
ይህ መመሪያ በፎርትናይት ምዕራፍ 5 ክፍል 3 ላይ ሊያገኙዋቸው ስለሚችሏቸው አዳዲስ ልዩ ኃያል መሳሪያዎች የሚዳሰስ ሲሆን ፣ የድሮው ምዕራፍ ላይ የነበሩ የተወሰኑ የጦር መሳሪያዎች የተቀነሱ ቢሆንም ከድሮዎቹ በእጥፉ የተሻሉ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች እንዲካተቱ ተደርጓል።
አዲስ የተካተቱ ኃያል የጦር መሳሪያዎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡-
ናይትሮ ጓንቶች (Nitro Gauntlets)
እነዚህ የቡጢ ጓንቶች ለቅርብ ፍልሚያ ተመራጪ እና ሶስት የቡጢ ዓይነትቶችንም ይሰጣሉ። ከስር ወደ ላይ የሚሰነዘር (Uppercut) እና የጠላቶችን አገጭ መስበር የሚያስችል ቡጢ እና የጠላትን ድምጥማጥ ማጥፋት የሚያስችል የዝላይ ቡጢ ማድረግ ያስችላሉ! እነዚህ የቡጢ ጓንቶች በተከታታይ አራት ጊዜ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቢሆንም መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ግን የተወሰነ ጊዜን ይወስዳሉ።
ፈንጂ ወርዋሪ ቀስት (Detonating Crossbow)
ይህ ቀስት እጅግ ፈጣን ተወርዋሪ ፈንጂዎችን በመተኮስ መንገድዎን የዘጉ መኪናዎችን ማስለቀቅ የሚያስችልዎ ሲሆን ፥ በጥቂት ተኩስ ብቻ መኪናዎችን ወደ አመድነት በመቀየር የተዘጋብዎትን መንገድ ማስከፈት ያስችሎታል።
ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ኃያል የጦር መሳሪያዎችን የራስዎ ለማድረግ ጠላቶች ላይ ጥቃት መጣል እና መንጠቅ ይጠበቅብዎታል፡-
የማሺኒስት ጠመንጃ (Machinist’s Combat Assault Rifle)
ይህንን ኃያል የቅርብ ርቀት ጠመንጃ ለማግኘት ማሺኒስቷን ሬድላይን ሪግ ላይ ወይም በኮንቮይ (Redline Rig or a convoy) ወቅት በማጥቃት ይህን ኃያል የጦር መሳሪያ መንጠቅ እና የራስዎ ማድረግ ይችላሉ።
የቀለበቷ ንግሥት ፈንጂ ወርዋሪ ቀስት (Queen of the Ring's Detonating Crossbow)
የቀለበቷን ንግሥት ስካርን (Scarr) ናይትሮድሮም ላይ ወይም በኮንቮይ ወቅት በማጥቃት ይህን ሁከት ፈጣሪ እና ኃያል የጦር መሳሪያ መንጠቅ እና የራስዎ ማድረግ ይችላሉ።
የሜጋሎ ዶን ናይትሮ ጓንት (Megalo don’s Nitro Gauntlets)
ሜጋሎ ዶን ከመደበኛ ናይትሮ ጓንቶች የተለዩ ጓንቶችን የሚጠቀም ሲሆን እሱን በማጥቃት ይህን ኃያል የጦር መሳሪያ መንጠቅ እና የራስዎ ማድረግ ይችላሉ።
አዲስ የተካተቱ ህይወት ማደሻዎች
ኑካ ኮላ (Nuka-Cola)
ይህ የድህረ-ምጽአተ ዓለም ይዘት ያለው ህይወት ማደሻ ፣ ህይወትዎን እና ጋሻዎን ቀስ በቀስ ማደስ የሚያስችል ግብዓት ሲሆን ፣ በጦርነቱ ወቅት ህይወትዎን ሊያድንልዎ ይችላል።
ፈዋሹ ቁልቋል (Refreshing cactus)
እነዚህን ቁልቋሎች በፒካክዎ በመምታት እራስዎን እና በአቅራቢዎ የሚገኙ ሰዎችን መፈወስ ያስችሎታል። በተጨማሪም ከመኪናዎ ሳይወርዱ እነዚህን ቁልቋሎችን በመኪናዎ በመግጨት የእራስዎን እና የመኪናዎን ህይወት ማደስ ይችላሉ!