
በ30.30 ዝመና ቅጂ ላይ ፣ መረጃ ፈልፋዮች የፎል ጋይስ እና የፎርትናይት ሽርክና ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁም መረጃን አግኝተዋል። ከዚህ በፊት ስለዚህ ሽርክና የተገለፀ ነገር ባይኖርም ፣ ከጌሙ ፋይሎች ያገኙትን ቁልፍ መረጃዎች መረጃ ፈልፋዮች አጋርተዋል።
ፎርትናይትን እና ፎል ጋይስን በተመለከተ ለወራት ወሬዎች ሲናፈሱ የቆዩ ሲሆን ፣ ሆኖም ግን በይፋ ስለሚለቀቅበት ቀን በግልጽ የተባለ ነገር አልነበረም። አሁን ግን ሰዓቱ የደረሰ ይመስላል! ፣ በስተመጨረሻ ሐምሌ 23፣ 2024 የሚደረገው ዝማኔ ጋር እንደሚለቀቅ መረጃዎች አሳይተዋል። ፎል ጋይስ ራሱን የቻለ ሞድ ወይስ ፎርትናይት ውስጥ ይካተታል? የሚለው ጉዳይ ፣ አሁንም የብዙ ተጫዋቾች ጥያቄ እንደሆነ ነው።
እንደ ሃይፕ-ኤክስ ያሉ መረጃ ፈልፋዮችን ምስጋና ይግባ እና የፎል ጋይስ ሞድ ቀጥታ ባትል ሮያል ውስጥ እንደሚካተት ማረጋገጥ ተችሏል። ኢፒክ ጌምስ ፣ ፎርትናይት ላይ ልዩ ሞድን ሮያል ባትል ላይ ሲያካተት ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ይህ አዲስ ሞድ ላይ መሳተፍ ፣ ሽልማቶችን ማግኘት የሚያስችልዎ አነስተኛ ጌሞች ላይ መሳተፍ ያስችልዎታል። አነስተኛ ጌሞቹን በተጫወቱ እና ደረጃዎን ከፍ ባደረጉ ቁጥር ልዩ ሽልማቶችን የማግኘት ዕድልዎ ከፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ፣ የደረጃ ሠንጠረዦች ላይ መንጠላጠልም ያስችልዎታል።
አሁን ላይ ፣ ባትል ሮያል ውስጥ የፎል ጋይስ ሞድን እንዴት መቀላቀል እንደሚቻል የወጡ መረጃዎች ባይኖሩም ፥ ዝርዝር መረጃው እንደደረሰን ፣ በፍጥነት የምናሳውቅዎ ይሆናል።
በዚህ ሞድ ፣ እርሶ የሚጠቀሙት ገፀ-ባህሪ የፎርትናይት ገጽታውን ሳይለውጥ ወደ ፎል ጋይስ ቢን ይለወጣል። ሽልማቶችንም ለማግኘት ፣ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር የመሰናክል ውድድሮችን መወዳደር የሚጠበቅብዎ ሲሆን ፣ የሚያገኟቸው ሽልማቶችም ፣ በውድድሩ መጨረሻ ላይ በሚኖርዎ ደረጃ ላይ የሚመሰረቱ ይሆናሉ።
በተጨማሪም ፣ በእዚህ አነስተኛ ጌም ውስጥ ተልዕኮዎች የሚኖሩ ሲሆን ፥ መረጃ ፈልፋዮች እንደ ፎል ጋይስ መቆፈሪያ ፣ የሽልማት ቦርሳዎች እና የፎል ጋይስ ሙዚቃ ያሉ ሽልማቶች እንደሚኖሩም አሳውቀዋል። እነዚህ ሽልማቶች ነፃ እንደሚሆኑም የተነገረ በመሆኑ ፣ ይህን ዕድል መጠቀምዎን እንዳይረሱ!