
ትዊች (Twitch) በተባለው ድረ-ገፅ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን መሳብ የቻለው ተወዳጅ ቪዲዮ ጌም ኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) ፣ የመጀመሪያ ወገን እይታን (first-person shooter) የሚጠቀም ጌም ሲሆን ፣ አንጋፋ ከሆኑት ፣ ኮል ኦፍ ዲውቲ እና ዋር-ዞን (Call of Duty and Warzone) ጎራ በመመደብ ጠንካራ ተፎካካሪነቱ እያሳየ ይገኛል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ፣ በዩቢ-ሶፍት ኮኔክት (Ubisoft Connect) ያለምንም ክፍያ በነፃ መጫወት ማስቻሉ ተመራጭ ያደርገዋል።
ኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) ፣ ከ18 በላይ የጦር መሳሪያ አማራጮች ያሉት ሲሆን ፣ እያንዳንዳቸውንም ተጫዋቾች እንደምርጫቸው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ልዩ አባሪዎች አሏቸው። በተጨማሪም ይህ ቪዲዮ ጌም አምስት የጦር ቡድኖች ያሉት ሲሆን ፣ አምስቱም የተለያየ የአጫዋት ዘይቤዎችን ይከተላሉ። ከዚህ ቀጥሎ ሊበርታድ (Libertad) በመባል ስለሚታወቀው ቡድን እና የቡድኑን ሙሉ አቅም እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚቻል በዝርዝር ተቀምጧል።
ሊበርታድ (Libertad) አራት ዋና ዋና ችሎታዎችን ይሰጣል፦
ልዩ ችሎታ፡- Medico Supremo - የራስዎን እና በአቅራቢያዎ የሚገኙ የቡድን አጋሮችዎን ህይወት ለማደስ ወይም ለመፈወስ የሚያገለግል የህክምና ቦርሳ።
መደበኛ ችሎታ፡- BioVida Boost - የእርስዎን እና በአቅራቢያዎ የሚገኙ የቡድን አጋሮችዎን ህይወት በፍጥነት የሚያድስ ማዕበል።
መደበኛ ችሎታ፦ El Remedio - እስኪጠፋ ወይም እስኪቆም ድረስ በአቅራቢያዎ የሚገኙ የቡድን አጋሮችዎን ህይወት የሚፈውስ ጋዝ።
ቋሚ ችሎታ፡- Espíritu de Libertad - እርስዎን እና በአቅራቢያ የሚገኙ የቡድን አጋሮችዎን ህይወት በተደጋጋሚ መፈወስ የሚያስችል የነጻነት መንፈስ (Freedom Spirit)።
የሊበርታድ ቡድን ፣ የቡድን አጋሮቻቸውን መርዳት በሚፈልጉ ተጫዋቾች ዘንድ ተመራጭ ቡድን ሲሆን ፣ ይህንን የፈውስ አቅም በብቃት ለመጠቀምም ከቡድን አጋሮችዎ አቅራቢያ መሆን ይጠበቅብዎታል። ይህን ቡድን ውጊያዎ ላይ በሚያሳትፉ ወቅት ፣ የረጅም ርቀት መሳሪያዎችን በማስወገድ ፣ እንደ AK47 ክላሽ ወይም እንደ MP5 መትረየስ ያሉ የአጭር ርቀት ውጊያ መሳሪያዎችን መጠቀም ተገቢ ነው።
ድልን ለመቀዳጀት ይችሉ ዘንድ የሚያደርጓቸውን ውጊያዎች የሚመጥኑ የጦር መሳሪያዎችን እና አባሪዎች መምረጥ ወሳኘ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፡-
AK47 ክላሽ፡- ለተሻለ ዒላማ ሆሎግራፊክ ማነሻጠሪያዎች እና የመሳሪያ እርግጫን መቆጣጠሪያ ሰደፍ አባሪዎችን መጠቀም።
MP5 መትረየስ፡- ብዙ ቀልሃ ጎራሽ ካርታ እና ድምጽ ማፈኛ አባሪዎችን በመጠቀም በቅርብ ርቀት ውጊያ ላይ ውጤታማ መሆን ይቻላል።