
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና ለብዙ ዓመታት በኤክስ-ቦክስ እና በፒሲ መድረኮች ላይ ብቻ ይገኝ የነበረው ፣ ሲ ኦፍ ቲፍት (Sea of Thieves) በ12ኛ ምዕራፉ ለቪዲዮ ጌም አፍቃሪያን አስደሳች ዜና ይዞ መቷል! ፥ አሁን ደግሞ ተደራሹነቱን በማስፋት የሶኒ የቪዲዮ ጌም መድረክ በሆነው ፕሌይስቴሽን 5 (PS5) ላይ ለጨዋታ በቅቷል።
ሲ ኦፍ ቲፍት (Sea of Thieves) የኤክስቦክስ ስቱዲዮ ጌሞች ከሆኑት ፥ ሃይ-ፋይ ረሽ (Hi-Fi Rush) ፣ ፔንቲመንት (Pentiment), እና ግራውንድድ (Grounded) ቀጥሎ በዚህ ዓመት ታዋቂ የሆነውን የቪዲዮ ጌም መድረክ ፒኤስ-5ን በመቀላቀል አራተኛ ነው። ሲ ኦፍ ቲፍት (Sea of Thieves) በተጨዋቾች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠበቀ ሲሆን ፣ በጉጉት ከሚጠብቁት መካከል አንዱ ከሆኑ እና ፒኤስ-5 ላይ የሚለቀቅበትን ቀን ማወቅ ከፈለጉ ማንበብዎን ይቀጥሉ።
ልዩ/ፕሪሚየም እትም
ሲ ኦፍ ቲፍት (Sea of Thieves) እስከሚለቀቅ መታገስ ካልቻሉ አያስቡ ፥ ልዩ/ፕሪሚየም እትሙን ቀድመው በማዘዝ ከመለቀቂያው አምስት ቀናት በፊት ማለትም ሀሙስ ፣ ሚያዚያ 25 ቀን ከጠዋቱ 05፡00 ላይ በእጅዎ ማስገባት እና ጨዋታዎን መጀመር ይችላሉ። በተጨማሪ ልዩ/ፕሪሚየም እትሙን ሲገዙ ልዩ አልባሳት እና ማስተካክያዎች በስጦታ መልክ ያገኛሉ።.
መደበኛ እና የተሻሻለ/ዴሉክስ እትም
መደበኛ እና የተሻሻለ/ዴሉክስ እትሙ ማክሰኞ ፣ ሚያዚያ 30 ቀን ከጠዋቱ 05፡00 ሰዓት ላይ የሚለቀቅ ይሆናል። መደበኛ ዕትሙ ቪዲዮ ጌሙን እና አንዳንድ ሽልማቶችን የሚያካትት ሲሆን ፣ የተሻሻለው/ዴሉክስ ዕትሙ ደግሞ ልዩ/ፕሪሚየም ዕትሙ ውስጥ ከሚገኙ ጥቂት ልዩ ነገሮች በስተቀር ሁሉንም ልዩ ይዘቶች ያካትታል።
የልዩ/ፕሪሚየም እትም ባለይዞታዎች ቪዲዮ ጌሙን አሁን ማውረድ የሚችሉ ሲሆን ሚያዚያ 25 ቀን በአዘጋጆቹ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።
የሲ ኦፍ ቲፍት (Sea of Thieves) ተጫዋቾች ሰፊውን ውቅያኖስ የሚያስሱ ሲሆን ፥ እያንዳንዳቸው የመሾፈር ፣ የመርከብ ሸራ የመዘርጋት እና መድፍ የመተኮስ እና የተለያዩ ኃላፊነቶችን ይወጣሉ። ተልዕኮዎችን መወጣት ፣ ሀብቶችን ማከማቸት ፣ እንደ ክራከንስ እና ሜጋሎዶኖስ የሚባሉ ከተለያዩ ጭራቆች ጋር መጋፈጥ ፣ እና ከሌሎች ወንበዴዎች እና በኤ.አይ-የሚንቀሳቀሱ የጠላት መርከቦች ጋር ውጊያ ማድረግ ይችላሉ።
የሲ ኦፍ ቲፍት (Sea of Thieves) የጋራ ዓለም በመሆኑ ተጫዋቾች ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር በባህር አሰሳ ወቅት ይገናኛሉ። ሆኖም ተጨዋቾች ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር ሳይገናኙ ለብቻቸው ወይም ከጓደኞቻቸው ጋር ብቻ ለመጫወት"The Shores of Plenty" የተባለ የራሳቸውን ሰርቨር የመፍጠር አማራጭ አላቸው።