
አክቲቪዢን (Activision) ፣ ትዊተር እና ዩቲዩብ ገፃቸው ላይ አጫጭር እና ረዣዥም ቪዲዮዎችን በመልቀቅ የኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6ን (Call of Duty: Black Ops 6) ታሪክ ጭብጥ አሳይቷል። ሰኞ ፣ ሰኔ 3 ላይ በተለቀቁት የጌሙ ተጨማሪ ታሪኮች ፣ Black Ops 6 ምን ይዞ እየመጣ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል። እስካሁን ስለ አዲሱ ክፍል ያወቅናቸው ነገሮች ፣ እንደሚከተለው አስቀምጠናል፦
የታሪኩ ጭብጥ
ፍራንክ ዉድስ (Frank Woods) ዋርዞን ላይ ፣ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ሆኖ የታየ ሲሆን ፣ ይህም የBlack Ops 2 ታሪክ ጭብጥ የአዲሱ ክፍል ታሪክ ጋር ግንኙነት ሊኖረው አንደሚችል ይጠቁማል።
ብላክ ኦፕስ 6 (Black Ops 6) የታሪክ ጭብጡን በ1990 እና 1991 በተደረገው የባህረ ሰላጤ ጦርነት (Gulf War) ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ፣ ዉድስ (Woods) በገለፃው ወቅት ፣ እሱ እየተከታተለው ስለሚገኘው ሰላይ ተጫዋቾች መረጃ እንዲሰበስቡ ተልዕኮ ሲሰጥ ይታያል።
አድለር የተባለ ሰውን ፈልገው ላገኙ አዳኞች የሚሰጥ ስጦታን የሚገልጽው ፖስተር እና አድለር ተፈላጊ የመንግስት ጠላት መሆኑን የሚያሳየው ሰነድ ፥ አድለር ተፈላጊው ሰላይ መሆኑን ይጠቁማሉ።
ሰኔ 9 በሚደረገው የኤክስቦክስ (Xbox) የጌም ትርዒት ላይ እና ሰኔ 7 ላይ በሚደረገው የጌም ፌስት ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይጋራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ፣ ተጫወቾች ምን አዲስ መረጃ ሊሰጥ አንደሚችል በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
ብላክ ኦፕስ 6 (Black Ops 6) ላይ የሚጠበቁ ነገሮች
የብላክ ኦፕስ (Black Ops) ሁሉም ክፍሎች የመጀመሪያ ሰው እይታን የሚጠቀሙ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ፣ አዲሱ ብላክ ኦፕስ 6ም (Black Ops 6) ይህንኑ አካሄድ ይከተላል ተብሎ ይጠበቃል።
የተራቀቁ የቡድን ጨዋታ አማራጮች ፣ አሳታፊ የትብብር ተልዕኮዎች እና በጀብዱ የተሞሉ የግል ተልዕኮዎች የሚጠበቁ ሲሆን የግራፊክስ ጥራቱ እና የጨዋታ አካሄዶቹ እጅግ እየተሻሻሉ መሄዳቸው ፣ አዲሱ ክፍል የበለጠ አስደናቂ እና መሳጭ አቀራረብን ይዞ አንደሚመጣ ማረጋገጫዎች ናቸው።
ብላክ ኦፕስ 6 (Black Ops 6) ሲለቀቅ ፣ ለጨዋታ ማለፊያ ተመዝጋቢዎች ፒሲ (PC) ፣ ኤክስቦክስ 1 (Xbox One) እና ኤክስቦክስ ቅጥያዎች (Xbox Series X|S) ላይ የሚገኝ ይሆናል።
ቫንጋርድ (Vanguard) ላይ ታዋቂ የሆነው የዞምቢዎች የጨዋታ ሞድ የሚካተት ይሆናል።
በእነዚህ አስደሳች ዝመናዎች Black Ops 6 አስደሳች እና መሳጭ የጨዋታ ተሞክሮን ለተጨዋቾች ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።