icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የካውንተር ስትራይክ-2 የሰኔ 25 ፣ 2024 ዝማኔ 

በአዲሱ ካውንተር ስትራይክ 2 የሰኔ 25፣ 2024 ዝማኔ ላይ የተካተቱ አዳዲስ ባህሪያት እና ማሻሻያዎች እንደሚከተለው ናቸው፦ 

የካርታ ለውጦች 

በተጨዋቾች የተሰሩ ካርታዎች 

አዲስ የተካተቱ ካርታዎች፡- 

  • ቴራ እና ሚልስ፡ በኮምፕታቲቭ ፣ ካዥዋል እና በዴዝ ማች ሞድ። 

  • መሜንቶ እና አሴምብሊ፡ በዊንግ-ማን ሞድ። 

  • ፑል ደይ፡ በአርሚ ሬስ ሞድ። 

በነባር ካርታዎች ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎች፡- 

  • ኑክ፦ የሲ4 ቦምብ ማጣበቂያ ቦታዎች። 

  • ኤኒሸንት፡- የሲ4 ቦምብ ማጣበቂያ ቦታዎች ፣ ጉድጓዶች እና ሌሎች ጥቃቅን ችግሮች። 

  • ቨርቲጎ፦ የሲ4 ቦምብ ማጣበቂያ ቦታዎች እና ሌሎች ጥቃቅን ጉዳዮች። 

  • አኑቢስ፡- የእጅ ቦምብ ግጭቶች እና ሌሎች ጥቃቅን ጉዳዮች። 

የገፅታ ለውጦች፦ 

  • በሁሉም የጨዋታ ሞዶች ላይ የMVP (የመሪ ተጫዋቾች) ክፍል ዘምኗል። 

  • ለልዩ ፕሪሚየር ግጥሚያዎች አዲስ ባለተንቀሳቃሽ ምስል MVP ክፍሎች ተጨምረዋል። 

  • MVP መሆን የሚያስችሉ የነበሩ ህጎች ተለውጠዋል። 

የጨዋታ ለውጦች፦ 

ከዚህ በኋላ በእያንዳንዱ ካርታ ያለዎት የችሎታ ደረጃ ፣ ሁለት ግጥሚያዎችን ካሸነፉ በኋላ የሚታይ ይሆናል። 

የቪዲዮ መቼት ለውጦች፥- 

ጠቃሚ ምክሮች፡- 

  • የስክሪንዎ ምስሎችን የማደስ ፍጥነት ከፍተኛ ላይ ካልሆነ ፥ ይህን እንዲያስተካክሉ ጌሙ ጥቆማ ይሰጣል። 

  • ጌሙ ያለምንም እክል እንዲካሄድ የሚያስችል የNVIDIA G-Sync ቴክኖሎጂ ኮምፒውተርዎ ላይ ኖሮ ሆኖም ግን ካላበሩት ፥ እንዲያበሩት ጌሙ ጥቆማ ይሰጣል።። 

  • G-Sync በርቶ ነገር ግን ፣ V-Sync እና NVIDIA Reflex መቼቶች ካልበሩ ፣ እንዲያበሯቸው ጌሙ ጥቆማ ይሰጣል።። 

ሌሎች ለውጦች፡- 

  • በዋናው ማውጫ ላይ ይገኙ የነበሩ ፥ የበስተጀርባ ምስሎችን መቀየሪያ እና መሳሪያዎችን አገላብጦ መፈተሻ አማራጮች ፥ እንዲቀሩ ተደርገዋል። 

  • ከዚህ በኋላ ፣ ስክሪንዎ በምን ያህል ፍጥነት ምስሎችን እንደሚያድስ ያሳየዎታል።  

  • የላፕቶፖች ሃይል መቆጠቢያ አማራጭ እንዲቀር ተደርጓል። 

  • G-Sync መብራቱን የሚያሳይ ክፍል ተጨምሯል። 

  • በጌሙ እና በማውጫው ላይ FPSን መቆጣጠሪያ ተንሸራታች ተጨምሯል። 

  • በማውጫ ውስጥ ያለውን ነባር የFPS ገደብ ከ120 ወደ 200 እንዲጨመር ተደርጓል። 

  • የምስል መቼቶችን ሲያስተካክሉ ፣ ቅድመ እይታው ጨዋታውን ሲጫወቱ ከሚያዩት ጋር አንድ አይነት እንዲሆን ተደርጓል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !