
ፎርትናይት (Fortnite) ያለማቋረጥ ለተጫዋቾቹ ትኩስ ይዘቶችን ማቅረቡን እና ማስደሰቱን ቀጥሏል። የፎርትናይት (Fortnite) ምዕራፍ 5 ክፍል 2 መቋጫ በመቃረቡ ፣ አዘጋጆቹ 3ተኛውን ምዕራፍ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን አነስ ባለ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማቸው ፍንጭ ሰተዋል!
ኦለምፐስ ተራራ ላይ የሚገኘው ሐውልት ኢፒክ ጌምስ ለአዲሱ ምዕራፍ አስደናቂ ነገሮችን እያዘጋጀ ስለመሆኑም ፍንጭ ሰጥቷል። ስለ መጪው መጪው ምዕራፍ 5 ክፍል 3 ማወቅ ያለብዎትን ነገሮች እንደሚከተለው አስቀምጠናል።
ምዕራፍ 3 የጅመላ ውጊያ (battle royale) ላይ መጠነ ሰፊ ለውጦችን ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። ስለሚለቀቅበት ቀን እስካሁን በይፋ አዘጋጆቹ ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም ፣ በቅርቡ እንደሚሆን ግን ይጠበቃል! ልክ እንደ ምዕራፍ 2 ተጫዋቾች የጦር ሜዳ ውግያዎች ላይ በመሳተፍ የዚህ ክስተት ተሳታፊ መሆን ይችላሉ።
በፎርትናይት ጦር ሜዳዎች ላይ በርካታ እንግዳ ክስተቶች የተስተዋሉ ሲሆን ፣ ግንቦት 13 ላይ በኦለምፐስ ተራራ ላይ የሚገኘው ባለ ትልቅ ክንፍ ሐውልት ላይ ጥቅጥቅ ደመና እና አስደንጋጭ የመብረቅ ብልጭታዎችን ተከትሎ የሐውልቱ ዓይኖቹ ሲያብረቀርቁ ታይተዋል። ይሄ ብቻ አይደለም! ይህ ክስተት በታየበት ማግስት ግንቦት 14 ፣ ለማመን በሚከብድ ሁኔታ ሐውልቱ ከተተከለበት በመንቀሳቀስ ድበቁን የፓንዶራ ሳጥን ሲከፍት ታይቷል! ይህም ፎርትናይት (Fortnite) በመጪዎቹ ቀናት አፍ የሚያስከፍቱ አስደናቂ ነገሮችን ይዞ እንደሚመጣ ማረጋገጫ ነው።
ምዕራፍ 3 ለጅመላ ውጊያዎች አዳዲስ ነገሮችን ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ፥ አዲስ በረሃማ አካባቢዎችን እና የፎርትናይት ደሴት ሙሉ ለሙሉ ሊቀየር እንደሚችል ቀድሞ የተለቀቀው የምጽዓት ዘመን ገፅታው ይጠቁማል። በተጨማሪም ፣ ከሜታሊካ እና ከፓይሬትስ ኦፍ ዘ ካሪቢያን ጋር ያደረገው ሽርክና አዲስ ተልዕኮዎች እና ሽልማቶችን ለማካተት ያስችለዋል።
አዲስ የሚካተቱት አካባቢዎች እና የመጓጓዣ አማራጮች ነባሩን የመዋጊያ እና ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀሻ መንገዶች በከፍተኛ ሁኔታ ሊለውጡ ይችላሉ። በተጨማሪም የፎል ጋይስ ገፀ-ባህሪያት (Fall Guys) መካተት እና አዳዲስ አኒሜሽኖች ጌሙ አዲስ እና አስደሳች ስሜት መፍጠር የሚያስችሉ ናቸው።