icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ባለመንታ ሰይፏ ተዋጊ ፣ ሬላናን (Rellana, Knight of Twin Blades) የት ማግኘት እና እንዴት ማሸነፍ ይቻላል? 

በጉጉት የሚጠበቀውን የኤልደን ሪንግ (Elden Ring) ቅጥያ (Shadow of the Erdtree DLC) በመጨረሻ ለጨዋታ በቅቷል። ይህ ቅጥያ በአዳዲስ ፣ የጦር መሳሪያዎች ፣ ድግምቶች ፣ ምትሃታዊ ክታቦች እና ፈታኝ የጠላት አለቆች የተሞላ አዲስ ግዛት ነው። ይህንን አደገኛ ዓለም ፣ ከሚኬላ (Miquella) እና ከመስመር (Mesmer) ጋር ለማሰስ ይዘጋጁ።  

ሬላና በኤልደን ሪንግ (Elden Ring) ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ የጠላት አለቆች መካከል አንዷ ስትሆን ፣ በልዩ የውጊያ ስልቶቿ እና ብቃቷ ትታወቃለች። እሷን በማሸነፍ የጦር መሣሪያዎቿን መንጠቅ የሚችሉ ሲሆን ፣ ሬላናን እንዴት እና የት አግኘተው ማሸነፍ እንደሚችሉ ፣ ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር አስቀምጠናል፡- 

የት? 

  • ኤንሲስ ካስትል (Ensis Castle) 

አጋዥ ቪዲዮ 

  • ከዚህ በታች የሬላናን ችሎታ የሚያሳይ አጭር የጨዋታ ቪዲዮ ያገኛሉ፡- 

ሪላናን (Rellana) ማሸነፊያ ስልቶች 

የውጊያ ስልቶቿን ያጥኑ 

  • የሬላና የውጊያ ስልቶች በቀላሉ ሊገመቱ የሚችሉ በመሆናቸው ፣ የረጅም ርቀት ውጊያን በማስወገድ አጠገቧ ሆነው ይፋለሙ። 

አቀማመጥ 

  • ከሪላና ጥቃት ለመዳን ፣ ከኋላዎ በመሆን ጥቃት ይጣሉባት። 

የመንታ ጨረቃዎች ጥቃቷን (Twin Moons Attack) ፣ በመዝለል ይሸውዱ  

  • ይህ የጥቃት ስልቷ ከፍተኛ ጉዳትን ስለሚያደርስ ፣ ጥቃቱን በምታደርግበት ወቅት ሁለት ጊዜ በመዝለል ራስዎን ያድኑ። 

ማስታወስ ያለብዎ ጠቃሚ ነጥቦች 

የመቋቋም አቅሟ፦ 

  • ሬላና ከ29,000 በላይ የህይዎት ነጥቦች ስላላት ፣ ለመሸነፍ ረጅም ጊዜን ትወስዳለች። 

ድክመቶቿ፦ 

  • ነጭ አስማት (Holy Damage) ፣ ስለታማ መሳሪያዎችን (Lacerations) እና የበረዶ ማድረቂያ ጥቃቶችን (Frost Damage) የመቋቋም አቅሟ አነስተኛ ነው።  

  • ጥቃቶቿን መመከት (Parry) የሚችሉ ሲሆን ፣ ሁለት ጊዜ ጥሩ አርገው በመመከት ፣ ሚዛኗን ስታ እንድትንገዳገድ ማድረግ ይችላሉ። 

የጥቃትን የመቋቋም አቅሟ፡-  

  • እሳትን የመቋቋም አቅሟ ከፍተኛ ነው።. 

የጥቃት ስልቶቿ፡- 

ሬላና ስለታማ መሳሪያዎችን ፣ እሳትን እና የበረዶ ማድረቂያ ጥቃቶችን ስለምትጠቀም ፣ ከጥቃት እራስዎን ለመጠበቅ ልዩ መከላከያ መታጠቅዎን ያስታውሱ። 

ስለ ኤልደን ሪንግ 

በፍሮም ሶፍትዌር (From Software) የተሰራው ኤልደን ሪንግ (Elden Ring) እ.ኤ.አ. በ2022 የተለቀቀ ሲሆን በተለቀቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአመቱ ምርጥ ጌም ለመባል በቅቷል። ምንም እንኳን ፈታኝ ጌም ቢሆንም ፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጫዋቾችን ልብ መግዛት ችሏል። ይህን መመሪያ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ፣ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ከፈለጉ Shadow of the Erdtree DLC ዙሪያ ያዘጋጀናቸውን ሌሎች መመሪያዎቻችንን ይመልከቱ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !