
በክላሽ ኦፍ ክላንስ (Clash of Clans) ፣ ክላሽ ሮያል (Clash Royale) እና ብራውል ስታርስ (Brawl Stars) አስደናቂ ስኬትን ያገኘው ሱፐርሴል (Supercell) ፣ አሁን ደግሞ ስኳድ በስተርስን (Squad Busters) ይዞ የመጣ ሲሆን ፥ ይህ አዲስ ጌምም ፣ ብራውል ስታርስ (Brawl Stars) ላይ የምናቃትን ሸሊን (Shelly) እና የክላሽ ኦፍ ክላንስ (Clash of Clans) ንግስትን አርቸር ክዊን (Archer Queen) በውስጡ አካቷል።
ስኳድ በስተርስ አስደናቂ ውጊያዎችን ፣ አዝናኝ እና አስደሳች የሆኑ ነገሮችን ይዞ እየመጣ ሲሆን ፣ ከዚህ ቀጥሎ ስለ ስኳድ በስተርስ መተግበሪያ ማወቅ ያለብዎ ጉዳዮችን እና ለምን ህጋዊ ከሆኑ ድረ-ገፆች ብቻ ማውረድ እንዳለብዎ በዝርዝር እናያለን።
ኤፒኬ ፋይል የአንድሮይድ (Android) ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ፣ መተግበሪያዎችን ለመጫን እና ለማሰራጨት የሚያገለግል የፋይል ዓይነት ሲሆን ፣ መተግበሪያው በአግባቡ እንዲሰራ የሚረዱ እና አስፈላጊ የሆኑ ፥ የመተግበሪያው ኮዶችን ፣ ግብዓቶችን እና የሚዲያ ፋይሎችን በውስጡ ይይዛል።
ተጫዋቾች አዲሱን የስኳድ በስተርስ ጌም ኤፒኬ ፋይል (APK File) አንድሮይድ እና አይፎን ስልካቸው ላይ ማውረድ እና መጠቀም ይችሉ እንደሆን በተደጋጋሚ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ኤፒኬ ፋይሎችን ማውረድ ጥንቃቄን የሚሻ ጉዳይ ሲሆን ፣ ህጋዊ ካልሆኑ ምንጮች ኤፒኬ ፋይሎችን ማውረድ የማንኛውንም የሞባይል ጌሞች እና የስኳድ በስተርስን ህግ እና ደንብ የሚጥስ ጉዳይ ነው።
ህጋዊ ያልሆኑ ኤፒኬዎች የሚያመጡት አደጋ፡-
የጨዋታ ህግ ጥሰት፡- ፈቃድ የሌላቸው ወይም ህጋዊ ያልሆኑ ስሪቶችን መጠቀም ፣ ከጨዋታው ሊያሳግድዎ ይችላል።
የደህንነት አደጋ፡- ፈቃድ የሌላቸው ወይም ህጋዊ ያልሆኑ ኤፒኬዎችን መጠቀም ፣ የስልክዎን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቫይረሶች (Malwares) በውስጣቸው ሊይዙ ይችላሉ።
ስኳድ በስተርስን (Squad Busters) ህጋዊ እና አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ ለመጫወት ፣ ህጋዊ ከሆኑ የአንድሮይድ እና የአይኦኤስ መተግበሪያ መደብሮች ብቻ እንዲያወርዱ በጥብቅ ይመከራል።
የስኳድ በስተርስ መተግበሪያን ከህጋዊ ምንጮች ለማውረድ የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፡-
ለአንድሮይድ፡
ጎግል ፕሌይ ስቶር (Google Play Store)፡- አንድሮይድ ላይ ስኳድ በስተርስን ለማውረድ አስተማማኙ እና ቀጥተኛው መንገድ ጎግል ፕሌይ ስቶር ሲሆን፦
ጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ Squad Busters ብለው በመፈለግ ፣ ቀጥታ ማውረድ
ስኳድ በስተርስን ማውረጃ ፡ የጎግል ፕሌይ ስቶር ማስፈንጠሪያን በመጠቀም ጌሙን ማውረድ ይችላሉ።
የሱፐርሴል ህጋዊ ድረ-ገጽ (Supercell’s Website)፡- ጌሙን ማውረድ የሚያስችልዎ ማስፈንጠሪያ ወይም ተጨማሪ መረጃዎችን ፣ የሱፐርሴል ድረ-ገፅ ላይ ያገኛሉ።
ለአይፎን (iOS)፡
አፕል አፕ ስቶር (Apple App Store)፡- አይፎን ላይ ስኳድ በስተርስን ለማውረድ አስተማማኙ እና ቀጥተኛው መንገድ አፕል አፕ ስቶር ሲሆን፦
ጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ Squad Busters ብለው በመፈለግ ፣ ቀጥታ ማውረድ
ስኳድ በስተርስን ማውረጃ ፡ የአፕል ስቶር ማስፈንጠሪያን በመጠቀም ጌሙን ማውረድ ይችላሉ።
የሱፐርሴል ህጋዊ ድረ-ገጽ (Supercell’s Website)፡- የሱፐርሴል ድረ-ገፅን በመጎብኘት ፥ ጌሙን ማውረድ የሚያስችልዎ ማስፈንጠሪያ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ያገኛሉ።
ከላይ የተቀመጡትን ህጋዊ ምንጮች በመጠቀም ፣ ደህንነቱ በተጠበቀ እና ህጋዊ በሆነ መንገድ በማውረድ ፥ ተያያዥ አደጋዎችን ማስወገድ ይችላሉ። መልካም ጨዋታ!