
በቅርብ የተለቀቀው የሄል-ዳይቨርስ 2 አዲስ ስሪት ፥ የጦር መሳሪያዎች ፣ ጠላቶች እና ተልዕኮዎች ላይ ብዙ ማስተካከያዎች ያደረገ ሲሆን ፥ ጋላቲክ ዲሞክራቶች ፣ እነዚህን ለውጦች በአግባቡ መረዳት ቀጣይ ለሚያደርጓቸው ወረራዎች ስልታዊ ዕቅድ መንደፍ ያስችላቸዋል።
በዚህ ዝማኔ ውስጥ የጨዋታ ተሞክሮዎን የበለጠ አስደሳች የሚያደርጉ ለውጦችን ፣ የአጨዋወት ማሻሻያዎችን እና ወሳኝ እርማቶች ተካተዋል።
የሄል-ዳይቨርስ 2 ፣ 01.000.300 ስሪት የተለያዩ ማሻሻያዎችን የሚያካተት ሲሆን ፥ ጌሙን ሚዛናዊ እና ቀለል ለማድረግ አንዳንድ የጦር መሣሪያዎች ላይ እና የቃጠሎ ጕዳት መጠን ላይ ቅነሳ ተደርጓል።
ቁልፍ ከሆኑ ማሻሻያዎች መካከል፡-
መሳሪያዎች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች
የመሳሪያ መከላከያ ትጥቅ፡- ከ100 በላይ ደረጃ ያለው መከላከያ ትጥቅ በዚህ ስሪት ከአንገት በላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መከላከል ያስችላል።
የድል አከባበር፦ ከተልዕኮ በኋላ በተሳካ ሁኔታ ተልዕኳቸውን የተወጡ ተጫዋቾች ብቻ ድላቸውን በማስመልከት መፎከር የሚችሉ ይሆናል።
ፈንጂ ወርዋሪ ቀስት (CB-9 Exploding Crossbow)፡- የፍንዳታ መጠኑ እንዲቀነስ ተደርጓል።
LAS-99 Quasar Cannon፡- በተኩስ መካከል መልሶ የመቀባበያ ቆይታው እንዲረዝም ተደርጓል።
BR-14 Adjudicator፡- የጠመንጃውን ምላስ ደጋግሞ መጫን ሳያስፈልግ በራስ-ሰር (Automatically) መተኮስ እንዲያስችል ተደርጓል።
ስትራታጀሞችም (Stratagems)፦ ላይ ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን ፥ የ(A/MG-43) ማሽን ጋን ሳንተሪ እና የ(A/ARC-3) ቴስላ ታወር በጦርነት ወቅት ጥቃትን የመቋቋም አቅማቸው ተጨምሯል።
ጠላቶች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች
ባይል ስፒወርስ (Bile Spewers)፡- የእነዚህ የጠላት ዓይነቶች ቅልጥፍናቸው እንዲገደብ የተደረገ ሲሆን ፥ ይህም በቀላሉ ኢላማ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።
ስኮርቸር ኸልክ (Scorcher Hulks)፡ እነዚህ የጠላት ዓይነቶች በተጫዋቾች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት በ20% ተቀንሷል።
ተልዕኮዎች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች
ካርታ፦ ካርታ ላይ የግብ ስርጭቶችን ለማረጋገጥ አነስተኛ ማስተካከያዎች የተድረገ ሲሆን ይህም ተጫዋቾች በተልዕኮ ወቅት የትም ቢሆኑ ማከናወን የሚገባቸውን ተግባራት በቀላል እንዲያቁ ይረዳል።
ስፕሪድ ዲሞክራሲ (Spread Democracy)፦ ስፕሪድ ዲሞክራሲ የተባለውን ተልዕኮ ፈታኝ በሆነ ደረጃ (Higher Difficulty Level) መጫወት እንዲቻል ተደርጓል።