icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ካውንተር ስትራይክ 2 (Counter-Strike 2) ላይ የሚገኙ ምስጢራዊ ኮዶች 

ካውንተር ስትርይክ 2 (Counter-Strike 2) በመጀመሪያው ሰው ዕይታ ዘውግ ፈር ቀዳጅ ሲሆን ፣ CS2ም ይህንኑ የጨዋታ መንገድ መከተሉን ቀጥሏል። ይህ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ተጫዋቾች የሚጫወቱት ጌም ፣ እያንዳንዷ ሚሊሴኮንድ ልዩነትን ልትፈጥር ትችላለች። የSteam ምስጢራዊ ኮዶችን በመጠቀም የጨዋታ ተሞክሮዎን ይበልጥ ማሻሻል የሚችሉ ሲሆን ፥ ይህንንም ለማድረግ የሚያስችልዎ ቀላል መመሪያ ከዚህ ቀጥሎ አዘጋጅተናል፦ 

የስቲም (Steam) ምስጢራዊ ኮዶችን ማስተካከያ ሂደቶች 

  1. የስቲም ዝርዝርዎን ይክፈቱ። 

  1. Counter-Strike 2 ላይ ራይት ክሊክ በማድረግ ባህሪያትን ይምረጡ። 

  1. በመጨረሻ ፥ የመረጡትን ምስጢራዊ ኮድ በተሰጠው ማስገቢያ ላይ ያስገቡ። 

CS2 ላይ የሚገኙ ምርጥ ምስጢራዊ ኮዶች 

የሙከራ ስሪቱ ላይ የነበሩ የተወሰኑ ምስጢራዊ ኮዶች ፣ የካውንተር ስትራይክ 2 ነፃ ኦፊሺያል ስሪት ላይ ባይሰሩም  ፣  በርካታዎች አሁንም ትልቅ ጥቅም ይሰጣሉ፦ 

  • -console፡- ጌሙ ሲጀምር ምስጢራዊ ገፅን (developer console) ይከፍታል። 

ትዕዛዝ፦ -console 

ጥቅም፡- ምስጢራዊ ገፁን ጌሙ ውስጥ ትዕዛዞችን እና ማረሚያዎችን እንዲያደርግ ያስችለዋል። 

  • -high፡- ይህ ምስጢራዊ ኮድ ኮምፒውተርዎ CS2ን ማስኬድ ላይ የበለጠ እንዲያተኩር የሚያደርገው ሲሆን ፣ ፈጣን እና እንዳይቆራረጥ ያደርገዋል። ቀጥታ እያሰራጩ (Stream) እያደረጉ ከሆነ ይህንን ከመጠቀም ይቆጠቡ። 

ትዕዛዝ፦ -high 

ጥቅም፡- ኮምፒውተርዎ ለተሻለ አፈጻጸም ተጨማሪ የሲፒዩችን ለCS2 ይመድባል። ሆኖም ኮምፒዩተርዎ ላይ ያሉ ሌሎች ፕሮግራሞችን ሊያዘገይ ይችላል። 

  •  +fps_max 0፡- ይህ ምስጢራዊ ኮድ ኮምፒውተርዎ በሚችለው ፍጥነት እና አቅም ጨዋታውን እንዲያካሂድ ያስችላል። 

ትዕዛዝ: +fps_max 0 

ጥቅም፡- የፍሬም ፍጥነቱን እንዳይገደብ የሚያደርግ ሲሆን ፣ ሌሎች የአፈጻጸም ችግሮች እንዳይከሰቱ በጥንቃቄ ይጠቀሙ። 

  • -nojoy፦ ጆይ-ስቲኮችን ከስራ ውጭ በማድረግ ፣ የጌሙን አፈፃፀም እና የጨዋታውን ቅልጥፍና ያሻሽላል። 

ትዕዛዝ፦  -nojoy 

ጥቅም፡- ጆይ-ስቲኮችን (Gamepad Support) ከስራ ውጭ በማድረግ ፣ የትዕዛዞች መዘግየትን በማስወገድ ፣      የጨዋታውን ቅልጥፍና ያሻሽላል። 

  • -novid: የመግቢያ ቪዲዮውን በማሳለፍ ፣ ቀጥታ ወደ ጨዋታው ይወስዳል 

ትዕዛዝ፦ -novid 

ጥቅም፡- ጨዋታው ሲጀምር የመግቢያ ቪዲዮውን በማሳለፍ ፣ ጊዜን መቆጠብ ያስችላል። 

  • -softparticlesdefaultoff" ፦ አንዳንድ አነስተኛ የምስል ውጤቶችን በማስወገድ ፣ ጌሙ ፈጣን እና ያለመቆራረጥ እንዲሄድ ያስችለዋል። 

ትዕዛዝ፦ -softparticlesdefaultoff 

ጥቅም፡- የተወሰኑ አነስተኛ የዕይታ ውጤቶችን (Soft Particles) በማስወገድ ፣ የጌሙን አፈፃፀም ያሻሽላል። 

  • +violence_hblood 0፡- የደም ነክ የምስል ውጤቶችን በመቀነስ ፣ ጌሙ ፈጣን እና ያለመቆራረጥ እንዲሄድ ያስችለዋል። 

ትዕዛዝ፡ +violence_hblood 0 

ጥቅም፡- ንጹህ ዕይታን ለመፍጠር ደም ነክ የምስል ውጤቶችን በመቀነስ ፣ ግልጽ የምስል ጥራት እና የተሻለ የጌም ተሞክሮ ለመፍጠር ያስችላል። 

ጊዜ ያለፈባቸው እና በሙከራ ሂደት ላይ ያሉ ምስጢራዊ ኮዶች 

እንደ -fullscreen እና -freq ያሉ አንዳንድ የቆዩ ምስጢራዊ ኮዶች የCS2 አዲስ ስሪት ላይ የማይሰሩ ሲሆን ፥ የ -tickrate ውጤታማነት በተመለከተ ተጨማሪ ሙከራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነው። 

እነዚህን የካውንተር ስትራይክ 2 ምስጢራዊ ኮዶች እንዴት በአግባቡ መጠቀም ይቻላል? 

እነዚህን የካውንተር ስትራይክ 2 ምስጢራዊ ኮዶች ሁሉም ሰው መጠቀም የሚችል ሲሆን ፥ አዲስ ተጫዋችም ይሁኑ ፣ ባለ ልምድ እነዚህን ምስጢራዊ ኮዶች በመጠቀም ፉክክር በበዛበት የካውንተር ስትራይክ ዓለም ላይ ፣ የጨዋታ ልምድዎን ወይም የአፈጻጸም ብቃትዎን ማሻሻል ይችላሉ። 

ስለካውንተር ስትራይክ 2 የበለጠ መረጃ እና ዝርዝር መመሪያዎችን ለማግኘት ፣ Breakflipን ይጎብኙ። Breakflip ገፅ ላይ ጠቃሚ ምክሮችን ፣ መረጃዎችን ፣ ምስጢራዊ ኮዶችን ፣ ሰርቨር ጥገና እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !