
ስለኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 (Call of Duty: Black Ops 6) የሚናፈሱ ወሬዎች ቀስ በቀስ እየተረጋገጡ ይገኛሉ። በቅርብ ጊዜ የተሰማውም መረጃ ፣ ብላክ ኦፕስ 6 የድሮ የጌም መድረኮች ላይ እንደሚለቀቅ ይጠቁማሉ። እንደ PlayStation 5 እና Xbox Series X ያሉ የቆዩ እና በርካታ ዓመታትን ያስቆጠሩ የጌም መድረኮች ቢሆኑም አክቲቪዥን (Activision) የቆዩ የጌም መድረኮችን ፣ በተለይም PS4 እና Xbox Oneን መደገፉን ቀጥሏል።
ምንም እንኳን PS5 እና Xbox Series X እ.ኤ.አ በ2020 የተጀመሩ ቢሆንም ፣ ብላክ ኦፕስ 6 በርካታ ዓመታትን ያስቆጠሩት PS4 እና Xbox One ላይም እንደሚለቀቅ ጌም-ስቶፕ (GameStop) ባጋራቸው ምስሎች ተረጋግጧል። ይህም መረጃ ጌሙ PS4 ፣ PS5 እና Xbox Series X ላይ በቅርቡ በቅድመ-ትዕዛዝ ማግኘት አንደሚቻል አረጋግጧል።
ማረጋገጫ የመረጃ ምንጮች
የGameStop ሰራተኞች ፣ የቪዲዮ ጌም አዘጋጆች እና ፣ በርካታ ምንጮች ይህን መረጃ ያረጋገጡ ሲሆን ፣ በInsider Gaming መሰረት ፣ ተመሳሳይ የጌም ግብዓቶችን ጥቅም ላይ ማዋል መቀጠል በተለያዩ ጊዜያት የተለቀቁ የጌም መድረኮችን ይበልጥ ለማሻሻል ዕድል እንደሚሰጥ ገልፀዋል። ባሳለፍነውም ዓመት ፣ Call of Duty: Modern Warfare 3 በድሮ የጌም መድረኮች ላይ መለቀቁ የሚታወቅ ነው።
የድሮ የጌም መድረኮችን መደገፍ ለምን አስፈለገ?
እነዚህ የጌም መድረኮችን የሚጠቀሙ ሰፊ ተጠቃሚዎች በመኖራቸው ፣ አክቲቪዢን የድሮ የጌም መድረኮችን መደገፍ መቀጠሉን መርጧል። Activision ሰፊ የድሮ ጌም መድረክ ተጠቃሚዎችን እና አዲስ የጌም መድረኮችን መጠቀም ያልጀመሩ ተጫዋቾችን ለማካተት እና ተቋዳሽ ለማድረግ ወስኗል።
ሌላው ትኩረት የታሰበው መረጃ ፣ የኒንቴንዶ ስዊች 2 አብሮ መጠቀስ ሲሆን ፣ በተገኘው መረጃ መሰረት አክቲቪዥን እና ማይክሮሶፍት ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ ፣ Call of Duty ለአስር ዓመታት በኒንቴንዶ መድረኮች ላይ እንደሚገኝ ፣ ግን ይህ የሚሆነው ፣ በሚቀጥለው ዓመት በሚለቀቀው አዲሱ ስዊች ላይ ይሆናል።
እነዚህ መረጃዎች ሰኔ 9 በሚደረገው የCall of Duty ኤግዚቢሽን ላይ የሚረጋገጡ ሲሆን ፣ ይህ ኤግዚቢሽን ስለ Black Ops 6 ይፋዊ መረጃዎችን ፣ የእያንዳንዱን የጌም መድረክ ስሪቶች ዝርዝርን እና ስለተካተቱ አዳዲስ ነገሮች ወይም ማሻሻያዎች ለማግኘት ይረዳል።