
ኤክስ-ዲፋየንት (XDefiant) ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ተጫዋቾች ከጓደኞቻቸው ወይም ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር ፈጣን ግጥሚያዎችን ማድረግ እንዲችሉ አስችሏል። የማሸነፍ እድልዎን መጨመር ይችሉ ዘንድም ፣ የጌም ቅንብሮችዎን ማስተካከል ይኖርብዎታል። ማስተካከል የሚኖርብዎን ቅንጅቶች እንደ አጫዋወት ልምድዎ ሊለያይ ቢችልም ፣ የሚከተሉትን ቢያስተካከሉ ይመከራል።
አጨዋወት እና በይነ-ገጽ፡
ዕይታ Field of View (FOV)፦ እንደ ምርጫዎ ከ90 እስከ 120 ያድርጉ።
ኤ.ዲ.ኤስ ዕይታ (ADS Field of View)፡- አፌክትድ
የስክሪን ሁኔታ (Display Mode)፦ ሙሉ ስክሪን
የስክሪን ጥራት (Display Resolution)፡- ኔቲቭ (ከስክሪንዎ ጥራት ጋር የሚመጣጠን)
የምስል ዥረትን የማደስ መጠን (Refresh Rate)፡- የስክሪንዎ የሚቀበለውን ከፍተኛ መጠን
ሞኒተር (Monitor)፡- ዋና ሞኒተር
አነስተኛ ፍጥነት (Reduced Latency)፡- ለፍጥነት ፣ ይህን ያብሩ
ንቪዲያ አነስተኛ ፍጥነት (NVIDIA Reflex Low Latency)፡- ለፍጥነት ፣ ይህን ያብሩ
የብርሃን መጠን (Brightness)፦ 15
ግልጽ ምስል (Contrast)፡- 15
ዲኤክስ 12 ሬንደሪንግ (DX 12 Rendering)፡- ያብሩ
ኤች.ዲ.አር (HDR)፡- ያብሩ
የግራፊክ ጥራት (Graphics Quality)፡- እንደምርጫዎ
ቪ-ሲንክ (V-Sync Mode)፡- ያጥፉ
የፍሬም መጠን በሰክንድ (Frame Rate Limit (FPS)፡- ያብሩ እና ፣ ከፍተኛውን መጠን ያድርጉ
የጥላዎች ጥራት መጠን (Shadow Quality)፡- ዝቅተኛ
ጥላማ ቦታዎች (Spot Shadows)፦ ዝቅተኛ
የጥላማ ቦታዎች ጥራት (Spot Shadow Resolution)፡- ዝቅተኛ
በንክኪ የሚፈጠሩ ጥላዎች (Contact Shadows)፦ ያጥፉ
የጥራት መጠን (Resolution Scale)፡ 85%
የምስል ድምቀት (Sharpening)፡ 10
የንድፎች ጥራት (Particle Details)፦ ዝቅተኛ
የጭጋግ ይዘታዊ መጠን (Volumetric Fog)፡- ዝቅተኛ
የግሎባል ነፀብራቅ ጥራት መጠን (Global Reflection Quality)፡- ዝቅተኛ
የሎካል ነፀብራቅ ጥራት መጠን (Local Reflection Quality)፡- ያጥፉ
የቬጂቴሽን ጥራት (Vegetation Quality)፦ ዝቅተኛ
አላፊ ነፀብራቆች (Subsurface Scattering)፡- ያብሩ
የብርሃን ግርዶሽ (Ambient Occlusion)፡- ዝቅተኛ
የነገሮች ምስል ጥራት (Object Details)፡- 50
የምስል ዥረት ጥራት (Enhanced Streaming Distance)፡ 5
የሌንስ ጨረሮች (Lens Flare)፡- ያጥፉ
የውሃማ ቦታዎች ጥራት (Water Quality)፦ ዝቅተኛ
አባሪ ከለሮች (Chromatic Aberration)፡- ያጥፉ
የቅርፆች ጥራት (Terrain Quality)፡- መካከለኛ
እነዚህ ማስተካከያዎች በዋነኛነት ለኮምፒውተር (PC) ተጫዋቾች የሚመከሩ ቢሆንም ፣ እንደ ምርጫቸው ሊያስተካክሏቸው ግን ይችላሉ። ይህም ሆኖ አልፎ አልፎ ፣ ግጥሚያዎችን ለማግኘት መቸገር ወይም ተዛማጅ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ሊያውቁ ይገባል።