icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የማሪዮ እና ሉዊጂ ፡ ብራዘርሁድ ኢፒክ መሸጫ ዋጋ 

ኒንቴንዶ እ.ኤ.አ ሰኔ 18 2024 ፣ ኒንቴንዶ ዳይሬክት ላይ ፥ (Nintendo Direct) ማሪዮ ፓርቲ ጃምቦሬ (Super Mario Party Jamboree) ፣ ዘ ሌጀንድ ኦፍ ዜልዳ፡ ኢኮስ ኦፍ ዊዝደም (The Legend of Zelda: Echoes of Wisdom) ፣ ሜትሮይድ ፕራይም 4፡ ቢዮንድ (Metroid Prime 4: Beyond) ፣ እና ማሪዮ እና ሉዊጂ፡ ብራዘርሁድ ኢፒክን (Mario & Luigi: Brotherhood Epic) ጨምሮ በርካታ በጉጉት የሚጠበቁ ቪዲዮ ጌሞችን ሊለቅ እንደሆነ ይፋ አድርጓል። 

ይህን ዜና ተከትሎ ፣ ብዙ የቪዲዮ ጌም አፍቃሪያን ፡ እነዚህ አጓጊ ቪዲዮ ጌሞች መቼ እንደሚለቀቁ ጥያቄ እያነሱ የሚገኙ ሲሆን ፣ በአሁኑ ኒንቴንዶ ዳይሬክት ላይ የተሰጡ መረጃዎችን እንደሚከተለው አስቀምጠናል። 

የሚለቀቅበት ዕለት 

ሰኔ 18 ላይ ኒንቴንዶ ዳይሬክት ባሳየው ማስታወቂያ መሰረት ፥ ማሪዮ እና ሉዊጂ፡ ብራዘርሁድ ኢፒክ ፥ እ.ኤ.አ ህዳር 7 ፣ 2024 ኒንቴንዶ ስዊች ላይ የሚለቀቅ ይሆናል። 

መሸጫ ዋጋ 

በቅድመ-ትዕዛዝ ፣ ኒንቴንዶ መደብር ላይ በ €59.99 ዩሮ ዲጂታል ቅጂውን ማግኘት የሚቻል ሲሆን ፣  ይህም በይፋ ከመለቀቁ በፊት ቀድመው እጅዎ ላይ ማስገባት ያስችልዎታል። እንዲሁም በይፋ ሲለቀው ፣ በሲዲ ለሽያጭ የሚቀርብ ይሆናል። 

ይህ ገፀ-ባህሪያትን በመላበስ መጫወት የሚያስችል ጌም (RPG) ፣ ተጫዋቾች ማሪዮን ወይም ሉዊጂን በመሆን የተለያዩ ተልዕኮዎችን እንዲወጡ ያስችላቸዋል። በቅርብ የተለቀቀው ማስታወቂያም ላይ የታዩት ገፀ-ባህሪያት ፣ ታሪኩ ውስጥ ቁልፍ ሚናን የሚጫወቱ ሲሆን ፥ ተጫዋቾች ምስጢሮችን መፍታት ፣ አለቆችን ጨምሮ የተለያዩ ጠላቶች ጋር መዋጋት እና አዳዲስ ችሎታዎችን ማስከፈት ይጠበቅባቸዋል። አንዳንድ ተልዕኮዎችም ፣ የሁለቱንም ወንድማማቾች ትብብር እና ቅንጅት የሚፈልጉ ናቸው። 

ጌሙ አስገራሚ ግራፊክስ እና ማራኪ ማጀቢያ ሙዚቃዎችን ያካተተ ሲሆን ፣ አዘጋጆቹ እውነተኛ ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርግ ፣ ተለዋዋጭ ዓለም መፍጠር ላይ ትኩረት አድርገው ሰርተዋል። ተጫዋቾች ከአስማታዊ ደኖች እስከ ምስጢራዊ ቤተ-መንግስቶች ድረስ ያሉ የተለያዩ አካባቢዎችን ማሰስ የሚችሉ ሲሆን ፣ እያንዳንዱንም አካባቢዎች ለማግኘት ምስጢሮችን መፍታት እና ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ማለፍ ይጠባቅባቸዋል። 

በተጨማሪም ፥ ተጨዋቾች በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ተልዕኮዎችን በጋራ መወጣት ይችላሉ። ይህ አዲስ የጨዋታ መንገድ ተጫዋቾች ተልዕኮዎችን በጋራ መወጣት እንዲችሉ ፣ የወዳጅነት ወይም የፉክክር ጨዋታዎችን ማድረግ የሚያስችላቸው አዲስ አማራጭም ነው።  የማሪዮ እና የሉዊጂ የረጂም ጊዜ አድናቂዎች! አሁንም የሚወዱላቸውን አዝናኝ እና ሳቢ ስብዕና ፣ ከተጨማሪ ትኩስ እና አስደሳች የጨዋታ መንገዶች ጋር የሚያገኙ ይሆናል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !