
አስደሳች ዜና! ለሁሉም የባህር ላይ ወንበዴዎች! መልሕቃችሁን ለመፍታት ተዘጋጁ! ምክንያቱም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና ለብዙ ዓመታት ፒሲ ፣ ኤክስ-ቦክስ አንድ ፣ ኤክስ-ቦክስ ኤክስ እና ኤክስ-ቦክስ ኤስ ላይ ብቻ ይገኝ የነበረው ፥ ሲ ኦፍ ቲፍስ (Sea of Thieves) ፣ የፕሌይስቴሽን 5 (PS5) ተጫዋቾችን የመርከብ አሰሳው ላይ ለማሳተፍ ፣ ሚያዚያ 30 ቀጠሮ ይዟል። ይህ ለብዙዎች አስደሳች ዜና ሲሆን ከዚህ በኋላ የፒኤስ-5 ተጫዋቾች ሰፊው የኦንላይን ቪዲዮ ጌም ዓለም ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን የባህር ላይ አሰሳቸውን ማድረግ ያስችላቸዋል።
ይህንንም ዜና ተከትሎ በታዋቂው ማህበራዊ ገፅ ፣ ኤክስ ወይም (የቀድሞው ትዊተር) ላይ ልዩ የቪዲዮ ጌም መድረኮችን (Crossplay) ማስተናገድ ስለመቻሉ ጥያቄን አስነስቷል።
ሲ ኦፍ ቲፍስን (Sea of Thieves) ለመጫወት ፥ ፒኤስ-5 ልዩ የቪዲዮ ጌም መድረኮችን (Crossplay) ያስተናገዳል? አዎ በሚገባ ፣ ከእርስዎ የሚጠበቀው ብቸኛ ነገር ፣ የማይክሮሶፍት መለያዎን ከፕሌይስቴሽን መለያዎ ጋር ማገናኘት ብቻ ነው። መለያዎን ከፒኤስ-5 ጋር ካገናኙ በኋላ ፥ የትኛውንም ዓይነት የቪዲዮ ጌም መድረክ (ፒሲ ፣ ኤክስ-ቦክስ አንድ ፣ ኤክስ-ቦክስ ኤክስ እና ኤክስ-ቦክስ ኤስ) የሚጠቀሙ ጓደኞችዎ ጋር መጫወት እና ቡድን መመስረት ይችላሉ።
ያስታውሱ! የተለያዩ የቪዲዮ ጌም መድረኮችን አገናኝተው ከጓደኞችዎ ጋር ለመጫወት ፥ በመጀመሪያ ፒሲን ወይም ኤክስ-ቦክስን በመጠቀም ጓደኞችዎን ማስገባት ያኖርብዎታል።
ፒሲ ወይም ኤክስ-ቦክስን በመጠቀም ጓደኞችዎን ለማከል የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፡-
ፒሲ ላይ ጓደኞችዎን ለማስገባት በመጀመርያ የኤክስ-ቦክስ መተግበሪያን ይክፈቱ → ወደ የማህበረሰብ ትር ይሂዱ → የጓደኛዎን ስም ይፈልጉ → ስም ይምረጡ → እና በመጨረሻ “ጓደኛን ለማከል” የሚለውን በመጫን ይጨርሱ።
ኤክስ-ቦክስ ላይ ጓደኞችዎን ለማስገባት በመጀመርያ መቆጣጠሪያዎ ላይ የሚገኘውን የኤክስ-ቦክስ ቁልፍ ይጫኑ → የተጫዋቾች ዝርዝር → ቀጥሎ መፈለግያውን በመጫን ፣ ማከል የሚፈልጉትን መለያ ይምረጡ እና “ጓደኛን ለማክል” የሚለውን ተጭነው ይጨርሱ።
ያስታውሱ ሲ ኦፍ ቲፍስ (Sea of Thieves) ከአንድ በላይ ተጫዋቾችን ማስተናገድ የሚችል የኦንላይን ቪዲዮ ጌም እንደሆነ ይታወቃል ፣ ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ የኢንተርኔት ግንኙነት ችግሮች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ከጓደኞችዎ ጋር ሰላማዊ እና የማይቋራረጥ ጨዋታ ማድረግ ይችሉ ዘንድ ሁልጊዜ ሰርቨሩ ጥገና ላይ አለመሆኑን ያረጋግጡ።