icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት በአዲስ ስሪቱ (30.00) ይዞት የመጣቸው አዳዲስ አማራጮች  እና ለውጦች  

ፎርትናይት በአዲሱ ምዕራፍ 5 ክፍል 3 ተጫዋቾች ማስደነቁን የቀጠለ ሲሆን ፣ ከፎልአውት (Fallout) ጋር ያደረገውን ሽርክና ተከትሎ ፣ "ሬክድ" የተባለ ጭብጥን መሰረት ባደረገ ፍጹም አዲስ አፅናፈ-ዓለም ላይ ተጫዋቾችን እንደሚያሳትፍ ፣ በአዲሱ ስሪት መግለጫ 30.00 (Patch notes 30.00) ላይ ፣ ፍንጮች ታይተዋል። 

የፓች 30.00 ፡ ምዕራፍ 3 አጠቃላይ እይታ 

የፎርትናይት ምዕራፍ 3 "ሬክድ" በስተመጨረሻ ፈተናዎች እንደ ምድር አሸዋ ወደበዙበት በረሃ ተጫዋቾችን እየወሰደ ሲሆን ፣ ዝማኔው እንደ ጦር መሳሪያዎች ፣ ተለዋዋጭ ገፀ-ባህሪዎች እና ልዩ የጨዋታ ተሞክሮዎችን እና ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ ይመጣል። 

አዲሱ በርሃ 

የፎርትናይት ካርታ በዌስተላንድ ጋንግ ቁጥጥር ስር የሚገኝ እና በደሴቲቱ ደቡባዊ ክፍል ላይ የሚገኝ አዲስ ግዙፍ በረሃማ ቦታን አካቷል። አዳዲስ የተካተቱ አካባቢዎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፦ 

  • ሬድላይን ሪግ (Redline Rig)፡- ማሽኒስት (Machinist) በተባለ ገፀ-ባህሪ ቁጥጥር ስር የሚገኝ የናይትሮ ፋብሪካ። 

  • ናይትሮድሮም (Nitrodrome)፡- በቀለበቷ ንግስት ስካር (Scarr) የሚመራ በነውጥ የተሞላ አካባቢ። 

  • ብሩታል ቢችሄድ (Brutal Beachhead)፡ በሜጋሎ ዶን (Megalo Don) የሚመራ የበረሃ ተዋጊዎች ምሽግ። 

አዲስ ናይትሮ 

የተሽከርካሪዎን ፍጥነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምሩ እና በውጊያ ወቅት ቅልጥፍናዎን የሚጨምሩ ፣ አዲስ የናይትሮ በርሜሎች።   

አዲስ የጦር መሳሪያዎች እና ማሻሻያዎች 

ናይትሮ ጓንቶች (Nitro Gauntlets)፦ በቅርብ ርቀት ውጊያ ወቅት ለጡጢዎ ተጨማሪ ኃይል የሚሰጡ ጓንቶች። 

የተሽከርካሪ ማሻሻያዎች (Vehicle modifications)፡- የተሽከርካሪዎን ጠንካሬ እና አቅም መጨመር የሚያስችሉ ተሬትስ (Turrets) እና ሮክ ራምስ (Rock Rams)። 

የሬክድ የውጊያ ማለፊያ 

የሬክድ ውጊያ ማለፊያ ብዙ አዳዲስ ሽልማቶች ፣ የዌስትላንድ ወንበዴዎችን መሰረት ያደረጉ ገፀ-ባህሪያት እና ሌሎች የበረሃ ገጽታዎች ያሉት ሲሆን ፥ እንደ ማሽኒስት ፣ ሲንደር እና ሌሎች ገፀ-ባህሪያትንም ማስከፈት ይችላሉ። 

ፎርትናይት በአዲስ ስሪቱ (30.00) ተጨዋቾችን አዲስ ይዘት ያለውን የድህረ-ምጽዓት ዓለም ማሰስ የሚያስችል እና ሌሎች ተጨማሪ አስደሳች ነገሮችን ይዞ በመምጣት ላይ ይገኛል።  

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !