icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

በፎርትናይት የመኪኖች ግዢ ዙርያ የተነሳው ውዝገብ እና የኢፒክ ጌምስ ምላሽ 

በኢፒክ ጌምስ ተዘጋጅቶ የቀረበው ታዋቂው የጦርነት ሮያል ቪዲዮ ጌም ፎርትናይት ሰሞኑን መነጋገሪያ ሆኗል። የእዚህም ምክንያት ምዕራፍ 5 ፣ ክፍል 3 ላይ ያስተዋወቃቸው መኪኖች ናቸው። በነጻ መኪኖች እና በግዢ መኪኖች መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩ እና ፥ ጌሙ ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ መሆን አለመቻሉ ነበር ሰፊ ክርክርን ያስነሳው። 

ታዋቂው እና ተፅዕኖ ፈጣሪው (NickEh30) በዚህ ጉዳይ ላይ ቲኪቶክ ላይ የሰራው ቪዲዮ ይበልጥ ነገሩን ያሰፋው እና ያባሰው ሲሆን ፣ በቪዲዮው ላይ ነፃ መኪናዎችን የሚጠቀሙ ተጫዋቾች ላይ ጥቃት ማድረስ ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እና ፣ የግዢ መኪኖች ደግሞ ምን ያህል አይበገሬ መሆናቸውን በግልፅ አሳይቷል። 

ይህንንም ተከትሎ ኢፒክ ጌምስ ፎርትናይት ውስጥ በሚገኙ መኪኖች መካከል ሚዛናዊነት አለመኖሩን እንዲያምን ተገዷል። NickEh30's በቪዲዮ ላይ ፣ እንደ ዊፕላሽ (Whiplash) ፣ ዌርዎልፍ (Werewolf) ፣ ስኮርፒዮን (Scorpion) እና ማሳሙኔ (Masamune) የተባሉ ነፃ መኪኖች ባለትልቅ መስታወት በመሆናቸው ፣ ጠላቶች ምን ያህል በቀላሉ ሹፌሩን በመስታወቱ በኩል ተኩሰው መግደል እንደሚችል እና ይባስ ብሎ በተሳፋሪ ወንበር በኩል ዘለው መግባት እንደሚችሉ አሳይቷል። 

በሌላ በኩል ደግሞ ፣ ባለአነስተኛ መስተዋት የሆኑ ፣ እንደ ሳሞራይ (Samurai) ያሉ የክፍያ መኪኖች ፥ ጠላቶች ሹፌሩን በቀላሉ አነጣጥረው መምታት እንዳይችሉ የመከላከል አቅማቸው ከፍ ያለ መሆኑን አሳይቷል። 

ይህ ልዩነት ለማሸነፍ ይክፈሉ (pay-to-win) የሚለው አካሄድ ችግር እንዳለበት የሚጠቁም እና ኢፒክ ጌምስ የቆመለትን ዓላማ የሚቃረን ነው።  

እየጨመረ የመጣውን ቅሬታ ፣ ኢፒክ ጌምስ ችላ ብሎ ማለፍ ባለመቻሉ ፣ ኩባንያው በቅርቡ ለኮታኩ (Kotaku) በሰጠው መግለጫ ላይ ፣ ይህን ኢ-ሚዛናዊነት መረዳታቸውን እና በመጪው ዝመና ላይ ማሻሻያ እና ማስተካከያ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አምነዋል። 

ለጊዜው ተጫዋቾች በመጪው ዝመና ላይ የሚደረገውን ማሻሻያ እና ማስተካከያ በትዕግስት መጠባበቅ ይኖርባቸዋል። ይህ ስለጨዋታው ፍትሃዊነት እና ተጨዋቾች በኩባንያው ላይ ያላቸውን ቀጣይ እምነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው። 

እንደ ፎርትናይት ባሉ አፎካካሪ እና ፣ ትንሽ ነገሮች ድል እና ሽንፈትን መፍጠር በሚችሉበት ቪዲዮ ጌም ፣ ለማሸነፍ ይክፈሉ (pay-to-win) የሚለው ጉዳይ ፍትሃዊነትን የሚቃረን ሀሳብ ነው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !