icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

በአልቢዮን ኦንላይን ላይ የሚገኙ ሁሉም የጦር መሳሪያዎች ዝርዝር መግለጫ 

አልቢዮን የኦንላይን ቪዲዮ ጌም ልዩ ችሎታዎችን እና “ደረጃዎችን” በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን ፥ በጨዋታው ውስጥ ማከናወን የፈለጓቸው ነገሮች ላይ ሙሉ ቁጥጥር ስለሚኖርዎት ፥ በቂ ልምድ እንዲያገኙ እና የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ችሎታዎን እንዲያሳድጉ ያስችልዎታል። 

ጌሙ ውስጥ ሶስት ዋና ምድቦች ያሉ ሲሆን እነሱም፦ የከባድ ትጥቆዎች ምድብ ፣ የመካከለኛ ትጥቆዎች ምድብ እና የቀላል ትጥቆዎች ምድብ ናቸው። በጌሙ ውስጥ ያለዎት "ደረጃዎችን" የሚወሰነው እያንዳንዱ ምድቦች በሚያቀርቧቸው ንዑስ ክፍሎች ሲሆን ፥ ይህም የጦር መሣሪያዎችን እንዲያገኙ ያስችልዎታል። ሆኖም ግን እነዚህ ምድቦች እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ልብ ሊሉ ይገባል። ለምሳሌ፦  የከባድ ትጥቆዎች ምድብ ፥ ከፍተኛ አካላዊ ጥበቃን የሚሰጥ ቢሆንም ጉርሻዎችን የማግኛ እድሎች ግን የመነመኑ ሲሆኑ ፣ የቀላል ትጥቆዎች ምድብ ደግሞ በተቃራኒው ይሆናል ማለት ነው። 

በሶስቱ ምድቦች ውስጥ የሚገኙ የጦር መሳሪያዎች አጠቃላይ ዝርዝር፡ 

የከባድ ትጥቆዎች ምድብ:- 

  • ሰይፍ (Sword)፡- ጥቃት ማድረሻ 

  • መጥረቢያ (Axe)፦ ጥቃት ማድረሻ 

  • መከትከቻ (Mace)፡- ለፊት-አውራሪ ወታደሮች የተዘጋጀ እና ፣ የጠላትን ልዩ የማጥቃት አቅም መንጠቅ የሚችል 

  • መዶሻ (Hammer)፡- ለፊት-አውራሪ ወታደሮች የተዘጋጀ እና ፣ ጠላትን ለተወሰነ ጊዜ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ የሚችል 

  • ጋሻ (Shield)፡- ለፊት-አውራሪ ወታደሮች ተጨማሪ የመከላከል አቅምን የሚሰጥ 

የመካከለኛ ትጥቆዎች ምድብ: 

  • ቀስት (Bow)፦ ጥቃት ማድረሻ 

  • ጦር (Spear)፡- ጥቃት ማድረሻ ፣ ለፈጣን ጥቃት እና ጠላት እርምጃ ሳይወስድ አስቀድሞ ጥቃት መጣል የሚያስችል 

  • ህይወት ማደሻ (Nature Staff)፡- ድጋፍ እና ፣ ፈውስ የመስጠት አቅም ያለው 

  • ጩቤ (Dagger)፦ ጠላትን ለመጉዳት ፣ እና የተነጣጠረ ጥቃት ለማድረግ የሚያስችል 

  • ዘንግ (Quarterstaff)፡- ለልዩ ድጋፍ ፣ እና ጠላትን ከክልል ገፍቶ ማስወጣት የሚያስችል 

  • ብቃት መጨመሪያ (Torch)፡- ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ማለትም (ፈጣን ጥቃት የማድረስ አቅም ፣ ልዩ ብቃቶችን የመጠቀም ድግግሞሾችን መጨመር ወይም ከፍተኛ የማጥቃት አቅምን) የሚሰጥ 

የቀላል መሳርያ መከላከያ ትጥቆዎች ምድብ: 

  • እሳት ተኳሽ በትር (Fire Staff):- በጊዜ ሂደት ጠላይ ላይ ጉዳት ማድረስ የሚችል 

  • ከለላ ሰጪ ምትሃታዊ በትር (Arcane Staff):- አስማታዊ ጋሻዎችን መፍጠር የሚያስችል እና ከፍተኛ ጉዳትን ማድረስ የሚያስችል  

  • የፈውስ በትር (Holy Staff):- የአንድ ገፀ-ባህሪን ህይወት ማደስ የሚያስችል 

  • በረዶ ተኳሽ በትር (Frost Staff) ፦ ጠላት ላይ ጉዳት ለማድረስ እና ፣ በአካባቢው ላይ ያለ እንቅስቃሴን ማዝገም የሚያስችል  

  • ድግምታዊ በትር (Curse Staff)፦ በጊዜ ሂደት ጠላይ ላይ ጉዳት ማድረስ የሚችል እና የጠላትን አቅም የሚያዳክም  

  • የአስማት መጽሐፍ (Book)፡- አቅምን ወይም ድግምታዊ ኃይልን ማደስ የሚያስችል 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !