
ፎርትናይት በምዕራፍ 5 ፣ 2ኛ ክፍሉ ለተጫዋቾች የሌዲ ጋጋ ኦንላይን ኮንሰርቶችን ፣ ልዩ መለዋወጫዎች ፣ ዝግጅቶችን የማቅረብ እና ከታዋቂ አርቲስቶች ጋር ሽርክናን የመፍጠር ልምድ አለው።
መረጃ አቀባዮች በቅርቡ በተለቀቀው ምዕራፍ 5 ፣ ክፍል 3 ዙሪያ እና ወደፊት ስለሚመጡ ይዘቶች ፍንጭ ለማግኘት የጌሙን ፋይሎች በመበርበር ላይ ይገኛሉ። የቅርብ ጊዜ ግኝታቸው አንድ አስደሳች አዲስ ክስተትን ጠቁሟል ፥ ይህም በሜታሊካ ባንድ የተሰራ የኦንላይን ኮንሰርት በቅርቡ ሊመጣ እንደሚችል ይጠቁማል።
ታዋቂው መረጃ አቀባይ ሺና ፣ በዚህ ምዕራፍ የሜታሊካ ኮንሰርት ሊኖር እንደሚችል እና ፋይሎቹ የሜታሊካ ኮንሰርት "በCH5S3 Metallica Concert" በግልፅ እንዳስቀመጡ አጋርቷል።
በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ተጨማሪ ዝርዝሮች ይለቀቃሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ፣ የሜታሊካ "Fuel" የተሰኘውን ዘፈን የፎርትናይት ምዕራፍ 5 ፣ ክፍል 3 ማጀቢያ ሙዚቃ መሆኑ ይበልጥ ነገሩን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም፣ ይህ የፎርትናይት አዲስ ምዕራፍ ተጫዋቾች ጠቃሚ ነጥቦችን ማግኘት የሚያስችሏቸውን አዳዲስ ልዩ የጦር መሳሪያዎችን ፣ ኦሪጅናል መለዋወጫዎችን ፣ አዲስ የውጊያ ማለፊያ እና ሳምንታዊ ተልዕኮዎችን እና በርካታ አዳዲስ ይዘቶችን ይዞ የሚቀርብ ይሆናል።
ፎርትናይት በአዳዲስ ዝመናዎቹ እና ልዩ ዝግጅቶቹ ተጫዋቾችን ማስደሰቱን የቀጠለ ሲሆን ፣ ከሙዚቀኞች ጋር ከሚደረገው ሽርክና በተጨማሪ ታዋቂ ፍራንቻይዝ ከሆኑት ፣ ማርቨል እና ዲሲ ኮሚክስ ሲርየስ (Marvel and DC Comics series) ጋር በመተባበር ዝግጅቶችን ያቀርባል። እነዚህም ሽርክናዎች ለተጫዋቾች አዳዲስ ገጸ-ባህሪያትን ፣ መለዋወጫዎችን እና ልዩ የሆኑ የጨዋታ አማራጮችን ይዘው የሚመጡ ይሆናል።
ከዚህም በላይ ፎርትናይት ፣ አዳዲስ ገፀ-ባህሪያትን እና ኦሪጅናል የጨዋታ አካሄዶችን በመደበኛነት በማስተዋወቅ ከኦንላይን ጌሞች በግንባር ቀደምነት የቆየ ሲሆን ፣ በጊዜያዊ የጨዋታ አማራጮች ፣ የማህበረሰብ ተልዕኮዎች ወይም አዳዲስ ዝመናዎች በማዘጋጀት ፣ ኢፒክ ጌምስ የተጫዋቾችን ፍላጎት ማሟላቱን ቀጥሏል።