
ግንቦት 24 ፎርትናይት ምዕራፍ 5 ክፍል 3 ከተለቀቀ በኋላ ብዙ ተጫዋቾች የተሽከርካሪዎች ከመጠን ያለፈ ጉልበት ተገቢ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ይህንንም አስመልክቶም ኢፒክ ጌምስ የተጨዋቾችን ፍላጎት ለማሟላት እና ጨዋታውን ለማመጣጠን ግንቦት 30 ማስተካከያዎችን አድርጓል።
ተሽከርካሪዎች ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎች (ግንቦት 30 ፣ አ.ኤ.አ 2024 ዝማኔ)
የተጫዋቾችን አስተያየት ተከትሎ ፣ ኢፒክ ጌምስ በፎርትናይት የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ላይ ያደረጋቸው ለውጦች ዝርዝር፡-
የተሽከርካሪ አቅም፡- የተሸከርካሪዎች ጉዳትን የመቋቋም አቅም የተቀነሰ ሲሆን ፣ ይህም በተለይ ለብቻ ጨዋታ ወቅት በቀላሉ እንዲጎዱ የሚያደርግ ይሆናል።
ተሽከርካሪ ላይ ተሰኪ መትረየሶች፡- የመትረየሶች አቅመም የተቀነሰ ሲሆን ፣ ናይትሮን በመጠቀም የመተኮስ ፍጥነታቸው ከ1.5x ወደ 1.25x ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
የናይትሮ ጓንቶች ዳግም የማቀባበያ ቆይታ፡- የዚህን ጓንት ዳግም የማቀባበያ ጊዜ በ3 ሰከንድ ተራዝሟል።
የጨረር ፈንጂዎች፡- ይህ መሳሪያ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከ3.0x ወደ 3.7x ከፍ እንዲል ተደርጓል።
ናይትሮ ባሽ እና ተሰኪ ፈንጂ ወርዋሪዎች፡- የናይትሮ ባሽ የጉዳት መጠን ከ75 ወደ 25 የተቀነሰ ሲሆን ፣ ተሰኪ ፈንጂ ወርዋሪዎችም ህንፃዎች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከ250 ወደ 150 ተቀንሷል።
በመዘጋጀት ላይ የሚገኙ አዳዲስ ማሻሻያዎች እና የጦር መሳሪያዎች
ከተሽከርካሪ ማስተካከያዎች በተጨማሪ ዳታማይነሮች በመዘጋጀት ላይ ያለ አዲስ መሳሪያ ያገኙ ሲሆን ፣ ይህም መሳሪያ የማይበገሩ የሚባሉ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚያስችል ከባድ መሳሪያ ነው። ምንም እንኳን አንዳንድ ድምፆች የጠፉ ቢሆንም ፣ ይህ መሳሪያ በቅርብ ጊዜ የሚካተት ይሆናል።
ሽርክናዎ እና በቅርቡ የሚካተቱ ይዘቶች
ፎርትናይት በምዕራፍ 5 ክፍል 3 አንጋፋ ከሆኑት ፣ ፎልአውት (Fallout) እና ማርቭል (Marvel) ጋር ሽርክናን ፈጥሯል። በተጨማሪም ከሌታል ኩባንያ ጋር የሽርክና ሂደትን መጀመሩ ተሰምቷል። ዳታሚነሮች የሌታል ኩባንያ ስብስቦችን የሚያመለክቱ ገፀ-ባህሪያት ፣ የገፀ-ባህሪያን ልዩ እንቅስቃሴዎች (Emote) ፣ ፒካክሶችን (Pickaxe) ፣ እና ታዛይ መሳሪያዎችን (Back Bling) አግኝተዋል።