የተሻለ ተጫዋች ለመሆን መሞክር የአስተዋዮች መርህ ነው።