icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የNBA 2K24 ፋይል መጠን እና ተጫዋቾችን ያበሳጨው ጉዳይ 

ከመውጣቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የNBA 2K24 ፋይል መጠን የተገለጸ ሲሆን ፣ የፋይን መጠኑም በቪዲዮ ጌሞች ታሪክ ሁኖ የማያውቅ መሆኑ ፣ በተጨዋቾች ዘንድ ግርታን እና ንዴትን ፈጥሯል።  

እ.ኤ.አ መስከረም 8 ፣ 2023 ለጨዋታ የበቃው NBA 2K24 ፣ በተጨዋቾች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ጌም ነው። ሆኖም ጌሙን ፕለይ ስቴሽን 5 ፣ ኤክስ-ቦክስ X|S ፣ ወይም ኮምፒውተርዎ ላይ ለመጫን ሃርድ ድራይቭ ላይ ከፍተኛ የሚባል መጫኛ ቦታን የሚጠይቅ ሆኖ ተገኝቷል።  

NBA 2K24 ወደ 161 ጂ.ቢ የሚጠጋ ቦታን እንደሚፈልግ መረጃ ወጥቷል።  ይህንንም ቁጥር ለማነጻጸር ያመች ዘንድ ፥ የፕለይስቴሽን 5 የመያዝ አቅም 825 ጂ.ቢ  ነው። ይህም የማከማቻ ቦታውን ወደ ሩብ የሚጠጋ ቦታ ይይዛል ማለት ነው። የዚህም መረጃ የኤክስ-ቦክስ መደብር ላይ መታየት ተጫዋቾችን ግራ አጋብቷል ፣ ሆኖም ግን ይህ መረጃ ሙሉ ለሙሉ እውነተኛ አይደለም። 

NBA 2K24 161 ጂቢ የሃርድ ድራይቭ ቦታን እንደሚጠይቅ የወጣው መረጃ ግምት ሲሆን ፣ መሬት የወረደው እውነታ ግን ከዛ ያነሰ መጠን እንደሚሆን ነው። የዚህ ግምት መነሻም ፥ በጊዜ ሂደት ጌሙ ላይ የሚጨመሩ ማስፋፊያዎችን ፣ ማሻሻያዎችን ፣ ተጨማሪ ይዘቶችን ፣ ዝማኔዎችን መሰረት አድርጎ በመጪዎቹ ዓመታት ሊኖረው ስለሚችል የፋይል መጠን በአዘጋጆቹ የተደረገ ትንበያ ነው። 

በጣም ትልቅ ቦታን ከሚጠይቁ ጌሞች መካከል ፣ ኮል ኦፍ ዲውቲ ወደ 230 ጂቢ ፣ ሬድ ዴድ ሪደምፕሽን II እና ጂቲኤ 5 ደግሞ ኮምፒውተር ላይ ከ100 ጂቢ የሚበልጥ ቦታን ይይዛሉ። ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ፣ በኔንቲዶው መድረክ ላይ የሚገኙ ፣ እንደ ዜልዳ፡ ቲርስ ኦፍ ዘ ኪንግደም ያሉ ጌሞች ስዊች ላይ ብቻ የሚገኙ በመሆናቸው 15 ጂ.ቢ የበለጠ ቦታን አይጠይቁም። ይህም በቀላሉ መጫን እንዲቻል እና ክፍት የሃርድ ድራይቭ ቦታን ለሌሎች ጌሞች ለመጠቀም ያስችላል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !