icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ላይ አሪፍ ተጫዋች መሆን የሚያስችሉ 4 ነጥቦች! 

ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) በልዩ እና በሚማርክ የጨዋታ ዘይቤው ፣ ተጫዋቾችን አስደናቂ ውድድሮች ላይ የሚያሳትፍ ሲሆን ፣ ጉርሻዎችን ክመሰብሰብ እና የተለያዩ ጭራቆችን ከመጋፈጥ ባለፈ ፣ እንቁዎችን (Gems) በአግባቡ መጠበቅ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። አሪፍ እና ድንቅ ተጫዋች ለመሆን እና የማሸነፍ ዕድልዎን ለመጨመር የብሬክ-ፍሊፕን (Breakflip) 4 ጠቃሚ ምክሮች እና ስልቶችን ይከተሉ፡- 

1. ለወታደሮች ውህደት ቅድሚያ ይስጡ! 

በስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ውስጥ በጣም ወሳኝ ከሆኑ ስልቶች መካከል ፣ የወታደሮች ውህደት ሲሆን ፣ ሶስት ተመሳሳይ ወታደሮችን በማዋሃድ ጠንካራ እና አይበገሬ ማድረግ ይቻላል። ይህን ዘዴ ለመጠቀም ፣ ተመሳሳይ ወታደሮችን መሰብሰብ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፦ ሶስት የተዋሃዱ ባርቤሪያኖች ፣ ከአንድ ባርቤሪያን ንጉስ የበለጠ ኃይለኛ እና አይበገሬ ናቸው! 

2. ወደ ማዕድን መክፈቻው በፍጥነት ያምሩ! 

ድልዎን ለማስጠበቅ ፣ በተቻለ መጠን ጊዜ ሳያልቅ ብዙ እንቁዎችን መሰብሰብ የሚኖርብዎ ሲሆን ፣ ጭራቆችን በማስወገድ ፣ ዛፎችን በመቁረጥ ፣ ሳጥኖችን በመሰባበር እና ጠላቶችን ድል በመንሳት እንቁዎችን መሰብሰብ ይችላሉ። እንቁዎችን በአጭር ጊዜ መሰብሰቢያው መንገድ ፣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ሲቀረው ፣ እጅግ በርካታ እንቁዎች የሚገኙበት ፣ ማዕድን ማውጫ ላይ በፍጥነት መገኘት ነው። 

3. ጉርሻዎችዎን በሙሉ ይሰብስቡ! 

ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ላይ የሚገኙ ጉርሻዎች ፣ የቦምብ ጥቃትን ለመጨመር ፣ ሠራዊቶችን ለመፈወስ እና ችሎታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመር ስለሚያስችሉ ፣ እጅግ ወሳኝነት አላቸው። ጉርሻዎች ድንገት ካርታ ላይ የሚመጡ ሲሆን ፣ ወዲያው እንደመጡ መውሰድ ይኖርብዎታል። 

4. የሠራዊትዎን አቅም ያሻሽሉ! 

ወታደሮችን ማዋሃድ አስፈላጊ ቢሆንም አቅማቸውን ማሻሻል ላይ ማተኮር ይበልጥ ወሳኝነት አለው። ጌሙ ውስጥ ስኳድ (Squad) የሚለው አማራጭ ውስጥ በመግባት ሠራዊትዎን ማሻሻል ይችላሉ። ተጨማሪ ክህሎቶችን ለማስከፈት እና የወታደሮችዎን አቅም ለማሻሻል ፣ የሠራዊት ሽልማቶችን ጨዋታ ሲጨርሱ ከሚያገኟቸው ሣጥኖች ወይም ከጌሙ መደብር ፣ መሰብሰብዎን አይርሱ። 

እነዚህን ነጥቦች በመከተል፣ ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ላይ መንገስ ይችላሉ። መልካም ዕድል! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !