
ፎርትናይት በሚያደርጋቸው እያንዳንዱ ዝመናዎች ፥ የተለያዩ ዓለማትን የሚወክሉ እጅግ ብዙ እና አዳዲስ ገፀ-ባህሪዎችን በማካተት ተጫዋቾቹን ማስደነቁን ቀጥሏል። እንደተለመደው በምዕራፍ 5 ክፍል 3ም ፣ ብዙ አዳዲስ ገፀ-ባህሪዎችን እና ማጌጫዎችን ያካተተ ሲሆን ፣ ሰኔ 22 ላይ በለቀቀው ዝመናም ለተጫዋቾች ይበልጥ አጓጊ የሆኑ ይዘቶችን ይዞ መጥቷል።
ክፍል 3 ስሪት 30.20 ላይ የተካተቱ አዳዲስ ገፀ-ባህሪዎች
እያንዳንዱ የፎርትናይት አዲስ ዝመናዎች ፣ አዳዲስ ገፀ-ባህሪዎችን ይዘው እንደሚመጡ የታወቀ ሲሆን ፣ ሰኔ 22 ላይ የተለቀቀው ስሪት 30.20ም ያካተታቸውን ገፀ-ባህሪያትንም ፣ ታዋቂው መረጃ አቀባይ ShiinaBR እንደሚከተለው አስቀምጧል፡-
ጃክ ስፓሮው (Jack Sparrow)
እርጉሙ ጃክ ስፓሮው (Cursed Jack Sparrow)
ካፕቴን ባርቦሳ (Captain Barbossa)
ዴቪ ጆንስ (Davy Jones)
ኤልዛቤት ስዋን (Elizabeth Swann)
ሻምፒዮን ስፓርክ-ፕለግ (Champion Sparkplug)
ጆይ ካሊየንቴ (Joey Caliente)
ፐርሰፎን (Persephone)
ሴፍቲ ስቲቭ (Safety Steve)
ሳስኪያ (Saskia)
ቫጋቦንድ (The Vagabond)
ከእነዚህ ገፀ-ባህሪዎች በተጨማሪ ፣ ቮልት ቦይ ቦብልሄድ እና ፓይሬትስ ኦፍ ዘ ካሪቢያን ጋር ሽርክና በመፍጠር የተዘጋጁ የተለያዩ ማጌጫዎችም ተካተዋል። ለበለጠ መረጃ ፥ ShiinaBR ስለ ዝመናው በዝርዝር የሚዳሰስበትን ቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።
እንደ ቫጋቦንድ ያሉ አንዳንድ አዳዲስ ገፀ-ባህሪዎች NPCs ሊሆኑ እንደሚችሉ ልብ ማለት የሚያስፈልግ ሲሆን ፥ በተጨማሪም በጌሙ መደብር ውስጥ በጥቅል መልክ ከሚገኙት ጃክ ስፓሮው እና እርጉሙ ጃክ ስፓሮው ገፀ-ባህሪዎች በስተቀር ፣ ሌሎቹ የፓይሬትስ ኦፍ ዘ ካሪቢያን ገፀ-ባህሪዎችም NPC ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል።
ለማስታወስ ያህል ፣ ፎርትናይት በኢፒክ ጌምስ አዘጋጅነት የታተመ የባትል ሮያል ጌም ሲሆን ፣ በዓለም ዙሪያ እጅግ በርካታ ተጫዋቾች ካላቸው እና ትርፋማ ከሆኑ ጌሞች መካከል አንዱም ነው። ጌሙ በነፃ የቀረበ ሲሆን ፣ አዘጋጆቹ በገፀ-ባህሪዎች እና ማጌጫዎች ሽያጮች የሚጠቀሙ ሲሆን ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ደግሞ.በግብዣ ኮዶች አማካኝነት ይጠቀማሉ።