icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ስኳድ በስተርስን (Squad Busters) ኮምፒውተር ላይ መጫወቻ መንገዶች 

የክላሽ ኦፍ ክላንስ (Clash of Clans) እና የብራውል ስታርስ (Brawl Stars) አዘጋጆች ሱፐር-ሴል (Supercell) እ.ኤ.አ ግንቦት 2024 መጨረሻ ላይ ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) የተባለው ጌማቸውን ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ ለቀዋል። ይህ አስደሳች ጨዋታም በአጭር ጊዜ ተወዳጅነትን አግኘቷል። ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) iOS እና አንድሮይድ ላይ ብቻ የሚገኝ ቢሆንም ፣ ፒሲ ላይ አንድሮይድ ኢምዩላተሮችን በመጠቀም መጫወት የሚቻልባቸው መንገዶችም አሉ። 

ስኳድ ብስተርስን (Squad Busters) ፒሲ እንዴት መጫን ይቻላል? 

ምንም እንኳን ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ለተንቀሳቃሽ ስልኮች ብቻ የተዘጋጀ ቢሆንም ፣ አንድሮይድ ኢሙሌተሮችን እና ከዚህ ቀጥሎ የተቀመጡት ሂደቶችን በመጠቀም ኮምፒውተርዎ ላይ መጫወት ይችላሉ። 

  • አንድሮይድ ኢሙሌተርን መምረጥ 

ስኳድ በስተርስን (Squad Busters) ያለምንም እክል መጫወት ይችሉ ዘንድ ፣ ጥሩ የአንድሮይድ ኢሙሌተር መጠቀም ያስፈልግዎታል። ለዚህም ይረዳዎት ዘንድ ፣ ሁለት ጥሩ አማራጮችን አስቀምጠናል። 

  • ብሉስታክስ (BlueStacks)፡- አስተማማኝ እና በሰፊው ጥቅም ላይ የሚውል ፣ ታዋቂ ኢሙሌተር። 

  • ሜሙ ፕለይ (Memu Play)፡- በአፈፃፀም ሂደቱ እና በአጠቃቀም ቀላልነቱ የሚታወቅ ፣ ሌላው ምርጥ አማራጭ። 

ኢሙሌተርን ማውረድ እና መጫን 

  • የብሉስታክስን (BlueStacks) ወይም የሜሙ ፕለይ (Memu Play) ህጋዊ ድረ-ገፅን ይክፈቱ። 

  • ኢሙሌተሩን ያውርዱ። 

  • ኢሙሌተሩን ኮምፒውተርዎ ላይ ለመጫን ፣ ስክሪንዎ ላይ የሚመጡትን መመሪያዎች ይከተሉ። 

  • ኢሙሌተሩን በመጠቀም ስኳድ በስተርስን (Squad Busters) ይጫኑ። 

  • የጫኑትን ኢሙሌተር ይክፈቱ። 

  • ወደ ጎግል ፕሌይ አካውንትዎ ይግቡ። 

  • ኢሙሌተሩ ውስጥ ጎግል ፕሌይ ስቶርን ይክፈቱ እና "Squad Busters" ብለው ይፈልጉ። 

  • በመጨረሻ ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ ለማንኛውንም መተግበሪያ እንደሚያደርጉት ፣ አውርደው ፣ ይጫኑት። 

ለተሻለ የጨዋታ ተሞክሮ መቆጣጠሪያዎቹን ያስተካክሉ 

አብዛኛዎቹ ኢሙሌተሮች  ፣ የተሻለ የጨዋታ ተሞክሮ እንዲኖርዎ የኮምፒውተርዎን ቁልፎች (Keyboards) እንደምርጫዎ እንዲያዘጋጁ ያስችሉዎታል። ጨዋታዎን የበለጠ አስደሳች እና ቀላል ለማድረግ እነዚህን መቆጣጠሪያዎች ያስተካክሉ፦ 

ስኳድ በስተርስን (Squad Busters) ኮምፒውተርዎ ላይ ያጣጥሙ 

ከላይ እንደጠቀስነው ፣ ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ለኮምፒውተሮች በይፋ ባይዘጋጅም ፣ እንደ ብሉስታክስ እና ሜሙ ፕሌይ ያሉ የአንድሮይድ ኢሙሌተሮችን በመጠቀም ኮምፒውተርዎ ላይ መጫወት ይችላሉ።  

ከላይ የተዘረዘሩትን ሂደቶች በመከተል ፣ አስደማሚውን የስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ዓለምን ፣ ኮምፒውተርዎ ላይ ማጣጣም ይችላሉ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !