
ኢፒክ ጌምስ ፣ ያለማቋረጥ እጂግ አስደናቂ የሆኑ ሽርክናዎችን እያመጣ እያመጣ ሲሆን ፣ ፎርትናይት ከዚህ በፊት ከዲዝኒ ጋር በመተባበር D23 አይላንድን ፣ ማርቭል ዱም ፣ እና ፎል ጋይስን ይዞ የመጣ ሲሆን ፣ አሁንም ታዋቂ ከሆኑ ብራንዶች ጋር ሽርክና በመፍጠር ተጫዋቾቹን ማስደነቁን ቀጥሏል።
በቅርቡም አንድ አስደሳች ወሬ እየተናፈሰ ይገኛል! Samleakss ከሲምፕሰንስ ጋር ሽርክና ሊኖር እንደሚችል በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ካሳወቀ ቆይታዎች በኋላ ፥ ታዋቂው የፎርትናይት መረጃ ፈልፋይ HypeX ፣ ከ 2 ሚሊዮን በላይ እይታን ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስተያየቶችን በያዘው ልጥፉ ፣ በቅርቡ የሲምፕሰንስ ገፀ-ባህሪያት የፎርትናይት የጦርነት አውድማን ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ አጋርቷል። ምንም እንኳን ከፎርትናይት እውነታነቱን የሚያረጋግጥ ፣ ስለሚለቀቀበት ቀን በይፋ የወጣ ዝርዝር መረጃ ባይኖርም ፣ ይህ ዜና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ ትኩረትን መሳብ እና በተጫዋቾች ዘንድ ጉጉትን አሳድሯል።
አንዳንድ የማህበረሰቡ አባላት ይህን መረጃ ትክክለኛነት እንደሚያጠራጥር ሃሳባቸውን የገለጹ ቢሆንም ፣ HypeX ታማኝ ምንጮቹ ያሉት እና አስተማማኝ መረጃዎችን በማቀበል እንደሚታወቅ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ሲቀጥል ፣ ትክክለኛነቱን ሳያረጋግጥ እንዲህ ያለ መረጃ በማጋራት በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን መልካም ስም አደጋ ላይ አይጥልም። በተጨማሪም ፎርትናይት ከዚህ ቀደም ሲምፕሰንስ ባለቤት ከሆነው ከዲዝኒ ጋር ከዚህ ቀደም ሽርክናን ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን ፣ ይህም የሚናፈሰውን ወሬ ይበልጥ አሳማኝ ያደርገዋል።
በዓለም ላይ ከሚገኙ በጣም ታዋቂ እና ተወዳጅ ከሆኑ ተከታታይ ፊልሞች ውስጥ አንዱ የሆነው ሲምፕሰንስ ፣ ፎርትናይት ላይ ገፀ-ባህሪያቱን በማካተት ተነክቶ የማያቅ ትልቅ ከፍታን መቆናጠጥ የሚችል ቢሆንም ፣ አሁን ላይ ግን በይፋ የወጡ ምንም መረጃዎች ባለመኖራቸው ፣ እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ያዳግታል። Samleakss በበኩሉ ይህ ዜና ማንነቱ ከማይታወቅ እና ከዚህ በፊት ዲዝኒ እና አቫታር ያደረጉትን የሽርክና ዜና ካቀበለ ፣ ምንጭ የመጣ መሆኑንም አሳውቋል።