icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የፎርትናይት ፈታኝ ተልዕኮዎችን ለማጠናቀቅ ፣ የበረሃ ገነቶችን (Oasis) የት እና እንዴት ማግኘት ይቻላል? 

ፎርትናይት በምዕራፍ 5 ክፍል 3 የተለመደውን ሳምንታዊ ተልዕኮዎቹን ቀጥሏል። እነዚህ ተልዕኮዎች ኤክስፒን (XP) ለመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ፣ ልዩ የውጊያ ማለፊያ ሽልማቶችን ፣ ማሻሻያዎችን እና ቪ-በክስን (V-Bucks) ማግኘት ያስችላሉ። ከዚህ ሳምንት ፣ ተልዕኮዎቹ አንዱ የበረሃ ገነት (Oasis) ውስጥ ህይወትን እና መከላከያ ትጥቆችን ማደስን ያካትታል። 

ፎርትናይት ላይ ህይወትን እና መከላከያ ትጥቆችን ለማደስ ፣ የፈውስ ግብዓቶችን መጠቀም የሚያስፈልግ ቢሆንም ፣ የተወሰኑ ልዩ አከባቢዎችም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ይሰጣሉ። ይህን ተልዕኮ ለመወጣት እና እንዴት እነዚህን የበረሃ ገነቶች (Oasis) ማግኘት እንደሚችሉ ከዚህ ቀጥሎ እናያለን። 

የፎርትናይት የበረሃ ገነቶችን (Oasis) በመጠቀም እንዴት ህይወትን ማደስ ይቻላል? 

ይህንን ተልዕኮ ለመወጣት በቅድሚያ የበረሃ ገነትን (Oasis) ማግኘት እና ውሃው ውስጥ መግባት ያስፈልጋል።  ወዲያው ውሃው ውስጥ እንደገቡ ህይዎትዎ መታደስ የሚጀምር ሲሆን ፣ ህይዎትዎ ሙሉ በሙሉ ታድሶ እንደጨረሰ ፣ መከላከያ ትጥቅዎ መታደስ ይጀምራል። ሂደቱ በሰከንድ 1 HP የሚያድስ በመሆኑ ጥቂት ጊዜን ስለሚወስድ ፣ በትዕግስት መጠባበቅ አስፈላጊ ነው። 

የተልዕኮውን ሂደት ማፋጠን ከፈለጉ የበረሃው ገነት (Oasis) ውስጥ እያሉ የፈውስ ግብዓቶችዎን መጠቀም ይችላሉ። ይህን ዘዴ መጠቀም የበረሃው ገነት (Oasis) ውስጥ በመግባት የሚያገኙት ነጥብ ላይ ተጨምሮ የሚቆጠር ይሆናል። 

የበረሃ ገነቶች (Oasis) የት ይገኛሉ፡- 

  1. ግድቡ ላይ የሚገኘው ድልድይ (The Dam Bridge)፡- ይህ የበረሃ ገነት ከደኑ በስተ-ምስራቅ የሚገኝ ሲሆን ፣ በቀላሉ የሚገኝ እና ብዙ መጨናነቀ ያልበዛበት በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል። 

  1. ፒ ቦይስ እና ሜጋሎ መጋዘን መካከል (Between Pea Bois HQ and Megalo Depot)፡- ይህ ቦታ በተትረፈረፈ የሀብት ክምችቱ በተጨዋቾች የሚመረጥ የዝርፊያ ቦታ በመሆኑ ፣ ይጠንቀቁ! 

  1. ሬድላይን ሪግ እና ሊል ደርቲ ሮክ መካከል (Between Redline Rig and Lil Dirty Rock)፡- ይህ ቦታ ወደ ውጊያ ከማምራትዎ በፊት ፣ ህይዎትዎን ማደስ ይየሚችሉበት ተመራጪ ቦታ ነው። 

  1. ከብራውለርስ ጦር ሜዳ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ፡- ይህ ቦታ ለጀብድ አፍቃሪዎች የሚሆን አካባቢ ሲሆን ፣ ህይወትን ሙሉ ለሙሉ ለማደስ ግን ከፍተኛ ጥንቃቄን ይጠይቃል። 

  1. በናይትሮድሮም እና በፓንታዮን መንገድ መካከል፡- ይህ ቦታ ግር ግር ያልበዛበት እና ፀጥተኛ ቦታ ሲሆን ፣ በሰላም ህይወትን ለማደስ ተመራጭ ነው። 

ምንጭ፡- Fortnite.gg 

አሁን ይህንን ተልዕኮ በድል ለመወጣት እና የውጊያ ማለፊያዎን ለማሳደግ በቂ መረጃ አግኝተዋል። ይህን አዲስ ምዕራፍ የመጫወት አጋጣሚን አግኝተው ከሆነ ፣ ውጊያዎችን ለማሸነፍ መኪናዎች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን አስተውለው ይሆናል። ይህን አስመልክቶም ፣ ኢፒክ ጌምስም አንዳንድ በክፍያ ማግኘት የሚችሏቸው የመኪና አማራጮች (Skins) ድልን ለመቀዳጀት ትልቅ አስተዋፆ እንደሚጫወቱ አመላክቷል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !