icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ስለ ማሪዮ እና ሉዊጂ ፡ ብራዘርሁድ ኢፒክ ፣ ማወቅ ያለብዎ ነጥቦች 

ሰኔ 18 በተደረገው ኒንቴንዶ ዳይሬክት ላይ ፣ ኒንቴንዶ ብዙ በጉጉት የሚጠበቁ ጌሞችን ሊለቅ መሆኑን አሳውቋል። ከጌሞቹም መካከል ማሪዮ እና ሉዊጂ ፡ ብራዘርሁድ ኢፒክ (Mario & Luigi: Brotherhood Epic) የብዙዎችን ትኩረትን ስቧል። ቀጥሎ ስለዚህ ጌም ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦችን በዝርዝር አዘጋጅተናል፡- 

ልዩ ትብብርን የሚጠይቁ ተልዕኮዎች 

ማሪዮ እና ሉዊጂ ፡ ብራዘርሁድ ኢፒክ ላይ ፣ ተጫዋቾች ማሪዮን ወይም ሉዊጂን በመሆን የተለያዩ ተልዕኮዎችን ማጠናቀቅ የሚችሉበት የRPG ትብብር ጌም ሲሆን ፥ ወንድማማቾቹ በዚህ ዓለም ውስጥ አንድ ላይ በመሆን የተለያዩ ተልዕኮዎችን መወጣት እና መሰናክሎችን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። እኚህ ወንድማማቾች የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች ለመወጣት ፣ ምስጢሮችን ለመፍታት ፣ ጠላቶቻቸውን ለመጋፈጥ እና አዳዲስ ችሎታውችን ለማስክፈት ችሎታቸውን ማጣመር እና በቡድን መሥራት ይኖርባቸዋል። 

የሚለቀቅበት ቀን 

ጨዋታው እ.ኤ.አ ህዳር 7 ፣ 2024 ኒንቴንዶ ስዊች ላይ የሚለቀቅ ሲሆን ፣ እስከዛ ድረስ መጠበቅ አልችልም ለሚሉ የጌሙ አፍቃሪያን ፣ ከመልቀቂያ ቀኑ አስቀድመው ኒንቴንዶ መደብር ላይ በ€59.99 ዩሮ ዲጂታል ቅጂውን በቅድመ-ትዕዛዝ ማግኘት ይችላሉ። 

ይህ ጌም ፣ በቀለማት ያሸበረቀ አስደማሚ ግራፊክስ እና የሁለቱን ወንድማማቾች ጀብዱ ይበልጥ አጉልተው የሚያሳዩ ለጆሮ የሚጥሙ ማጀቢያ ሙዚቃዎችም ጌሙን ይበልጥ የማይረሳ ያደርጉታል። 

ተጫዋቾች ከአስማታዊ ደኖች እስከ ሚስጥራዊ ቤተ-መንግስቶች ድረስ ያሉ የተለያዩ አካባቢዎችን ማሰስ የሚችሉ ሲሆን ፣ እያንዳንዱንም አካባቢዎች ለማግኘት ምስጢሮችን መፍታት እና ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ማለፍ ይጠባቅባቸዋል። አዘጋጆቹም ተጫዋቾች እውነተኛ ዓለም ውስጥ ያሉ ያክል እንዲሰማቸው ፣ ልዩ እና ማራኪ ዓለም መፍጠር ላይ ትኩረት አድርገው ሰርተዋል።  

ኦንላይን ከአንድ በላይ በመሆን መጫወት 

ማሪዮ እና ሉዊጂ ፡ ብራዘርሁድ ኢፒክን ፥ ከፈለጉ ለብቻዎ ፣ ከፈለጉ ከጓደኞችዎ ጋር ኦንላይን መጫወት የሚችሉ ሲሆን ፣ ይህ ሞድ ጓደኞችዎ የትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ቢሆኑም ጨዋታውን መቀላቀል ያስችላቸዋል። ይህም ተልዕኮዎችን በጋራ እንዲወጡ እና ከጓደኞችዎ ጋር እንዲፎካከሩ ያስችሎታል። 

አዝናኝ እና ሳቢ! 

የእዚህ ተከታታይ ጌም አድናቂዎች ፣ የማሪዮን እና የሉዊጂን አዝናኝ እና ሳቢ ስብዕና ፣ ከተጨማሪ ትኩስ እና አስደሳች ጨዋታ መንገዶች ጋር የሚያገኙ ሲሆን ፣ የጌሙ አስደናቂነት እና አዝናኝነት ለፍሬንቻይዙ ስኬታማነት እንደምክንያት የሚቀመጡ ናቸው።

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !