icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት ምዕራፍ 5 ክፍል 2 ላይ የሚገኘውን E-11 ጠመንጃ (E-11 Blaster Rifle) እንዴት ማግኘት ይቻላል? 

በዚህ ወር ፎርቲናይት (Fortnite) አዲስ ስሪቱን (29.40 ) በዚህ ወር ያወጣ ሲሆን ፥ በውስጡም መለዋወጫወችን ፣ ተጨማሪ መዳረሻዎችን እና አዳዲስ መሳሪያዎችን አካቷል። እንደተለመደው ሁሌ ወርሃ ግንቦት የስታር ዋርስ (Star Wars) ይዘቶች ወደ ፎርቲናይት የሚመጡበት ወር መሆኑ ይታወቃል።  

ይሄ ብቻ አይደለም! ልዩ የስታር ዋርስ ውድድሮችም ላይ መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ፣ ከውደድሮቹ አንዱ E-11 ጠመንጃ (E-11 Blaster Rifle) ማግኘት እና መጠቀምን ይጠይቃል። እንዳያስቡ! ከዚህ ቀጥሎ እንዴት መሳሪያውን እንደሚያገኙ እንጠቁሞታለን። 

E-11 ጠመንጃ (E-11 Blaster Rifle) ማግኘት የሚችሉባቸው ሁለት መንገዶች ያሉ ሲሆን፦ 

የመጀመሪያው ስቶርም-ትሩፕርስ (Stormtrooper) የተባሉ የጠላት ዓይነቶችን በማስወገድ መሳሪያቸውን በመንጠቅ የራስዎ ማድረግ ሲሆን ፥ ሁለተኛው መንገድ ደግሞ በተለያዩ የጠላት ምሽጎች ውስጥ የተቀመጡ እና በስቶርምትሩፕርስ (Stormtrooper) ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግላቸውን የጠላት ሳጥኖችን በመበርበር E-11 ጠመንጃን (E-11 Blaster Rifle) በእጅዎ ማስገባት ይችላሉ።  

እነዚህን በጠላት ምሽጎች ውስጥ የሚገኙ ሳጥኖች የንጉሠ ነገሥቱ አርማ ስለታተመባቸው በቀላሉ መለየት እና ማግኘት ይችላሉ። ያስታውሱ! እነዚህ ሳጥኖች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ሀብቶችን በውስጣቸው በመያዛቸው ፥ ፈላጊያቸው ብዙ ነው! ስለዚህ በጥንቃቄ በመንቀሳቀስ ከሌሎች ባላንጣዎች ጥቃት ራስዎን ይጠብቁ። 

በእነዚህ ምሽጎች ውስጥ በርካታ የሚዘረፉ ሳጥኖች የሚገኙ በመሆኑ እያንዳንዱን በመበርበር መሳሪያውን የግልዎ ማድረግ ይችላሉ። በተጨማሪም ፣ መሣሪያውን የያዙ ጠላቶች ሲያጋጥምዎም እርመጃ በመውሰድ መንጠቅም ይችላሉ። ይህ ጠበንጃ የንጉሠ-ነገስት መሳሪያ የሚጠቀሙ ጠላቶችን ማጥቃትን እና ስቶርምትሩፕርስን (Stormtrooper) በማስወገድ E-11 ጠመንጃቸውን (E-11 Blaster Rifle) መንጠቅን የሚጠይቁ የስታር ዋርስ ተልዕኮዎችን በድል ለመወጣት አስፈላጊ ናቸው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !