
አዲሱ የ NBA 2K24 ስሪት ተጫዋቾችን ይበልጥ የሚያስደስቱ እና የሚያዝናኑ አስደሳች ለውጦችን እና ማሻሻያዎችን ይዞ የመጣ ሲሆን ፣ በዚህ አዲስ ምዕራፍ ፣ ተጫዋቾች ልዩ ልዩ ሽልማቶች እና አዳዲስ ደረጃ ማሳደጊያ አማራጭ የሚያገኙባቸው መንገዶች ተካተዋልል።
በተጨማሪም ፣ የMyTEAM እና MyCAREER ሂደቶች የተዋሃዱ ሲሆን ፥ ይህም ተጫዋቾች በትጋት ያገኟቸውን ሽልማቶች ሳያጡ ሞዶችን እንደልባቸው እንዲቀያይሩ ያስችላቸዋል።
አዳዲስ የምዕራፍ ማለፊያ ትኬቶች፡- ከነባር ሽልማቶች በተጨማሪ ፣`ፕሮ እና ሆል ኦፍ ፌም` (Pro and Hall of Fame) የተባሉ ሁለት ልዩ የምዕራፍ ማለፊያ ትኬቶችን ይዞ መጥቷል። እነዚህ ትኬቶች የተጨዋቾችን የበጀት እና የፍላጎት ደረጃዎች ማሟላት እንዲችሉ እና ሽልማት የማግኘት ዕድልን ከፍ እንዲያደርጉ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው።
ነፃ ማለፊያ፡- እስከ 80 የሚደርሱ ሽልማቶችን የሚያስገኙ እና ተጨማሪ ወጪ ሳያወጡ ጌሙን ማጣጣም ለሚፈልጉ ተጫዋቾች የተዘጋጀ።
ፕሮ ማለፊያ (9.99 ዩሮ)፦ 40 ተጨማሪ ፕሪሚየም ሽልማቶች እና ተጨማሪ የቨርቹዋል ምንዛሬ (VC) እና የቡድን ነጥቦች (MTP) ጉርሻዎችን የሚያስገኝ ሲሆን ፣ ተጨማሪ ሽልማቶችን በማግኘት መንበሽበሽ ለሚፈልጉ ተጫዋቾች የተዘጋጀ አማራጭ ነው።
ሆል ኦፍ ፌም (€19.99)፦ ፕሮ ማለፊያ ላይ የሚገኙ ሁሉም ጥቅሞችን የሚያካትት ፣ እንዲሁም የ15% XP ጭማሪ እና 10 ደረጃ መሸጋገሪያዎችን የሚያቀርብ ሲሆን ፣ ከፍተኛውን ሽልማቶችን እስከጥግ ድረስ ማግኘት ለሚፈልጉ የጌሙ አፍቃሪያን የተዘጋጀ አማራጭ ነው።
የNBA 2K24 አዘጋጆች ተጫዋቾች ለጌሙ የሚሰጡትን ሰዓት እና የሚያደርጉትን ጥረት ትኩረት ሰጥተው የሚመለከቱን ጉዳይ ሲሆን ፣ ተጫዋቾን በሜዳ ላይ ለሚያጠፉት እያንዳንዷ ደቂቃ በየቨርቹዋል ምንዛሬ (VC) እና የቡድን ነጥቦች (MTP) ወይም በልዩ ልዩ ሽልማቶች የሚካሱ ይሆናል። እነዚህ ማሻሻያዎች ጌሙ ይበልጥ መሳጭ እንዲሆን እና የተጫዋችን ተሳትፎ እና ትጋት የመካስ ግልፅ አላማ እንዳላቸው ያሳያል።