
ኑክ-ታውን ከመጀመሪያው ኮል የኦፍ ዲውቲ ምዕራፍ ጀምሮ የሚታወቅ ካርታ ነው። ጥቅምት 25 የሚለቀቀው የኮል የኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 (Bo6) ላይም ይህ ታሪካዊ ካርታ ተመልሶ ይመጣል አይመጣም የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል።
ኑክ-ታውን ኮል የኦፍ ዲውቲ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የቆየ ታሪካዊ ካርታ ሲሆን ፣ በጀብዱዎች እና በልዩ ገጽታው የሚታወቅ ፣እና አዳዲስ ምዕራፎች በወጡ ቁጥር ብዙዎች በጉጉት የሚጠብቁት ታላቅ ካርታም ነው። የብላክ ኦፕስ 6 መውጫ በተቃረበ ቁጥር ፣ የኑክ-ታውንን መካተት የሚጠቁሙ በርካታ ጭምጭምታዎች እየተሰሙ ይገኛሉ።
በቅርቡ በተካሄደው የኤክስ-ቦክስ ጌሞች ማሳያ ፕሮግራም ወቅት የትሬይያርች ቡድን አባላት በብላክ ኦፕስ 6 ውስጥ የሚያሳይ ምስሎች የወጡ ሲሆን ፣ ከእነዚህ ምስሎች ውስጥም ፣ ኑክ-ታውን በካርታ አማራጭ ዝርዝሮች ውስጥ ተቀምጦ ታይቷል። ይህ ፍንጭም የአድናቂዎችን ተስፋ ያለመለመ እና የዚህን ታሪካዊ ካርታ መመለስ ፍንጭ ያሳየ ነው።
በኮል ኦፍ ዲውቲ ማህበረሰብ ዘንድ ታማኝነት ያለው ቦብ ኔትዎርክዩኬ ፣ የብላክ ኦፕስ 2 ኑክ-ታውን በ2025 የሚወጣው Bo6 ላይ ሊመለስ እንደሚችል ገልጿል። ይህ እትም በተለይ በልዩ ንድፉ እና ልዩ የአጨዋወት አቀራረቡ ተወዳጅ ነው ፣ የእዚህ ዜና ዕውን መሆንም ተከታታይ ምዕራፎቹን ሲጫወቱ ለነበሩ ነባር ተጫዋቾች ታላቅ ዜና ነው።
ብላክ ኦፕስ 6 ፣ 16 አዲስ ባለብዙ ተጫዋቾችን ካርታ በማካተት የሚጀምር ሲሆን ፣ 12ቱ ለ6ለ6 ውጊያዎች እና 4ቱ ደግሞ ለ 2ለ2 ወይም ለ6ለ6 ሞድ የተዘጋጁ ናቸው። ይሁን እንጂ ኑክ-ታውን ጌሙ ሲለቀቅ የሚኖሩ ካርታዎች አካል ይሁን ወይም በኋላ DLC ጥቅሎች ጋር ቆይቶ የሚለቀቅ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ነገር የለም።
ትሬይያርክ እና አክቲቪዚን ፣ ኑክ-ታውን በተጫዋች ዘንድ ያለውን ትልቅ ተጽእኖ በሚገባ ያውቃሉ። ኑክ-ታውን የካርታዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ገና ያልተረጋገጠ ነገር ቢሆንም ፣ አሁን ያሉ ፍንጮች ግን ጥሩ ምልክት በመሆናቸው ፣ ኑክ-ታውን ኮል ኦፍ ዲውቲ ላይ ቢካተት የሚገርም ነገር አይሆንም።
የኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 መውጫ ቀን በቀረበ ቁጥር ፣ ስለ ኑክታውን መመለስ የሚሰጡ ግምቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በየማህበራዊ ሚዲያዎቹ የሚወጡ ጭምጭምታዎችም ተጫዋጮችን በተስፋ እየሞሉ ይገኛሉ ፥ ሆኖም ግን ይህን አንገብጋቢ ጥያቄ እና ውጥረት ሊያረጋጋው የሚችለው ብቸኛ ነገር ይፋዊ ማስታወቂያ ብቻ ነው። እስከዚያው ድረስ ፣ ተጫዋቾች ስለ ኑክ-ታውን በይፋ የሚወጡ ታማኝ ዜናውችን እንዲከታተሉ ይመከራል።