icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ፣ አዲስ ምዕራፍ 

ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ፣ እስካሁን አክቲቪዥን ከሰራቸው ምርጥ ጌሞች መካከል አንዱ ሲሆን ፣ በይፋ ይሁን አፈትልከው የወጡ መረጃዎች እና የሚናፈሱ ወሬዎች አድናዊዎቹም ላይ ይሁን ተቺዎቹ ላይ ከፍተኛ ጉጉትን እየፈጠረ ይገኛል። ምንም እንኳን አክቲቪዥን ይፋዊ ያልሆኑ እና አፈትልከው የሚወጡ መረጃዎችን ለማፈን ጠንክሮ እየሰራ ቢሆንም ፣ ቁልፍ የሚባሉ መረጃዎች ማህበረሰቡ እጅ ላይ ቀድመው በመግባታቸው ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይበልጥ ውዝገብ እና ጉጉት እንዲፈጠር አድርጓል።  

አፈትልከው የወጡ መረጃዎች፡- 

የኑክ-ታውን መመለስ፡- አፈትልከው ከወጡ ዋና መረጃዎች መካከል አንዱ አንጋፋው የኑክ-ታውን ካርታ ተመልሶ መምጣት ሲሆን ፣ ይህም ለነባር ተጫዋቾችን የሚያስደሰት እና አዳዲስ ተጫዋቾችንም መሳብ የሚያስችል ትልቅ ዜና ነው። 

አዲስ ካርታዎች፡- ብላክ ኦፕስ 6 አንጋፋውን የኑክ-ታውን ካርታ ብቻ ሳይሆን ፣ 20 አዳዲስ የብዛት ተጫዋቾች ሞድ ካርታዎችን እና፣ የተለያዩ የአጨዋወት አማራጮችንም ይዞ እየመጣ ነው። ከነዚህም መካከል 12ቱ ለክላሲክ 6ለ6 ግጥሚያዎች ፣ 4ቱ ደግሞ ለ2ለ2 ወይም ስትራይክ ሞድ የተዘጋጁ ናቸው። 

የአዲሶቹ ካርታዎች ስም ዝርዝር፡- 

  • ባቢሎን 

  • ካናልስ 

  • ካታኮምብ 

  • ዲግ 

  • ፋየሪንግ ሬንጅ 2 

  • ፍላት 

  • ሃሴንዳ አልት 

  • አይላንድ 

  • ፕላጅ 

  • ራዳር 

  • ሬድ ካርድ 

  • ራሽያን ቤዝ 

  • ስቲልዝ 

  • ስትሪፕ ሞል 

  • ትሬን ግሬቭያርድ 

  • ቪልድ 

  • ቮርኩታ 

  • ቮርኩታ ማይን. 

እነዚህ ልዩ ልዩ ገጽታ ያላቸው ካርታዎች ፣ ተጫዋቾች ሰፊ እን በርካታ አከባቢዎችን ማሰስ እንዲችሉ እና ልዩ የተጨዋታ ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ናቸው። 

ተወዳጁ የዞምቢ ሞድም ጭብጡን የቀድሞዎቹ የሪኪውም ቡድን አባላት ላይ እና ፣ ኤድዋርድ ሪችቶፈንን በማካተት ፣ አዲስ ታሪካዊ ጭብጥን ይዞ የሚመለስ ይሆናል። 

"ኦምኒሙቭመንት" የተባለ አዲስ አማራጭም የሚያስተዋወቅ ሲሆን ፣ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የእንቅስቃሴ ነጻነትን የሚሰጥ ሲሆን ፣ ይህም ጌሙን የበለጠ መሳጭ እና ልዩ ያደርገዋል። ይህም አዲስ ቴክኖሎጅን ከነባር ዝመናዎች ጋር በማጣመር የተዘጋጀ ሲሆን ፣ ነባር እና አዲስ ተጫዋቾችን ቀልብ በቀላሉ መማረክ የሚችል ትልቅ ማሻሻያም ነው

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !