
ተጫዋቾች ፎርትናይት ክሬቲቭ ሞድ ውስጥ የራሳቸውን ካርታ መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ፣ አልፎም ከሌሎች ጌም አዘጋጅ ድርጅቶች ጋር ትብብር በማድረግ ይሰራሉ። በቅርብ ጊዜ በተደረገው የፎል ጋይስ ዝማኔም (ስሪት 30.40) ፣ አዳዲስ የፎል ጋይስ ካርታዎች ወደ ፎርትናይት ኣንዲካተቱ ተደርጓል።
እነዚህ ፎል ጋይስን መሰረት አድርገው በተሰሩ ካርታዎች ላይ ከጓደኞችዎ ጋር መጫወት ከፈለጉ እንዴት መጫወት እንደሚችሉ ቀጥለው የተቀመጡትን ሂደቶች ይከተሉ፡-
በመጀመሪያ ፣ ወደ ፎርትናይት ዋና ገጽ ይሂዱ።
በእስክሪንዎ ቀኝ መሃል አካባቢ የሚገኘውን የጌም ሞድ ይጫኑ።
በመቀጠል ፣ የመጣልዎ አዲስ ገጽ ላይ የሚገኘውን “የደሴት ኮድ” የሚለውን ይጫኑ።
በመጨረሻም ፣ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የፎል ጋይስ ካርታ ኮዶች ውስጥ አንዱን ያስገቡ፡-
ሪቨርስ ፎል፦ 4185-8103-4745
ቲልትድ ታዎርስ፦ 1985-3300-5865
ብለንደርዶም ቦምባርድ፦ 7671-9041-8194
አንሊሚትድ ሄክሳጎን፦ 2214-7960-2047
ቢኢን ሲርኪውት፦ 0057-3389-4313
ፔንግዊን ካፕቸር፦ 7485-7322-4774
ለዚህ ሽርክና ምስጋና ይግባውና ፥ ተጫዋቾች ፎርትናይት ክርኤቲቨ ውስጥ የተጨመሩትን የፎል ጋይስ እቃዎችን እና መሰናክሎችን በመጠቀም የራሳቸውን ካርታ መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ፣ የሰሩትንም ካርታ ሌሎች እንዲጫወቱበት ማጋራት ይችላሉ።
በሌሎች ተጫዋቾች የተፈጠሩ የፎል ጋይስ ካርታዎች ዝርዝርን ፣ ጌሙ ውስጥ በሚገኘው የዲስከቨር ማውጫ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የፎርትናይት ምዕራፍ 5 ክፍል 3 ነሐሴ 16 የሚጠናቀቅ ሲሆን ፣ የምዕራፍ 4ን ጅማሮን አስመልክቶም ጌሙ ውስጥ ልዩ ዝግጅት እንደሚደረግ ያስታውሱ።