icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የፎርትናይት ምዕራፍ 5፣ ክፍል 3 የውጊያ ማለፊያ ዝርዝር መረጃዎች እና ትንበያዎች 

መረጃ እና ትንበያዎች  

ኢፒክ ጌምስ የምተ-ዓለም ገጽታ ይዘት ያለውን ምስል በቅርቡ በማጋራት ፣ የፎርትናይት አዲስ ምዕራፍን ማስተዋወቅ የጀመረ ሲሆን ፣ በዚህ ምዕራፍ ፎል አውት (Fallout) ጋር እና ማድ ማክስ (Mad Max) ጋር በመቀናጀት ብዙ አስገራሚ እና አስደሳች ሽልማቶችን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምዕራፍ 5 ክፍል 2 መገባደጃ ላይ እንደመድረሳችን በፎርትናይት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ጉጉት ተፈጥሯል። 

ምዕራፍ 5 ክፍል 3 በትክክል የሚለቀቅበት ቀን በግልጽ ባይታወቅም ፣ ከትልቅ ዝመናዎች እና ዝግጅቶች በኋላ ይለቀቃል ተብሎ ይገመታል።  ሐሙስ፣ ግንቦት 23፣ 2024 እንደሚለቀቅ የሚዘዋወረው ዜና የሀሰት ዜና ቢሆንም ፣ መረጃ አሰራጮች ስለ ምዕራፍ 3 የውጊያ ማለፊያ ዝርዝር መረጃዎችን እያጋሩ ይገኛሉ። 

የአዳዲስ ገፀ-ባህሪያት ዝርዝር 

"ሬክ" ተብሎ የሚጠራው የፎርትናይት አዲስ ምዕራፍ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2024 የሚጀመር ሲሆን ፣ ይህ ምዕራፍ ፎልአውትን (Fallout) መነሻ ያደረገ የድህረ-ምጽዓተ ዓለም ጭብጥ የሚኖረውም ይሆናል። በውጊያ ማለፊያ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ተለዋዋጭ ገፀ-ባህሪዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡- 

  • ናይትሮ ካሮት (Nitro Carrot)፡- ጠንካራ እና ባለጡንቻ ፣ የካሮት ድቅል ገፀ-ባህሪ። 

  • ሬድ ሄልሜት (Red Helmet)፡- አፔክስ ሌጀንድስ ላይ ያለውን ኦክቴን የተባለ ገፀ-ባህሪ ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቀለሞች ያሸበረቀ ፣ ፈጣን ገፀ-ባህሪ። 

  • ባለሰማያዊ ፀጉሯ ልጅ (Blue Hair Girl)፡- ከተሰራጩት ምስሎች ጋር ተመሳሳይነት ያላት ገፀ-ባህሪ። 

  • ሪሚክስ ደሚ (Remix Dummy)፡- የድህረ-ምጽዓት ገጽታን የተላበሰ ፣ ነባር የኤንፒሲ (NPC) ገፀ-ባህሪ። 

  • ስከል ማስክ (Skull Mask)፡- ከተሰራጨው የስፔክትሮግራም የራስ-ቅል ምስል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ገፀ-ባህሪ። 

  • ሮቦ ማውዝ ገርል (Robo Mouse Girl)፡- ባለ ሮቦቲክ ማውዝ ሄልሜት ገፀ-ባህሪ። 

  • ሳንድ-ስቶርም (Sandstorm)፡- በቀጥታ ስርጭት ወቅት ፣ ከበረሃ አውሎ ንፋስ የወጣው ፍጥረት። 

  • ሄፍይስተስ (Hephaestus): የመጨረሻው የውጊያ ማለፊያ ገፀ-ባህሪ ሲሆን ፣ የእሳት አምላክን ይወክላል። 

  • ኢላይት አርኪ-ታይፕ (Elite Archetype)፡- ለዊንተርፌስት የተዘጋጀ ነፃ ገፀ-ባህሪ። 

የሚጠበቁ እና የተረጋገጡ ሽርክናዎች 

አዲሱ ምዕራፍ ታዋቂ እና አንጋፋ ጌሞች ጋር አጓጊ ሽርክናዎች ያደረገ ሲሆን ፣ እነሱም፡- 

  • ፎል-አውት (Fallout)፡- ተልዕኮዎች ላይ የሚገኘውን T-60 የተባለ ፣ ከባድ የጥይት መከላከያ ትጥቅ ይጨመራል ተብሎ ይጠበቃል። 

  • ፓይሬትስ ኦፍ ዘ ካሪቢያን (Pirates of the Caribbean)፡- የጃክ ስፓሮው ገፀ-ባህሪ ይካተታል ተብሎ ይጠበቃል። 

  • ሜታሊካ (Metallica)፡ ፎርትናይት ፌስቲቫል ላይ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

  • ክሎምቦ (Klombo)፡ በሌጎ ፎርትናይት (LEGO Fortnite) ሽርክናቸውን አሳውቀዋል። 

  • ማርቭል (Marvel)፡ ተጨማሪ መረጃዎች በቅርቡ የሚገለፁ ይሆናል። 

ከላይ የተዘረዘሩትን አዳዲስ ገፀ-ባህሪያት መካተት እና ፣ እንዴት በውጊያ ማለፊያ ውስጥ መጠቀም እንደሚቻል ከአዘጋጆቹ ማረጋገጫን እስከምናገኝ በጉጉት እየጠበቅን እንገኛለን። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !