
ኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) የመጀመሪያ ወገን እይታን (first-person shooter) የሚጠቀም ጌም ሲሆን ፣ አንጋፋ ከሆኑት ፣ ኮል ኦፍ ዲውቲ እና ዋር-ዞን (Call of Duty and Warzone) ጎራ በመመደብ ጠንካራ ተፎካካሪነቱ እያሳየ የሚገኝ ቪዲዮ ጌም ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ፣ በዩቢ-ሶፍት ኮኔክት (Ubisoft Connect) ያለምንም ክፍያ በነፃ መጫወት ማስቻሉ ተመራጭ ያደርገዋል።
ኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) ፣ ከ18 በላይ የጦር መሳሪያ አማራጮች ያሉት ሲሆን ፣ እያንዳንዳቸውንም ተጫዋቾች እንደምርጫቸው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ልዩ አባሪዎች አሏቸው። በተጨማሪም ይህ ቪዲዮ ጌም አምስት የጦር ቡድኖች ያሉት ሲሆን ፣ አምስቱም የተለያየ የአጫዋት ዘይቤዎችን ይከተላሉ። ከዚህ ቀጥሎ ዴድ-ሴክ (DedSec) በመባል ስለሚታወቀው ቡድን እና የቡድኑን ሙሉ አቅም እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚቻል በዝርዝር ተቀምጧል።
ዴድ-ሴክ (DedSec) አራት ዋና ዋና ችሎታዎችን ይሰጣል፦
ልዩ ችሎታ፡- Lockout - ጠላቶች ልዩ ችሎታቸውን መጠቀም እንዳይችሉ መቆለፍ የሚያስችል።
መደበኛ ችሎታ፦ Hijack - የጠላት ችሎታዎችን መንጠቅ እና መልሶ ራሳቸው ላይ መተግበር የሚያስችል።
መደበኛ ችሎታ፦ Spiderbot - በአቅራቢያ የሚገኙ የጠላቶች ፊት ነዳፊ ሸረሪቶችን መላኪያ።
ቋሚ ችሎታ፡- Fabricator - የሚጠቀሙት መሳሪያ አገልገሎቱን ሲጨርስ አውቶማቲካሊ ራሱን እንዲተካ ማድረጊያ።
የዴድ-ሳክ (DedSec) ቡድኖች ፣ ሌሎች ኤችሎን (Echelon) ወይም ፋንተም (Phantom) ከሚባሉ ቡድኖች አንፃር ለመቆጣጠር ትንሽ ከበድ የሚሉ ሲሆን ፣ ልዩ ብቃት ስለሌላቸው ፣ ተጫዋቾች ማንኛውንም መሳሪያዎች እና ስልቶች መጠቀም ያስችላቸዋል። ሌሎች ቡድኖች የረጅም እና የቅርብ ርቀት ውጊያዎች ላይ የተሻሉ በመሆናቸው ፣ እንደ M4A1 ፣ AK-47 ፣ ACR 6.8 ክላሾችን መጠቀም ይመከራል። እንዲሁም ገፀ-ባህሪዎችን ማስተካከል የሚያስችል አማራጮች አላቸው።
ድልን ለመቀዳጀት ይችሉ ዘንድ የሚያደርጓቸውን ውጊያዎች የሚመጥኑ የጦር መሳሪያዎችን እና አባሪዎች መምረጥ ወሳኘ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፡-
M4A1 ጠመንጃ፡- ለተሻለ ዒላማ ባለጨረር ማነጣጠሪያ እና ለአያያዝ ምቹ የሆነ የእርግጫ መቆጣጠሪያ ሰደፍ አባሪዎችን መጠቀም።
AK-47 ክላሽ፡- ብዙ ቀልሃ ጎራሽ ካርታ እና እርግጫን መቆጣጠሪያ ሰደፍ መጠቀም።
አስጨናቂ ውጊያዎች ላይ ጠላቶችንን ድል ለመንሳት እነዚህን ነጥቦች መጠቀም እና መለማመድ የሚያስፈልግ ሲሆን ፣ ማንኛውም የጌም መድረክ ላይ የሚገኙ ጓደኞችዎ ጋር በመሆን ልምድዎን ማካበት እና ድልን መቀዳጀት ይችላሉ።