
ጥላማው ግዛት በአደጋዎች እና ምስጢሮች የተሞላ ስውር ግዛት ነው። በኤልደን ሪንግ አፈ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ የሆነው ሚኬላ (Miquella) በዚህ አዲስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሚናን ይጫወታል። ተጫዋቾች ስለዚህ እንቆቅልሽ ገፀ-ባህሪ ይበልጥ ማወቅ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ጓዶች እና ጠላቶች ጋር የመገናኘት ዕድል ይኖራቸዋል። ከእነዚህም መካከል መስመር (Mesmer) የተባለው ገፀ-ባህሪ በአስደናቂ ልዩ ችሎታዎቹ ከሁሉም ጎልቶ ይታያል።
Shadow of the Erdtree አዳዲስ ፈታኝ የጠላት አለቆችን ያካተተ ሲሆን ፣ የእያንዳንዳቸውም አቅም ይለያያል ፥ እነሱንም ለማሸነፍ ልዩ ስልቶችን መከተል ያስፈልጋል። እነዚህን ፈታኝ የጠላት አለቆች እንደየ ደረጃቸው መጋፈጥ የሚያስችሉ ስልቶች በዚህ መመሪያ አዘጋዝተናል።
የShadow of the Erdtree ቅጥያ ላይ የሚገኙ የጠላት አለቆችን ፣ በደረጃዎች እና ባገኟቸው ሽልማቶች መሰረት ፥ መጋፈጥ የሚችሉባቸው ስልታዊ ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ተቀምጧል፦
የመለኮቱ አውሬ ደናሽ አንበሳ (Dancing Lion of the Divine Beast)
ሬላና ፣ ባለመንትያ ሰይፏ ተዋጊ (Rellana, Knight of Twin Blades)
ወርቃማው ጉማሬ (Golden Hippopotamus)
ሮሚና ፣ ቅድስቷ እምቡጥ አበባ (Romina, Saint of the Bud)
መስመር ባለሰንጢው (Mesmer the Impaler)
ሌዳ እና ጓዶቿ (Leda and her Allies)
ራዳህን ፣ (Radahn, Future Consort) ፥ የመጨረሻው እና በጣም ፈታኙ ጠላት ሲሆን ፣ የእዚህ DLC መዝጊያ አስደናቂ ውጊያን ከእዚህ ጠላት ጋር ያደርጋሉ።
ተጨማሪ ጠላቶች
ዋና ጠላቶችን ካሸነፉ በኋላ ፣ ተጨማሪ ሽልማቶችን ለማግኘት ሌሎች ጠላቶች ጋር መፋለም ይችላሉ። ለምሳሌ፦ ሜቲር (Metyr) ታሪኩ ውስጥ ጉልህ ቦታ ባይኖረውም ፥ ተጨማሪ ፍልሚያ እና ድልን ለሚሹ ተጫዋቾች ያገለግላል።
ጠቃሚ ስልቶች
እነዚህን ጠላቶች መጋፈጥ ትዕግስት ብቻ ሳይሆን ጥሩ ዝግጅትንም ይጠይቃል። ለእዚህም ይረዳዎት ዘንድ ቀጥሎ የተቀመጡትን ስልቶች ይጠቀሙ፡-
የጥቃት ዘዴዎችን ማጥናት፦ እያንዳንዱ የጠላት አለቆች ልዩ የጥቃት ዘዴዎችን የሚጠቀሙ በመሆኑ ፣ ጥቃትን ለመከላከል እና መልሰው ማጥቃት እንዲችሉ ስልቶቻቸውን በሚገባ ያጥኑ።
ትጥቆችን በአግባቡ ይታጠቁ፡- እያንዳንዱን የጠላት አለቆች የሚመጥኑ እና ጌሙ ውስጥ የተካተቱ አዳዲስ መሳሪያዎችን እና ድግምቶችን ይጠቀሙ።
ጓዶችን ይጠቀሙ፡- መንገድ ላይ የሚያገኟቸውን NPCዎች እርዳታ በመጠቀም ፣ አንዳንድ የጠላት አለቆችን በቀላሉ ማሸነፍ የሚችሉ በመሆኑ ፣ ትግሉን ሚዛናዊ ለማድረግ እነሱን ከመጥራት ወደኋላ አይበሉ።
ጥላማውን ግዛት በጥንቃቄ እና በቆራጥነት ያስሱ። እያንዳንዱ የሚያሸንፏቸው የጠላት አለቆች ኤልደን ሪንግ ዩኒቨርስ ወደምትሰጠው ክብር እና ሽልማቶች አንድ እርምጃ ያቀርቦታል።