icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

NBA 2K24ን ላይ ሊቀላቀሏቸው የሚገቡ ምርጥ ቡድኖች 

ምርጥ አሰላለፎች 

ተከላካይ (PG) 

ቦስተን ሴልቲክስ 

  • አሰላለፍ፡- ዴሪክ ዋይት ፣ ጄይለን ብራውን ፣ ጄይሰን ታተም ፣ ክሪስታፕስ ፖርዚንግስ ፣ አል ሆርፎርድ 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፡- የታተም ፣ ብራውን እና ፖርዚንግስን ብቃት በአግባቡ ለመጠቀም ፥ ስልታዊ ጨዋታን መፍጠር የሚችል ጠንካራ ተከላካይ (PG) ያሰልፉ። 

ማያሚ ሂት 

  • አሰላለፍ፡- ታይለር ሂሮ ፣ ጆሽ ሪቻርድሰን ፣ ጂሚ በትለር ፣ ኬቨን ላቭ ፣ ባም አዴባዮ 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፡- ጎሎችን በማስቆጠር የታይለር ሂሮን ክፍተት መሸፈን የሚችል ፥ እና ስልታዊ ጨዋታን መፍጠር የሚችል ጠንካራ ተከላካይ (PG) ያሰልፉ። 

ኒው ኦርሊንስ ፔሊከንስ 

  • አሰላለፍ፡- ሲጄ ማኮለም ፣ ኸርበርት ጆንስ ፣ ብራንደን ኢንግራም ፣ ዛዮን ዊሊያምሰን ፣ ዮናስ ቫላንቺናስ 

  • ጠቃሚ ነጥብ፡- ኢንግራም እና ዊሊያምሰን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል እና ስልታዊ ጨዋታን መፍጠር የሚችል ጠንካራ ተከላካይ (PG) ያሰልፉ። 

አጥቂ ተከላካይ (SG) 

ሚልዎኪ በክስ 

  • አሰላለፍ፡- ጁሩ ሆሊዳይ ፣ ግሬሰን አለን ፣ ክሪስ ሚድልተን ፣ ያኒስ አንቲቶኮዎምቦ ፣ ብሩክ ሎፔዝ 

  • ጠቃሚ ነጥብ፦ ጥሩ ኳስ አከፋፋይ እና ባለ ሶስት ነጥብ ጎሎችን ማስቆጠር የሚችል ጎበዝ አጥቂ ተከላካይ ማካተት ለዚህ አሰላለፍ ይመከራል። 

ዴንቨር ነጌትስ 

  • አሰላለፍ፡- ጀማል ሙሬይ ፣ ኬንታቪየስ ካልድዌል-ፖፕ ፣ ሚካኤል ፖርተር ጁኒየር ፣ አሮን ጎርደን ፣ ኒኮላ ጆኪች 

  • ጠቃሚ ነጥብ፦ በጥሩ ሁኔታ ኳስን መወርወር እና መከላከል የሚችል አጥቂ ተከላካይ በማሰለፍ የቡድኑን ክፍተት መሸፈን ይቻላል። 

ሻርሎት ሆርኔትስ 

  • አሰላለፍ፡- ላሜሎ ቦል ፣ ቴሪ ሮዚየር ፣ ብራንደን ሚለር ፣ ፒ.ጄ. ዋሽንግተን ፣ ማርክ ዊሊያምስ 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፡- ውጤታማ የጨዋታ ስልቶችን መፍጠር እና የመከላከል ብቃት ያለው አጥቂ ተከላካይ ማሰለፍ ሆርኔትቶችን ለድል ሊያበቃ ይችላል። 

አጥቂ አማካኝ (SF) 

ፊኒክስ ሰንስ 

  • አሰላለፍ፡- ብራድሊ ቤል ፣ ዴቭን ቡከር ፣ ጆሽ ኦኮጊ ፣ ኬቨን ዱራንት ፣ ዴአንድሬ አይቶን 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፡- ጥሩ የመከላከል ብቃት እና ውጤታማ የጨዋታ ስልቶችን መፍጠር የሚችል አጥቂ አማካኝ በማሰለፍ ፣ የፊኒክስ ሰንስን ጎል አስቆጣሪነት መጨመር ይቻላል። 

ሳክራሜንቶ ኪንግስ 

  • አሰላለፍ፡- ዲ`አሮን ፎክስ ፣ ኬቨን ወርተር ፣ ሃሪሰን ባርነስ ፣ ኪጋን ሙሬይ ፣ ዶማንታስ ሳቦኒስ 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፦ መከላከል እና ባለ ሶስት ነጥብ ግብን ማስቆጠር የሚችል ፣ አጥቂ አማካኝን በማሰለፍ ፣ የሃሪሰን ባርንስን ቦታ መሽፈን እና ቡድኑን ለድል ማብቃት ይቻላል። 

ሚኒሶታ ቲምበርዎልቭስ 

  • አሰላለፍ፡- ማይክ ኮንሊ ፣ አንቶኒ ኤድዋርድስ ፣ ጄደን ማክዳንኤል ፣ ካርል-አንቶኒ ታውንስ ፣ ሩዲ ጎበርት 

  • ጠቃሚ ምክር፡- ሁለገብ አጥቂ አማካኝ በማሰለፍ ፣ የቡድኑን አቅም ማጎልበት ይቻላል። 

አጥቂ (PF) 

ፊላዴልፊያ 76ርስ 

  • የመነሻ አሰላለፍ፡- ጄምስ ሃርደን ፣ ታይሪስ ማክሲ ፣ ቶቢያስ ሃሪስ ፣ ፒ.ጄ. ተከር ፣ ጆኤል ኢምቢድ 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፡- መከላከል እና ጥሩ ውርወራዎችን ማድረግ የሚችል አጥቂን በማሰልፍ ፥ የቡድኑን የማጥቃት እና የመከላከል አቅም መጨመር ይቻላል። 

ኦክላሆማ ሲቲ ተንደር 

  • የመነሻ አሰላለፍ፡- ሻይ ጊልጅየስ ፣ ጆሽ ጊዲ ፣ ሉጌንትዝ ዶርት ፣ ጄለን ዊሊያምስ ፣ ቸት ሆለምግሪን 

  • ጠቃሚ ምክር፡ መከላከል እና ጥሩ ውርወራዎችን ማድረግ የሚችል አጥቂን ማሰልፍ ፥ የቡድኑን ጥሎ የማለፍ ዕድል ይጨምራል። 

አትላንታ ሃውክስ 

  • አሰላለፍ፡- ትሬይ ያንግ ፣ ዲጆንቴ ሙራይ ፣ ዲ`አንድሬ ሃንተር ፣ ሳዲቅ ቤይ ፣ ክሊንት ካፔላ 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፡- ጠንካራ አጥቂ ተከላካይ ማሰለፍ ፣ የቡድኑን የመከላከል አቅም ይጨምራል። 

መሃል (C) 

ሎስ አንጀለስ ሌከርስ 

  • አሰላለፍ፡- ዲ`አንጄሎ ረስል ፣ ኦስቲን ሪቭስ ፣ ሌብሮን ጀምስ ፣ ጃሬድ ቫንደርቢልት ፣ አንቶኒ ዴቪስ 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፡- አንቶኒ ዴቪስን ለመደገፍ የአማካኝ ተከላካይ ቦታን ይዘው ይጫወቱ። 

ጎልደን ስቴት ዎርየርስ 

  • አሰላለፍ፡- ክሪስ ፖል ፣ ስቴፈን ከሪ ፣ ክሌይ ቶምፕሰን ፣ አንድሪው ዊግንስ ፣ ድሬይሞንድ ግሬን 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፦ ጠንካራ መሃል ተጫዋች በማሰለፍ ፣ ድሬይመንድ ግሪንን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል 

ዳላስ ማቭሪክስ 

  • አሰላለፍ፡- ሉካ ዶንሲች ፣ ካይሪ ኤርቪንግ ፣ ቲም ሃርዳዌይ ጁኒየር ፣ ግራንት ዊሊያምስ ፣ ድዋይት ፓውል 

  • ጠቃሚ ነጥቦች፦ ሁለገብ መሃል ተጫዋች በማሰለፍ ፣ የዶንሲክን እና ኤርቪንግን ውጤታማ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ፣ የቡድኑን አጠቃላይ ብቃት ማረጋገጥ ይቻላል። 

ይህ መመሪያ የሚጫወቱበትን ቦታ መሰረት አድርጎ ፣ መቀላቀል የሚችሏቸውን ምርጥ ቡድኖች ቀለል ባለ ሁኔታ ይተነትናል። ለተሻለ ውጤት ፣ የእያንዳንዱ ቡድን ጥንካሬ እና ድክመቶች ከእርስዎ አጨዋወት ጋር እንዴት እንደሚስማማ ጊዜ ወስደው ይለዩ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !