
“አንብራይድልድ” "Unbridled" በመባል የሚጠራው ፣ የፎርትናይት 5ኛ ምዕራፍ 3ኛ ክፍል ፣ አዳዲስ ይዘቶችን እና የተሽከርካሪ ማስተካከያዎችን እና መጠገኛ አማራጮችን ይዞ የመጣ ሲሆን ፣ ይህም ተጫዋቾች ተሽከርካሪዎቻቸው የምድረ-በዳውን አስቸጋሪ ፣ ወጣ ገባ ቦታዎችን እና ሁኔታዎችን መቋቋም እንዲችሉ የተለያዩ ማሻሻያዎችን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
የተሽከርካሪ ማሻሻያዎች
ሮክ ራም (Rock Ram)፡- በተሽከርካሪዎ ፊት የሚገጠም ሲሆን ፣ በግጭት ወቅት ጉዳትን የሚቀንስ እና የተሽከርካሪውን ጥንካሬ የሚጨምር ነው።
ሁለገብ ጎማዎች (All-Terrain Tires)፡- እነዚህ የተሻሻሉ ጠንካራ ጎማዎች አስቸጋሪ እና ወጣ ገባ ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎን ያለ ምንም እክል እንዲነዱ ያስችሎታል።
ከመደበኛ ማሻሻያዎች በተጨማሪ አራት አዳዲስ አማራጮች ተካተዋል፡-
ተሰኪ መትረየስ (Machine Gun Turret)፡- ተሽከርካሪዎ ጣሪያ ላይ ተገጥሞ ፣ ከተሽከርካሪዎ ሳይወርዱ መተኮስ ያስችልዎታል።
ተሰኪ ፈንጂ ወርዋሪ (Grenade Launcher Turret)፡- ይህ ከባድ መሳሪያ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ፈንጅዎችን መተኮስ እና ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ያስችልዎታል።
ተለጣፊ ፈረፋንጎ (Spiked Bumper)፡- ነገሮችን ወይም ተጫዋቾች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ተሽከርካሪዎ ፊት የሚገጠም መሳሪያ።
ጥይት የማይበሳቸው ጎማዎች (Bulletproof Tires)፡- በውጊያ ወቅት ጥይትን እና ፍንዳታን መቋቋም የሚችሉ እና በቀላሉ የማይፈነዱ ጠንካራ ጎማዎች።
የማሻሻያ ሳጥኖች በደሴቱ ዙሪያ ተበታትነው የሚገኙ ሲሆን ፣ በፍጥነት ተሽከርካሪዎን ማሻሻል ያስችሎታል። እነዚህን ማሻሻያዎች ለመጠቀም እነዚህም ሂደቶች ይከተሉ፡-
ተሽከርካሪዎን ቀጥታ ወደ ማሻሻያ ሳጥኑ ይንዱ።
ማሻሻያ ሳጥኑ ላይ በተቀመጠው ምልክት መሰረት ምነም ማድረግ ሳይጠበቅዎ አውቶማቲካሊ ተሽከርካሪዎ ይሻሻላል።
ቀድሞ በነበረ ማሻሻያ መተካት ወይም ተሽከርካሪዎን ወደ ነበረበት መመለስ ይችላሉ።
ተሽከርካሪዎ ሲጎዳ የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም መጠገን ይችላሉ፡-
የጥገና ሳጥን፡- ተሽከርካሪዎን ሙሉ ለሙሉ ለመጠገን ፣ ቀጥታ ወደ ማሻሻያ ሳጥኑ መንዳት።
መጠገኛ መሳሪያ፡- ይህን ግብዓት የፈነዳ ጎማዎን ፣ የተሰበሩ መስኮቶችዎን ለመጠገን እና የተሸከርካሪዎን ጉዳት ነጥብ ለመመለስ ሊጠቀሙት ይችላሉ።
የነዳጅ ማደያዎችም የተሻሻሉ ሲሆን ነባር የነዳጅ ፓምፖችን በማስቀረት ፣ በቀላሉ የተዘጋጁ ቦታዎች ላይ በመቆም ብቻ የተሽከርካሪዎን ነዳጅ መሙላት እና መጠገን እንዲችሉ ተደርጓል።