icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት ምዕራፍ 5 ክፍል 3 ላይ የሚገኙ ሁሉም ሳምንታዊ ተልዕኮዎች ዝርዝር 

አዲሱ ፎርትናይት ምዕራፍ 5 ክፍል 3 አዲስ የመኪና ማሻሻያዎችን እና አዳዲስ ሜዳሊያዎችን ከሶስት የጠላት መሪዎች ጋር ይዞ መጥቷል። የሁሉም አዲስ ምዕራፎች ጅማሬ ኤክስፒን (XP) ማግኘት የሚችሉባቸው አዲስ የውጊያ ማለፊያዎች እና ሳምንታዊ ተልዕኮዎችን የሚያካተት ይሆናል። 

ፎርትናይት በአዲሱ ምዕራፍ ፣ የምዕራፍ 1 መዳረሻ ቦታዎችን ፣ የጦር መሳሪያዎችን እና ትውስታዎችን በመተው እና አዳዲስ ነገሮችን በማካተት ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል። የተሻሻሉ ካርታዎች ፣ የጦር መሣሪያዎች ስብስብ ፣ አስጨናቂ የጠላት መሪዎች እና የመሳሰሉት በዚህ ምዕራፍ ተካተዋል። የዚህን ምዕራፍ ሳምንታዊ ተልዕኮዎች እንዳያመልጥዎት መከታተልዎን አይዘንጉ! 

ኤክስፒን (XP) ለማግኘት እና ከውጊያ ማለፊያዎ ሽልማቶችን ለማግኘት ሳምንታዊ ተልዕኮዎች ላይ መሳተፍ ይኖርብዎታል። እነዚህ ተልዕኮዎች ብዙውን ጊዜ ቀላል እና በአንድ ቀን ውስጥ ሊጠናቀቁ የሚችሉ ቢሆኑም ፣ የተወሰኑት ትንሽ ተጨማሪ ጊዜን ሊወስዱ ይችላሉ። 

ሁሉንም በተልዕኮዎች ዝርዝር ገጽ ላይ በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ፣ ይህ ገጽ ሂደትዎን ለመከታተል እና ሳምንታዊ ተልዕኮዎችን በማጠናቀቅ የጦርነት ማለፊያዎን በፍጥነት እንዲያሳድጉ ይረዳዎታል። 

የሳምንት 0 ተልዕኮዎች 

  • የተሽከርካሪዎን ነዳጅ መሙላት ወይም ሙሉ በሙሉ ማስጠገን 

  • ጠላቶች ላይ የፈንጂ ጥቃት ማድረስ 

  • ሬድላይን ሪግን (Redline Rig) ፣ ብሩታል ቢችሄድን (Brutal Beachhead) እና ናይትሮድሮምን Ntridromeን መጎብኘት 

  • ተሽከርካሪ ውስጥ ሆነው ነገሮችን ማውደም 

  • በከፍተኛ ፍጥነት (Speed Boost) የተወሰነ ርቀት መጓዝ 

የሳምንት 1 ተልዕኮዎች 

(በቅርብ ቀን) 

ፎርትናይት በምዕራፍ 5 ክፍል 3 ላይ አስደናቂ አዳዲስ አማራጮች ማካተቱን እና ከፎል-አውት (Fallout) ጋር አብሮ መስራት መጅመሩን ተከትሎ ፥ ከዚህ ጋር ግንኙነት ያላቸው ልዩ ተልዕኮዎች የሚካተቱ ይሆናል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !