
በ`ከርሰድ ሴልስ` ዝማኔ ፓይሬትስ ኦፍ ዘ ካሪቢያን ፎርትናይት ላይ የተካተተ ሲሆን ፣ ይሄን ተከትሎ ተጫዋቾች እንደ ሽፕሬክ ሻሎ ያሉ አዳዲስ አካባቢዎችን ማሰስ እና የተደበቁ ውድ ሀብቶችን ማግኘት ይችላሉ። `ከርሰድ ሴልስ` ፓይሬትስ ኦፍ ዘ ካሪቢያንን መሰረት ያደረጉ ልዩ ልዩ ተልዕኮዎችን ፣ እና ሽልማቶችን ለተጫዋቾች አዘጋጅቷል።
የከርሰድ ሴልስ ማለፊያ ነፃ እና የክፍያ እቃዎችን የሚያቀርብ ሲሆን ፣ እንደ ጃክ ስፓሮው ሰይፍ እና የሽልማት ቦርሳን በነፃ የሚያቀርብ ሲሆን ፣ ፕሪሚየሙን በመግዛት የጃክ ስፓሮው አልባሳትንም ማስከፈት ይቻላል።
ዝመናው አዳዲስ የመጓጓዣ ዘዴዎችን ይዞ የመጣ ሲሆን ፣ የጠርሙስ ውስጥ መርከቦችን በመጠቀም ያለ ኮሽታ ጠላቶችን ማጥቃት ወይም እራስዎን በፓይሬት መድፍ ረጅም ርቀት ማስወንጨፍ ይችላሉ። ይህም ይበልጥ ጨዋታው ይበልጥ እጅግ አዝናኝ እና አዲስ ገፅታ እንዲኖረው አድርጎታል!
በተጨማሪም ፣ የውድ ሃብቶች ካርታው የሚመለስ ሲሆን ፣ ይህም የተደበቁ ውድ ሃብቶችን እና ድጋሚ እንዲካተት የተደረገውን ፍሊንትሎክ ሽጉጥ እንዲያገኙ ያስችልዎታል።
የክርስድ ሴልስ ተልዕኮዎች
የተረገሙ ሳንቲሞችን ለማግኘት እና በክርስድ ሴልስ ማለፊያ ውስጥ ሽልማቶችን ለማስከፈት የባህር ውንብድና ተልዕኮዎችን ያጠናቅቁ። ተልዕኮዎች የሚለቀቁበት ቀናት፡-
ተልዕኮ 1፡- ተለቋል!
ተልዕኮ 2፡ ሐምሌ 14 በ3፡00 PM (CEST)
ተልዕኮ 3፡ ሐምሌ 16 በ3፡00 PM (CEST)
ተልዕኮ 4፡ ሐምሌ 18 በ3፡00 PM (CEST)
ተልዕኮ 5፡ ሐምሌ 20 በ3፡00 PM (CEST)
ተልዕኮ 6፡ ሐምሌ 22 በ3፡00 PM (CEST)
ተልዕኮ 7፡ ሐምሌ 24 በ3፡00 PM (CEST)
ተልዕኮ 8፡ ሐምሌ 26 በ3፡00 PM (CEST)
ሁሉንም ተልዕኮዎች በማጠናቀቅ የጃክ መርከብን ማብረሪያ ማስከፈት ይችላሉ።
የኤልዛቤት ስዋን ፣ ካፒቴን ባርቦሳ እና ዴቪ ጆንስ አልባሳት አሁን በመደብሩ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ፣ እያንዳንዱ ጥቅል የሌጎ ጭብጥ ያላቸው መለዋወጫዎችን እና መፍለጫን ያካትታሉ፡-
ኤሊዛቤት ስዋን ጥቅል፡- የኤልዛቤት ስዋን ልብስን ፣ የተረገመ የሽልማት ቦርሳን እና የኤልዛቤት መፍለጫን ያካትታል።
ካፒቴን ባርቦሳ ጥቅል፡- የካፒቴን ባርቦሳ ልብስን እና የባርቦሳ ሰይፍን ያካትታል።
የዴቪ ጆንስ ጥቅል፡ የዴቪ ጆንስ ልብስን ፣ የቤቢ ክራከ የሽልማት ቦርሳን እና የኖሪንግተንን የመስዋዕት ሰይፍን ያካትታል።