
በዚህ ወር ፎርቲናይት (Fortnite) አዲስ ስሪቱን (29.40 ) በዚህ ወር ያወጣ ሲሆን ፥ በውስጡም መለዋወጫወችን ፣ ተጨማሪ መዳረሻዎችን እና አዳዲስ መሳሪያዎችን አካቷል። እንደተለመደው ሁሌ ወርሃ ግንቦት የስታር ዋርስ (Star Wars) ይዘቶች ወደ ፎርቲናይት የሚመጡበት ወር መሆኑ ይታወቃል ፥ በአሁኑ ዙር እንደ E-11 ጠበንጃ እና ተወዳጁን የዳርት ቫደር የጨረር ጎራዴ እንዲመለሱ የተደረጉ ሲሆን ፥ ይህ ዓመት ይህን አጋርነት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ አማራጮች የሚቀርቡበት ዓመትም ነው።
ይሄ ብቻ አይደለም! ልዩ የስታር ዋርስ ውድድሮችም የተዘጋጁ ሲሆን ፣ ከውደድሮቹ አንዱ አዲሱን ውኪ ባለጨረር ቀስት (Wookiee laser crossbow) ማግኘት እና መጠቀምን ይጠይቃል ፣ እንዳያስቡ! ከዚህ ቀጥሎ እንዴት መሳሪያውን እንደሚያገኙ እንጠቁሞታለን።
ውኪ ባለጨረር ቀስትን (Wookiee laser crossbow) ማግኘት የሚችሉባቸው ሁለት መንገዶች ያሉ ሲሆን፦
የመጀመሪያው በጠላት ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ቺውቤካን (Chewbacca) ማዳን ሲሆን ፥ ካርታውንም በመጠቀም በጠላት ምሽግ ውስጥ ተደብቆ የሚገኘውን ውኪ ባለጨረር ቀስትን ማግኘት ይችላሉ።
ሁለተኛው መንገድ በተለያዩ የጠላት ምሽጎች ውስጥ የተቀመጡ የጠላት ካዝናዎችን በመበርበር ፣ ውኪ ባለጨረር ቀስትን በእጅዎ ማስገባት ይችላሉ። ይህ ከባድ መሳሪያ ትልቅ ውድመትን የሚያስከትል የጨረር ፈንጂን መተኮስ ያስችሎታል።
ይህንን ቀስት የማግኘት አስፈላጊነቱ ውድድሩን ለማጠናቀቅ እና ይህንን ከባድ መሳሪያ በመጠቀም ጠላቶችን ለማንበርከክ እጅጉን ስለሚጠቅምዎ ነው።
ይህንን ወሳኝ መሣሪያ በእጅዎ ለማስገባት በእነዚህ ሦስት ካምፖች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሳጥኖችን መበርበር የሚጠበቅብዎ ሲሆን ፥ ሌላኛው መንገድ ደግሞ ይህንን መሳሪያ የሚጠቀሙ ጠላቶችን በማስወገድ እና መሳሪያቸውን በመንጠቅ የራስዎ ማድረግም ይችላሉ። እነዚህ ቀስቶች ሌሎች የስታር ዋርስ ተልዕኮዎችን በድል ለመወጣትም አስፈላጊነታቸው ከፍ ያለ ነው።