icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) ፋንተም ቡድን ወሳኝ ትጥቆች ፣ ማስተካከያዎች እና የጦር መሳሪያዎች ዝርዝር 

ኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) ትዊች (Twitch) በተባለው ድረ-ገፅ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን መሳብ የቻለ ተወዳጅ ቪዲዮ ጌም ነው። ቪዲዮ ጌሙ የመጀመሪያ ወገን እይታን (first-person shooter) የሚጠቀም ሲሆን ከቅርብ ጊዜ በኋላ አንጋፋ ከሆኑት ፣ ኮል ኦፍ ዲውቲ እና ዋር-ዞን (Call of Duty and Warzone) ጎራ በመመደብ ጠንካራ ተፎካካሪነቱ እያሳየ ይገኛል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ፣ በዩቢ-ሶፍት ኮኔክት (Ubisoft Connect) ያለምንም ክፍያ በነፃ መጫወት ማስቻሉ ተመራጭ ያደርገዋል። 

ኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) ላይ ተጫዋቾች ፣ ከ18 በላይ የጦር መሳሪያ አማራጮች ያሏቸው ሲሆን ፣ እያንዳንዳቸውም እንደምርጫቸው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ልዩ አባሪዎች አሏቸው። በተጨማሪም ይህ ቪዲዮ ጌም አምስት የጦር ቡድኖች ያሉት ሲሆን ፣ አምስቱም የተለያየ የአጫዋት ዘይቤዎችን ይከተላሉ። ከዚህ ቀጥሎ ፋንተም (Phantom) በመባል ስለሚታወቀው ቡድን እና የቡድኑን ሙሉ አቅም እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚቻል በዝርዝር ተቀምጧል። 

ፋንተም (Phantom) አራት ዋና ዋና ችሎታዎችን ይሰጣል፦ 

  • ልዩ ችሎታ፦ AEGIS - መከላከያ ጋሻ እና ቅርብ ርቀት ላይ የሚደረጉ ውጊያዎች ላይ ጠላትን የሚበታትን ጠመንጃ።  

  • መደበኛ ችሎታ፡- Mag Barrier - ከጠላት የተተኮሱ ጥይቶችን እና የእጅ ቦምቦችን መከላከል የሚያስችል ኤሌክትሮማግኔቲካዊ መካላከያ። 

  • መደበኛ ችሎታ፡- Blitz Shield - የሜሊ ቁልፍን በመጠቀም ፣ የቅርብ ርቀት ውጊያ ላይ ጥቃት ማድረስ የሚችል ታክቲካዊ መከላከያ ጋሻ። 

  • ቋሚ ችሎታ፡- Hardened - በልዩ የጂን ህክምና ህይወትን ማደሻ። 

የፋንተም ቡድን አባላት ፣ ጥቃትን የመከላከል አቅም እና ተጨማሪ ህይወት እንዲኖራቸው ተደርገው ዲዛይን የተደረጉ ሲሆን ፣ የቅርብ እና የርቀት ውጊያዎች ላይ እንደ TAC-50 ስናይፐር ወይም ጠመንጃ (Shotgun) ያሉ መሳሪያዎችን የመጠቀም ብቃታቸው ከፍተኛ ነው። እንዲሁም በክፍያ ሊከፈቱ የሚችሉ ሶስት ልዩ ገፀ-ባህሪዎችም አሏቸው። 

ድልን ለመቀዳጀት ይችሉ ዘንድ የሚያደርጓቸውን ውጊያዎች የሚመጥኑ የጦር መሳሪያዎችን እና አባሪዎች መምረጥ ወሳኘ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፡- 

ለረጅም ርቀት ውጊያዎች፡- TAC-50 ስናይፐር ከማነጣጠሪያ እና ድምጽ ማፈኛ አባሪዎቹ ጋር ፣ ከርቀት ጠላትን ላይ ያልተዛነፈ እርምጃ ለመውሰድ ተመራጭ ነው። 

ለቅርብ ርቀት ውጊያዎች፡- ባለ አጭር አፈ-ሙዝ እና ለአያያዝ ምቹ የሆነ ሰደፍ ያለው ጠመንጃ ፣ ተልዕኮዎን በአግባቡ እንዲወጡ ይረዳዎታል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !