icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የኤልደን ሪንግ ቅጥያ (Elden Ring DLC) ​​ላይ የሚገኘውን ፒውትረሰንት ናይትን (Putrescent Knight) የት ማግኘት እና እንዴት ማሸነፍ ይቻላል? 

በጉጉት የሚጠበቀውን የኤልደን ሪንግ (Elden Ring) ቅጥያ (Shadow of the Erdtree DLC) በመጨረሻ ለጨዋታ በቅቷል። ይህ አዲስ ቅጥያ ፣ የሚኬላ (Miquella) ፈለግ በመከተል ሚስጥራዊውን አዲስ ገፀ-ባህሪ መስመርን (Mesmer) እና ሌሎች አስደናቂ ነገሮችን ወደ ሚያገኙበት ጥላማው ግዛት ያስገባዎታል። 

ይህ አዲስ ጥቅያ (DLC) ብዙ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን ፣ ድግምቶችን ፣ ምትሃታዊ ክታቦችን እና ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አስፈሪ አዳዲስ የጠላት አለቆችን አካቷል። ከዚህ በተጨማሪ ፣ የራሳቸው ተልዕኮ እና አላማ ያላቸው አዳዲስ ፀጉረ ልውጥ ገፀ-ባህሪያትም ተካተዋል። ወደ ቅድስት ትሪና (St. Trina) የሚያደርጉት ጉዞ ላይ እንቅፋት የሚሆንብዎን ፒውትረሰንት ናይትን (Putrescent Knight) እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻሉ በዚህ መመሪያ በዝርዝር እናያለን። 

ፒውትረሰንት ናይትን (Putrescent Knight) የት ይገኛል? 

ፒውትረሰንት ናይት ፣ ከቲዮሊየር (Thiollier) ጋር የሚያደርጉትን ተልዕኮ የሚያሰናክል አስፈሪ ጠላት ነው። ይህም አስፈሪ ጠላት ፊሸር (Fissure) ውስጥ ከሚገኘው ፣ የበሬ ጭንቅላት መሳይ ግዙፍ የድንጋይ መዋቅር ስር የሚገኝ ሲሆን ፣ ከበሬ ጭንቅላት ወደ ታች ሲዘሉ ያገኙታል። ዝላዩ ጉዳት ያደርስብኛል ብለው አይጨነቁ ፣ ምንም ጉዳት አይደርስብዎትም። 

ፒውትረሰንትን እንዴት ማሸነፍ ይቻላል? 

ቦታው ላይ እንደደረሱ ይህን ሞት የጠማው ባለጋራ የሚፋለምዎ ሲሆን ፣ እሱን ማሸነፍ የሚያስችሉት ውጤታማ መንገዶች ፣ በእምነት ላይ የተመሠረቱ ማሻሻያዎችን እና ነጭ አስማትን መጠቀም ነው። ለፍልሚያው የሚረዱዎትን አንዳንድ ነጥቦች እንደሚከተለው አስቀምጠናል፦ 

  • ቅዱስ ድግምቶች፡- ከፍተኛ ጉዳቶችን ለማድረስ ቅዱስ ድግምቶችን ይጠቀሙ። 

  • በቅርበት ያጥቁት፡- ፈረስ ላይ ሁኖ በሰይፉ ወይም በሌላ በቅርብ ርቀት መሳሪያዎች እንዳያጠቃዎ ፣ በተቻለ መጠን በደንብ ተጠግተው ይፋለሙት። 

  • ክፍተቶችን ይጠቀሙ፡- ጥቃት ካደረሰ በኋላ የሚፈጥራቸውን የመዘናጋት አጋጣሚዎች ፣ ከባድ ጥቃት ለማድረስ ይጠቀሙባቸው። 

  • ፒውትረሰንት ናይትን ካሸነፉ በኋላ ወደ ቅድስት ትሪናን ያቅኑ ፣ እዛ እንደደረሱ ይህን አስፈሪ የጠላቶች አለቃ ድል ለነሱበት ትልቅ ሽልማት ተዘጋጅቶ ይጠብቆታል። 

ስለ ኤልደን ሪንግ 

በፍሮም ሶፍትዌር (From Software) የተሰራው ኤልደን ሪንግ (Elden Ring) እ.ኤ.አ. በ2022 የተለቀቀ ሲሆን በተለቀቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአመቱ ምርጥ ጌም ለመባል በቅቷል። ምንም እንኳን ፈታኝ ጌም ቢሆንም ፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጫዋቾችን ልብ መግዛት ችሏል። ይህን መመሪያ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ፣ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ከፈለጉ Shadow of the Erdtree DLC ዙሪያ ያዘጋጀናቸውን ሌሎች መመሪያዎቻችንን ይመልከቱ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !