icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ላይ የሚገኙ ምርጥ ገፀ-ባህሪያት ዝርዝር ፥ ሐምሌ 2024 እ.ኤ.አ  

በክላሽ ኦፍ ክላንስ (Clash of Clans) ፣ ክላሽ ሮያል (Clash Royale) እና ብራውል ስታርስ (Brawl Stars) አስደናቂ ስኬትን ያገኘው ሱፐርሴል (Supercell)  ፣ አሁን ደግሞ ስኳድ በስተርስን (Squad Busters) ይዞ የመጣ ሲሆን ፥ Brawl Stars ላይ የምናቃትን Shelly እና የClash of Clans ንግስቷን Archer Queen እና ሌሎች ታዋቂ ገፀ-ባህሪያትን ፣ እና አዳዲስ አስደናቂ ነገሮችን በማካተት ፥ ተጫዋቾችን ለማስደሰት ተዘጋጅቷል። 

ሚያዚያ 23 ፣ 2024 እ.ኤ.አ ተለቆ ፣ በአጭር ጊዜ የብዙ ተጫዋቾችን ልብ መግዛት የቻለው አስደናቂ ቪደዮ ጌም ስኳድ በስተርስ ላይ ምርጦቹ ገፀ-ባህሪያት የትኞቹ ናቸው? የሚለውን አንገብጋቢ ጥያቄ ፣ በዚህ መመሪያ መልስ የምንሰጥበት ይሆናል።  

ገፀ-ባህሪያትን በቀላሉ መምረጥ እንዲያስችሎት ፥ ከመደብ ኤስ (Tier S) (ኃይለኛ ገፀ-ባህሪያት) እስከ መደብ ዲ (Tier D) (ደካማ ገፀ-ባህሪያት) የሚገኙ ገፀ-ባህሪያትን በአምስት መደብ ከፋፍለን አስቀምጠናል።  

ማስታወሻ፡- ዝርዝሮቹ ጌሙ በተሻሻለ ቁጥር ሊለወጡ ይችላሉ። 

ምድብ ኤስ (Tier S) 

በእዚህ ምድብ የሚገኙ ገፀ-ባህሪያት እጅግ ኃይለኛ ፣ እና አስደናቂ ነገሮችን ማድረግ የሚችሉ ናቸው፦ 

  • አርቸር ክዊን (Archer Queen) - (ብርቅየ ገፀ-ባህሪ) 

  • ባርቤሪያን ኪንግ (Barbarian King) - (ብርቅየ ገፀ-ባህሪ) 

  • ፔኒ (Penny) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ሆግ ራይደር (Hog Rider) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ታንክ (Tank) (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

ምድብ ኤ (Tier A) 

በእዚህ ምድብ ላይ የሚገኙ ገፀ-ባህሪያት እጅግ ኃይለኛ ቢሆኑም የተወሰኑ ድክመቶች አሏቸው። ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ማድረግ ስለሚችሉ ግን ሊሞክሯቸው ይገባል፦ 

  • ዊች (Witch) - (ብርቅየ ገፀ-ባህሪ) 

  • ሞርቲስ (Mortis) - (ብርቅየ ገፀ-ባህሪ) 

  • ማክስ (Max) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ባርቤሪያን (Barbarian) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ቢያ (Béa) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ሮያል ኪንግ (Royal King) - (ብርቅየ ገፀ-ባህሪ) 

  • ቦ (Bo) -  (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ዊዛርድ (Wizard) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

ምድብ ቢ (Tier B) 

እነዚህን ገፀ-ባህሪያት ፣ ከፍተኛ ምድብ ላይ የሚገኙ ገፀ-ባህሪያትን እስከሚያስከፍቱ ድረስ ሊጠቀሟቸው የሚችሉ አማራጭ ገፀ-ባህሪያት ናቸው። 

  • አርሚ ሂለር (Army Healer) - (ብርቅየ ገፀ-ባህሪ) 

  • ኒታ (Nita) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ሮያል ኪንግ (Royal King) - (ብርቅየ ገፀ-ባህሪ) 

  • መርቻንት (Merchant) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ሸሊ (Shelly) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ሜዲክ (Medic) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ዳይናማይክ (Dynamike) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ግሬግ (Greg) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ኮልት (Colt) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

ምድብ ሲ (Tier C) 

እነዚህ ገፀ-ባህሪያት ፣ የጌሙ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ቢሆንም ፣ ከፍተኛ ምድብ ላይ የሚገኙ ገፀ-ባህሪያትን ማስከፈት ካልቻሉ ብቻ ይጠቀሟቸው።  

  • ፓም (Pam) - (ልዩ ገፀ-ባህሪ) 

  • ኤል-ኮስቶ (El Costo) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ማቪስ (Mavis) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ኤል-ታይገር (El Tigre) (Rare) 

ምድብ ዲ (Tier D) 

በዚህ ምድብ የሚገኙ ገፀ-ባህሪያት ፣ እጅግ ደካማ በመሆናቸው ፥ በተቻለ መጠን ባይጠቀሟቸው ይመከራል። 

  • ችክን (Chicken) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

  • ጎብሊን (Goblin) - (መደበኛ ገፀ-ባህሪ) 

የምድብ ደረጃ ዝርዝሮቹን እንዴት በአግባቡ መጠቀም ይቻላል 

የጨዋታው መጀመሪያ፡-  የምድብ ኤስ (Tier S) እና የምድብ ኤስ (Tier A) ገፀ-ባህሪዎችን መስከፈት እና ማሻሻል ላይ ያተኩሩ። 

የጨዋታው መኃል፡- ቡድንዎ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት ምድብ ቢ (Tier B) ውስጥ ያሉ ገፀ-ባህሪዎችን ይሞክሩ። 

የጨዋታው መጨረሻ፡- ምድብ ኤስ እና ኤ (Tier S & A) ገፀ-ባህሪዎችን በመጠቀም ስልቶትን ያጠናክሩ ፥ እንደ አስፈላጊነቱም የምድብ ቢ (Tier B) ገፀ-ባህሪዎችን ለተመረጡ ሚናዎች ይጠቀሙ። 

እነዚህ የምድብ ዝርዝሮችን በአግባቡ እና አስፈላጊ ሁኔታዎች ላይ በመጠቀም፣ ስኳድ በስተርስ (Squad Busters) ላይ ውጤታማ መሆን ይችላሉ ፥ መልካም ዕድል! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !