
ፎርትናይት አዲሱ ማሻሻያውን ስሪት 30.40 ፣ ማክሰኞ ነሐሴ 6 ፣ 2024 አውጥቷል። ይህ ማሻሻያ የምዕራፍ 3 የመጨረሻ እና ምዕራፍ 4 ከመጀመሩ በፊት የሚለቀቅ የመጨረሻውም ማሻሻያ ነው።
ዝማኔ 30.40 ፣ በኢፒክ ጌምስ የተዘጋጀው ሌላ ተወዳጅ ጌም ፎል ጋይስ ጋር በተደረገ ሽርክና መዘጋጀቱ ይበልጥ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በቅርቡ ለወጡ መረጃ ምስጋና ይግባና ፣ በዚህ ዝማኔ ላይ ስለተካተቱ አዳዲስ አማራጮች ፍንጮችን ማግኘት ችለናል።
በፎርትናይት ማህበረሰብ ዘንድ ታማኝነት ያላቸው መረጃ ፈልፋዮች HYPEX እና ShiinaBR ፣ በፎርትናይት ድህረ-ገጽ ላይ ከተለጠፉ መረጃዎች በተጨማሪ ያልተሰሙ መረጃዎችን አጋርተዋል። ዋና ዋና ያልናቸውን ቀጥለን በዝርዘር አስቀምጠናል፡-
ቴስላ ሳይበርትራክ በፎርትናይት መደብር ውስጥ ይገኛል።
የፎል ጋይስ ሽርክና ያካተታቸው ነገሮች፦
መደብር ውስጥ መግዛት የሚችሉት "Everybody Falls (Chill Mix)" የተባለ አዲስ ሙዚቃ።
ፎል ጋይስን መሰረት ያደረገ እና አነስተኛ ጌሞች ያቀፈ አዲስ ካርታ።
“Where Are We Tripping This Time?” የሚባሉ አዳዲስ ተልዕኮዎች።
እነዚህን ተልዕኮዎች በማጠናቀቅ ሊያገኟቸው የሚችሏቸው አዳዲስ ማጌጫዎች።
በአንዳንድ ምንጮች መሰረት ፣ የሌጎ ፎርትናይት ሞድ አንዳንድ አዳዲስ ተጨማሪ ነገሮችን እንደሚያካተትም ተሰምቷል።
ባትል ሮያል ሞድ ላይ ፣ የሚኒ-ገን መመለስ።
ቅዳሜ ነሐሴ 10 የሚደረገውን ዝግጅት ቀሪ ጊዜያት የሚያሳይ ቆጣሪ እንዲካተት ተደርጓል።
ከእነዚህ ዝመናዎች በተጨማሪ ፣ ሌከርሶች በቅርቡ የሚካተቱ ተወዳጅ ገፀ-ባህሪያትን ይፋ ያደረጉ ሲሆን ፣ ከእነሱም መካከል፡-
ድራገን ቦል፦ C17 እና C18.
ኤክስ-ሜን፡- ሳይክሎፕስ ፣ ጁብሊ እና ቆላስየስ
ስታር ዋርስ፡- አዲስ ገፀ-ባህሪዎቭ
ያስታውሱ! ፎርትናይት ምዕራፍ 5 ክፍል 3 ፣ ነሐሴ 16 የሚጠናቀቅ ሲሆን ፣ የምዕራፍ 4ን ጅማሮ አስመልክቶ የሚዘጋጀው ትልቅ ዝግጅትም ፣ ለተጫዋቾች አስገራሚ ነገሮችን ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።